በሻሸመኔ በህገወጥ መንገድ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረተ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ ድርጅት ታሸገ።
በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ከሻሸመኔ ጤናና ጤና ነክ የስራ ሂደት ተቆጣጣሪ ጋር በጋራ በመሆን በኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የደቡብ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በምግብ ዘይት ላይ የገበያ ቅኝት መሥራቱን የኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።
በዚህም ቅኝት ከሚመለከተው የተቆጣጣሪ አካል የዘይት ምርት ለማምረት የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው፣ የምርት ማሸጊያ መስፈርት ባላሟላ፣ ንጽህናዉ ባልጠበቀ የአመራረት ሂደት እንዲሁም ዘይት ለማምረት ምቹ ባልሆነ ቤት ውስጥ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረቱ ለህብረተሰቡ እየሸጠ የተገኘ አንድ ድርጅት ላይ ምርት የማምረት ሥራዉን እንዲያቆሙና ድርጅቶቹ ከተመረተው የዘይት ምርትና ለዘይት ምርት የሚገለገሉበት የቅባት እህል (ጎመንዘር) ጋር እንዲታሸጉ መደረጉ ተገልጿል።
በገበያ ቅኝቱ ወቅት ባጠቃላይ በግምት 150 ኩንታል በላይ የጎመንዘር እህል እና በዛገ በርሜል የተከማቸ 80 በርሜል ህገወጥ ዘይት አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋው 2 ሚሊየን 244 ሺህ ብር የሚያወጣ ህገወጥ የዘይት ምርት ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው መደረጉንም ባለስልጣኑ አስታውቋል።
ከድርጅቶቹ ጋር በተያያዘ ቀጣዩን የክትትል ሥራዉን ከኦሮምያ ጤና ቢሮ ጤ/ጤ/ግ/ጥ/ቁ/የስራ ሂደት እና ከሻሸመኔ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን የሚሰራ ሲሆን በቀጣይም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተመሳሳይ ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም የኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ገልጿል፡፡ (አዲስ ማለዳ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply