የጦር መሳሪያ ጨምሮ ሌሎች ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በዚህም፡-
18 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ደረቅ ጫት፣ እህል፣ ትምባሆ እና ሌሎች ዕቃዎች በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ እና መቅረጫ ጣቢያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 13 ሚሊዮን በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለውና 8,980 ኪ.ግ መጠን እንዳለው የተገለጸው ደረቅ ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ሲጓጓዝ የተያዘ ነው፡፡
- ከሱማሌላንድ ወደ ጅጅጋ ሊገቡ የነበሩ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም በቀብሪበያህ በኩል በኤፌሳር እና ሚኒባስ ተጭኖ ሊገባ የነበረ የውጭ ሀገር ማሽላ እና ዘይት 3,500,000 ብር አጠቃላይ ግምታዊ ዋጋቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡
- በኢትዮጵያ ለሚገኙ ለደቡብ ሱዳን ስደተኞች በእርዳታ የገባ ጠቅላላ ግምታዊ ዋጋው 1,141,599 ብር የሆነ ማሽላ፣ ስንዴ እና አተር ክክ ከጋምቤላ ክልል ወደ አዲስ አበባ በህገ-ወጥ መንገድ በመጓጓዝ ላይ እያለ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
- ከአዲስ አበባ ወደ ቆቦ ከተማ ሲጓዝ ከነበረ መለስተኛ የጭነት ተሸከርካሪ 3 (ሶስት) ህገ ወጥ ሽጉጦች ሴራሚክ ውስጥ ደብቆ ለማለፍ ሲሞክር በወልደያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ጉምሩክ ሰራተኞች በተደረገ ፍተሻ መስከረም 11 ቀን 2013 ተይዟል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ አሽከርካሪው እና ረዳቱ በቁጥጥር ስር ውለው በክልሉ ፖሊስ ተጨማሪ ማጣራት እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የገቢዎች ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply