
የመለስ ዜናዊ የግል ጠባቂ/አጃቢ የነበረው ሚኪ ራያ ሰሞኑን በማኅበራዊ ሚዲያ በተሰራጨ ቪዲዮ ላይ የቀድሞ ጌታውን ማንነት ባልታወቀ ምክንያት እያዝረከረከው ነው። በትግሪኛ የተናገረውን አስፋው አብርሃ በቴሌግራም ገጹ ተርጉሞ አቅርቦታል፤
መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ ከኢትዮጵያ በበለጠ ለኤርትራ ያስቡና ይጨነቁ ነበር። ይህ የሁለቱ ሰዎች ስሜትና ባህሪ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገልጧል – ከ1992ቱ ጦርነት በፊት፣ በጦርነቱ ወቅት እና ከጦርነቱ በኋላ ምንም ያልተቀየረ ስሜት!
ከጦርነቱ በፊት ….
ሚኪ ራያ “መለስ ዜናዊ መዝናናት ሲፈልግ ወደ አስመራ ይመላለስ ነበር፤ በረራውም Unofficial በረራ ነበር ይለናል – ያው በድብቅ ማለት መሆኑ ነው።
“መለስ ዜናዊ ከስራ ውጪ መዝናናት ሲፈልግ አስመራ ነበር የሚሄደው። የራሱን ሰዎች ብዙም አይቀርባቸውም ነበር። እኔ ቢያንስ ለሦስት ጊዜ ያህል ከሱ ጋር ወደ አስመራ unofficial በረራዎችን አድርገናል። ኢሳያስና መለስ በሁለት አገሮች ውስጥ ያሉ ወንድማማቾች ይመስሉ ነበር። በቃ በሁለት አገር ያሉ ሁለት ዳይናስቲዎች ነበሩ ማለት ትችላለህ። Scary ነው ግን እውነታው እሱ ነበር”።
ሚኪ ራያ መለስ ዜናዊን በ1992ቱ የባድመው ጦርነት ወቅት በዚህ መልኩ ይገልጸዋል፤
ጦርነቱ ተጀምሮ ሠራዊቱ ውጊያ ላይ እያለ መለስ ዜናዊ ለአስመራ እጅግ ከመጨነቁ የተነሳ ፕሮቶኮልንና አግባብነትን የተቃረነ አስነዋሪ ሥራ ሠርቷል።
ጦርነቱ ተጀምሮ የኢትዮጵያ ወታደሮች እየተዋደቁ ባለበት ቅፅበት አገሪቱ (ኢትዮጵያ) ሳታውቅ መለስ ወደ አስመራ ሄዶ ነበር። አንድ መሪ አገሪቱ በመሰል ወሳኝ ሁነት ውስጥ እያለች ከወታደራዊ ካውንስልም ሆነ ከካቢኔው ዕውቅና ውጪ በግሉ ወስኖ በግሉ የሚፈፅመው ምንም አይነት ተነሳሽነት ሊኖረው ተገቢ አልነበረም። መለስ ግን አድርጎታል። ጦርነቱ ኤርትራን እንደሚጎዳ ስላወቀ የተጀመረው ጦርነት እንዲቆም ኢሳያስን ለማሳመን ነበር ወደ አስመራ የሄደው። በነገራችን ላይ መለስ ዜናዊ ኤርትራን የሚመለከትበትና የሚያስተናግድበት መንገድ በፃድቃንና በስዬ ተደጋጋሚ ወቀሳና ትችትን አስተናግዷል።
ወደ ታሪኩ ስንመለስ ጦርነቱ ተጀምሮ በሁለቱም ወገን ያለው ወታደር በተጋጋለ ተኩስ ውስጥ ተጥዶ እያለ እሱ ወደ አስመራ መሄዱ ምን ያህል በሕይወቱ ላይ እንደፈረደ ለመገመት አይከብድም። የሚያሳዝነው ግን ከኢሳያስ ጋር የነበረው ግንኙነት በቅሌት ነበር የተጠናቀቀው።
እንደ ሚኪ ራያ ገለፃ ከሆነ በወቅቱ ከመለስ ጋር የሄደውና ከውጪ ሆኖ ሲጠብቅ የነበረ ታጋይ (አሌ ይባላል) ጭቅጭቅ ሰምቶ ወደ ውስጥ ሲገባ ኢሳያስ መለስ ዜናዊን “ጨምላቃ” ብሎ ሲሰድበው ሰምቷል። መለስም ጭንቅላቱን እንዳዘቀዘቀ ድምፅ ሳያሰማ ስድቧን ጠጥቷታል!
መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን!
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply