ግምቱ 64 ሚሊዮን ብር የሆነ ወርቅ በህገ-ወጥ መንገድ ደብቆ ኬላ ጥሶ ለማለፍ የሞከረው አሽከርካሪ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፤ የጉምሩክ እና በአካባቢው በነበሩ የኦሮሚያ ክልል የሚሊሻ ኃይል ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ። ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ከቀኑ በ11:30 በኦሮሚያ ክልል ነጌሌ ቦረና ከተማ ዶሎ በር ኬላ ሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ-3-ኢት AA 03775 የሆነ ትዮታ ደብል ፒክአፕ ላንድ ክሩዘር ከነጋሌ ከተማ ወደ ሶማሌ ክልል ለመሄድ ቀጥታ በጉምሩክ ኬላ በኩል መጥቶ ለፍተሻ ሲያስቆሙት ፊቃደኛ ባለመሆን በኬላው ጎን ባለው የእግረኛ መንገድ በመጠቀም ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር ለማስቆም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ጥይት ቢተኩሱም ሳይቆም በማምለጥ ላይ እያለ የጉምሩክና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ለነበረው ኮማንድ ፖስት መረጃውን በፍጥነት ማስተላለፉን … [Read more...] about ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ
illegal items
የምግብ ዘይት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ተከማችቶ ተገኘ
በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 03 ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል። ክ/ከተማው በ11 ሱቆች ላይ ተደረገ ባለው ፍተሻ 442 ሊትር ዘይት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን አሳውቋል። ፍተሻ የተደረገው በወቅታዊ የዋጋ ንረት ምክንያት ካሉ 6 ቀጠናዎች በ3ቱ ቀጠናዎች ላይ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል። ክ/ከተማው በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት ባልተገባ ቦታ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ተደብቆ መገኘቱን የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ድርጊት የሚፈፅሙትን "ሌባን ሌባ " ሲል እንዲያጋልጥ ጥሪ አቀርቧል። በአግባቡ ስራቸው ላይ የሚገኙ ነጋዴዎች አሁን በያዙት ልክ ዘይትን ወደ ፊት በማምጣት መሸጥ ይኖረባቸዋል የተባለ ሲሆን ህገወጥ ስራዎችን በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ ንግድ ፍቃድ መሰረዝ ጨምሮ ጠበቅ ያሉ እርምጃዎች … [Read more...] about የምግብ ዘይት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ተከማችቶ ተገኘ
መረን የለቀቀ ግፍ፤ በዛገ በርሜል የተሠራ የጎመንዘር ዘይት ለሕዝብ
በሻሸመኔ በህገወጥ መንገድ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረተ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ ድርጅት ታሸገ። በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ከሻሸመኔ ጤናና ጤና ነክ የስራ ሂደት ተቆጣጣሪ ጋር በጋራ በመሆን በኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የደቡብ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በምግብ ዘይት ላይ የገበያ ቅኝት መሥራቱን የኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል። በዚህም ቅኝት ከሚመለከተው የተቆጣጣሪ አካል የዘይት ምርት ለማምረት የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው፣ የምርት ማሸጊያ መስፈርት ባላሟላ፣ ንጽህናዉ ባልጠበቀ የአመራረት ሂደት እንዲሁም ዘይት ለማምረት ምቹ ባልሆነ ቤት ውስጥ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረቱ ለህብረተሰቡ እየሸጠ የተገኘ አንድ ድርጅት ላይ ምርት የማምረት ሥራዉን እንዲያቆሙና ድርጅቶቹ ከተመረተው የዘይት … [Read more...] about መረን የለቀቀ ግፍ፤ በዛገ በርሜል የተሠራ የጎመንዘር ዘይት ለሕዝብ