ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የኮንትሮባንድ ጉዳይ መላ እንዲበጅለት ዜጎች እየጠየቁ ነው ከኢትዮጵያ በኮንትሮባንድን በመላላክ ወደ ኤርትራ የሚሸጋገሩ ቁሳቁሶች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እየጎዳ መሆኑ፣ በሕዝብ የእለት ተእለት ፍጆታ ላይም ተጸዕኖ እያሳደረ መሆኑን የሚያውቁ መንግሥት መላ ሊፈልግ እንደሚገባ እያሳሰቡ ነው። በትግራይ ክልል በሕዝብ ቁጥጥር በአንድ አቅጣጫ ብቻ በሶስት ወር ውስጥ ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ መያዙ ተገልጿል። በውጭ ገንዘብ ምንዛሬ፣ በግንባታና በዕለታዊ ፍጆታ ዕቃዎች ላይ በስፋት ኮንትሮባንድ ላይ የተሰማሩና የኤርትራ መንግሥት ድጋፍ የሚያደርግላቸው ክፍሎች የአገሪቱን ኢኮኖሚ እየተፈታተኑት እንደሆነ የሚገልጹ ወገኖች “ወዳጅነትና የኮንትሮባንድ ዝርፊያ ለየቅል ናቸው” ሲሉ መንግሥት መስመር ሊያስይዘው እንደሚገባ አመልክተዋል። ቀደም ባሉት … [Read more...] about ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው
human trafficking
በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ
በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 19 ህጻናትንና 6 አዘዋዋሪ ሴቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። እድሜያቸው ከ5 እስከ 10 የሚገመቱ ህጻናቶችን አዘዋዋሪዎቹ ማዳበሪያ በማልበስ አፍነው ሲያጓጉዟቸው እንደነበር የገለጹት የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እንስፔክተር ሸምሱ ጠቁመዋል። ህጻናቱ ወራቤ ከተማ ሲደርሱ ባሰሙት ጩሀት መነሻ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተከታትሎ ከተማ አስተዳደር ህጻናቱንና አዘዋዋሪ እናቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል። አዘዋዋሪ እናቶች በሰጡት አስተያየት በዚህ ተግባር ተሳታፊዎች ቁጥር በርካቶች መሆናቸውን ገልፀው በጠዋቱ ክፍለጊዜ ህጻናትን የጫነ አንድ መኪና ወደ አዲስ አበባ መጓዙንም ተናግረዋል። የዚህን መሰል የወንጀል ተግባራትን ከጸጥታው አካል ጎን በመሆን ሊከላከልእንደሚገባም እንስፔክተሩ ጥሪ … [Read more...] about በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ