
በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 19 ህጻናትንና 6 አዘዋዋሪ ሴቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
እድሜያቸው ከ5 እስከ 10 የሚገመቱ ህጻናቶችን አዘዋዋሪዎቹ ማዳበሪያ በማልበስ አፍነው ሲያጓጉዟቸው እንደነበር የገለጹት የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እንስፔክተር ሸምሱ ጠቁመዋል።
ህጻናቱ ወራቤ ከተማ ሲደርሱ ባሰሙት ጩሀት መነሻ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተከታትሎ ከተማ አስተዳደር ህጻናቱንና አዘዋዋሪ እናቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል።
አዘዋዋሪ እናቶች በሰጡት አስተያየት በዚህ ተግባር ተሳታፊዎች ቁጥር በርካቶች መሆናቸውን ገልፀው በጠዋቱ ክፍለጊዜ ህጻናትን የጫነ አንድ መኪና ወደ አዲስ አበባ መጓዙንም ተናግረዋል።
የዚህን መሰል የወንጀል ተግባራትን ከጸጥታው አካል ጎን በመሆን ሊከላከልእንደሚገባም እንስፔክተሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።(የስልጤ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply