በሱዳን ለአንድ ዓመት የዘለቀው የእርስ በእርስ እልቂት ብዙ ተዋንያኖች አሉበት። ከአርቡ ዓለም፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪቃ፣ ሩሲያና አሜሪካንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት የሚዳክሩበት በዚህ ጦርነት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ መገኘቱ ይፋ መሆኑን ተከትሎ አማራ ክልል ውስጥ ያሉ ታጣቂዎችን ከፍፍሏል።
ትህነግ በድርጅት ደረጃ በውስጡ አለመጋባባት እንዳለበት፣ ከጊዜያዊ አስተዳደሩም ጋር ስምምነት እንደሌለው ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ዳዊት ከበደ አቶ ጌታቸው ረዳ “ከሱዳን ተፋላሚዎች ጀርባ ትህነግ መኖሩን ጌታቸው ረዳ አረጋግጠዋል” ሲል ሚስጢር ያለውን ይፋ አድርጓል። በመረጃው ለምን አቶ ጌታቸው ብቻ ተለይተው በዚህ ጉዳይ ግንባር ሊሆኑ እንደቻሉ ወይም እንደተፈልገ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። በተደጋጋሚ እንደሚባለው ከራያ ወገን መሆናቸው ለያዙት ስልጣን ችግር ሆኖባቸዋል።
ከሱዳን የወጣውንና ዳዊት ከበደ ያሰራጨውን መረጃ የገመገሙ “እኛም አውቀናል” ብለዋል። እነዚሁ ወገኖች ትህነግ ከአማራ ታጣቂ ሃይሎችና ፋኖዎች ጋር አብሮ የሚሰራው እንዴት ነው? በሚል የተለዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል። ትህነግ በሱዳን ጦርነት ውስጥ ሚና ለይቶ አሁን ድረስ ተሳታፊ መሆኑ ይፋ መሆኑ ” በሱዳን ተንደርድሮ ማን ላይ ጥቃት ለመክፈት ነው? ወራጅ አለ” በሚል አቋማቸውን ያሰሙ አሉ። ይህንኑ ተከትሎ አፍቃሪ ትህነግ የሆኑ ሚዲያዎች ” እስክንድርን የማትቀበል ፋኖ ከትህነግ ጋር መስራት አትችልም” በሚል ንዴት የተቀላቀለበት ማብራሪያ ሲሰጡ ተሰምቷል። እስክንድርን መሪ እንዲሆን የመረጡበት ምክንያት ግን አልተብራራም።
በሱዳን በኩል የሚደረገው ጥምረት ነገ በወልቃይት በኩል ለሚደረገው ፍልሚያ መንገድ ጠራጊ መሆኑን በማስላት የውስጥ አንድነታቸውን ማጠንከሩ እንደሚበጅ እየገለጹም ያሉ አሉ። ይህ እየሆነ ባለበትና ከጎጃም አካባቢ ያሉ ፋኖዎችና አንዳርጋቸው ጽጌ ከሁዋላ ሆነው የሚመሩት የነ እስክንድር አደረጃጀት አቋማቸውን ደግመው እንዲያስቡ ማስጠንቀቂያ በሚነገርበት ወቅት ዳዊት ከበደ ያጋራው ሚስጢር ጉዳዩን አጉኖታል።
“ዛሬ” ይላል የቀድሞ አውራ አምባ የዜና አውታር ባለቤት ዳዊት ከበደ፣ “ዛሬ የአህዮች ቀን ነው። አህዮችና የአህያ ባህሪያትን የተላበሱ እኛ ካለፍን ሳሩ አይብቀል በሚል ለሚነቀሳቀሱ እንኳን ለዚህ ቀን አደርሳችሁ” ሲል መልካም ምኞቱን ያስቀድማል።
ዳዊት ይህን ያለው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በጄኔራል መሃመድ ሃምዳን ደጋሎ የሚመራውን የፈጥኖ ደራሽ ጦር RSF ( Rapid Support Forces) ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ነው።
በጄኔራል መሃመድ ሃምዳን ደጋሎ ወይም ሂመቲ የሚመራውን የፈጥኖ ደራሽ ጦር ክንዳቸውን በአንድ አስተባብረው ከሱዳን ወታደራዊ ሃይል /SUDANESE ARMED FORCES SAF/ ጀኔራል አልቡርሃ ጋር በማበር እየወጉት ያሉትን ጀሃዲስት፣ ቅጥረኞች፣ አሸባሪዎች ወዘተ በማለት ይጠራቸዋል።
ጀነራል ደጋሎ የሚመሩት ይህ ሃይል የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግን ከነዚህ ሃይሎች አንዱ አድርጎ በመፈረጃ ከሱዳን ወታደራዊ ሃይል /SUDANESE ARMED FORCES SAF/ ጀኔራል አልቡርሃ ጋር አብረው እየወጉት እንደሆነ “በቂ መረጃና ማስረጃ” አለኝ ሲል ነው መግለጫ ያወጣው።
በግንቦት 4 ቀን 2024 የወታው የሃምዳን ዳጋሎ መግለጫ በቀጥታ ትህነግን ወይም ወያኔን የሚመለከት ቢሆንም መግለጫውን ” ፍጹም ሀሰተኛ ነው ” ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ነው ያስተባበለው።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በመንግስት የተወከለ ቢሆንም፣ ትህነግ በቅጥረኛነት በዳጋሎ ሃይሎች ላይ ቃታ መሳቡን ተጠቅሶ ለተሰራጨው መግለጫ ምላሽ የሰጡት አቶ ጌታቸው ” ሁለት ቦታ እየተጫወቱ ነው” የሚል መረጃ ነው ዳዊት ከበደ ያወጣው።
“በሱዳን የሚገኙ የወያኔ ወታደሮች ከአልቡርሃን ሰራዊት ጋር ወግነው ወታደሮቼን እየወጉ ነው” ሲል በይፋ መግለጫ ያወጣው የጄኔራል መሃመድ ሃምዳን ደጋሎ ሃይል ከበቂ በላይ ማስረጃ እንዳለው አመልክቷል። ከዚህ በፊት ቆስለው የተማረኩ የትህነግ ወታደሮችን ወደ አገራቸው መሸኘቱንም በመግለጫው ጠቅሶ አስጠንቅቋል። ዳዊት “ከ150 ሺህ እስከ 250 ሺህ በወር እንደሚከፈላቸው የግምት አክቲቪስቶች ተርታ እፈረጃለሁ በሚል ፍርሃቻ ሃቅ ከመናገር አላፈገፍግም” ሲል ሚስጢራዊ መረጃውን ያወጣው።
ዳዊት ከበደ ” የአህዮች ቀን ነው እንኳን ለአህዮች ቀን አደረሳችሁ” ሲል ተሳልቆ በጀመረውና በፌስ ቡክ ገጹ ላይ በትግርኛ ያሰራጨው መረጃ ከወራት በፊት የተሰማ ነበር። ዝርዝሩ ባይገለጽም አቶ ጌታቸው ለህክምና ዱባይ ሄደው ከሱዳን ሃይሎችና ከተለያዩ ታጣቂ ሃይሎች ጋር መገናኘታቸው ተገልጾ ነበር።
ዳዊት እንዳለው ግን አቶ ጌታቸው ረዳ በህክምና ስም የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ከሄዱ በሁዋላ ሁለት ተግባራትን ፈጽመዋል። ይህ ተግባራቸው ነው ” እኛ ካለፍን” እንዳሉት አህዮች ያስቆጠራቸው።
አቶ ጌታቸው በኤምሬትስ በጄኔራል መሃመድ ሃምዳን ደጋሎ የሚመራውን የፈጥኖ ደራሽ ጦር ሰዎች ጋር መገናኘታቸውን የጠቀሰው ዳዊት፣ ከተገናኙም በሁዋላ በውይይታቸው “ከአልቡርሃን ጦር ጋር በመሆን የRSF – የጋማሎን ሃይል የሚወጉት የእኛ ሃይሎች ናቸው” ሲሉ መናገራቸውን ይፋ አድርጓል።
ከአቶ ስብሃት ነጋና ከትህነግ ቁልፍ አመራሮች ጋር የቀጥታ ግንኙነት እንደነበረው፣ አሜሪካ ድረስ ለድርጃታዊ ስራ ተጉዞ እንደነበር በገሃድ ያመነው ዳዊት ከበደ፣ አቶ ጌታቸው በሁለተኛ ደረጃ እንደፈጸሙት የተቀሰው ጉዳይ ከአረብ ኤምሬትስ ባለስልጣናት ጋር መገናነታቸውን ነው።
ለዳዊት በማሳረጊያው ላይ “አቶ ጌታቸውም ሆኑ እሳቸውን የሚጻረሯቸው ወንጀለኞች ናቸው። ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል” እንዲል መነሻ የሆነው ” ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ባለስልጣናት ጋር የተደረገ ውይይት ነው። በእናንተ የሚደገፉ የ RSF ታጣቂዎች ውጤታማ ሊሆኑ አይችሉም ምክንያቱም አል-ቡርሃን እየታገዘ ያለው በራሳችን (ትህነግ) ሃይል ነው” ሲሉ አቶ ጌታቸው መናገራቸው ነው።
አቶ ጌታቸው ለRSF ታጣቂዎች አመራሮችና ለአረብ ኢምሬትስ ባለስልጣናት የትህነግ ሃይሎች ከጄነራል አልቡርሃን ሃይል ጋር ህብረት ፈጥረው እየተዋጉ መሆናቸውን ጠቅሰው ማረጋገጫ መስጠታቸውን ሚስጢር የሚያገኘው ዳዊት ማስታወቁን ተከትሎ አቶ ጌታቸው ላይ ከፍተኛ ቅሰቀሳ ተከፍቷል።
እንደ ዳዊት አባባል የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል ትህነግን ጠቅሶ “ቅጥረኛ” ሲል መግለጫ ያወጣው በአቶ ጌታቸው መረጃ መሰረት ነው። ዳዊት እንደሚያምነው አቶ ጌታቸው ይህን ባይሉ ኖሮ “ጸለምት” ያለው ስም አጥፊ መግለጫ አይወጣም ነበር።
ዳዊት ይህን ሁሉ ለማለቱ በዋናነት ” እንዴት ሁለት ጊዜ ማሰብ ተሳነን” ሲል ጠይቆ አቶ ጌታቸው የሰጡት መረጃ ” በስደት ሱዳን ላሉ የትግራይ ተወላጆች ምን ይዞ እንደሚመጣ እንዴት ማሰብ አልተቻለም” የሚለው ነው። ዳዊት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ያወጣውን መግለጫ አስመልክቶ ምንም አላለም።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል “የህወሓት ታጣቂዎች ከሱዳን ወታደራዊ ሃይል ጋር በማበር በቅጥረኛነት እየወጉኝ ነው ” በማለት ያወጣውን መግለጫ ሲያጣጥል፣ “የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መግለጫ ለዘመናት የቆየውና በፅኑ መሰረት የቆመው የትግራይና የሱዳን ህዝቦች ወዳጅነት ከግምት ያላስገባ ነው” በማለት ነው።
የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በሱዳን የሺዎች ህይወት በመቅጠፍ ላይ ያለውን የአገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ላይ “የህወሓት ሃይሎች ተሳትፈዋል የሚል ክስ ማቅረቡ ሃሳባዊና መሬት ላይ መረጋገጥ የማይችል የለየለት ፈጠራ ነው ” ሲል ነው አስተዳደሩ “ከደም ንጹህ ነኝ” ያለው።
የትግራይ አስተዳደር፣” በሱዳን ያለው የአርስበርስ ግጭት ዓለምአቀፍ መልክ ለማስያዝና እርዳታ ለማግኘ ያለመ ነው ” በሚል ከክሱ ጋር ግንኙነት የሌለው ሃረግ በማጣቀስ ራሱን ለመከላከል ሞክሯል። ይሁን እንጂ ዓለም ዓቀፍ እውቅና አግኝቶ የድጋፍ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ለሚረዱ የትግራይ አስተዳደር ምን ለማለት እንደፈለገ ግልጽ አልሆነላቸውም።
በመግለጫው “በመሰረቱ ህወሓት የፓለቲካ ድርጅት እንጂ የሚያዘውና የሚያስተዳድረው ታጣቂ ሃይል የለውም” ሲል በመግለጫው አካቷል። ይህ ማስተባበያው “ከሚሰጠኝ በጀት ላይ በማንሳት 250 ሺህ ጦር ካምፕ አስቀምጬ እየቀለብኩ ነው” ላሉት አቶ ጌታቸው በስማቸው ከወጣው መግለጫና ማብራሪያቸው ጋር እንዴት የሚጋጭ ሆኗል።
ትህነግ ሲፈጠር ጀምሮ ታጣቂ ያሰባሰበ፣ ሲዋጋ የኖረ ግማሽ ምዕተ ዓመት የዘለለ ድርጅት ነው። ትህነግ ሰፊ የጦር ሃይል የገነባ፣ ይህንኑ ሃይሉን ሲያስመርቅና ሲሸልም፣ ሲያወድስና በምርቃት ስነ ስርዓት ወደ ውጊያ ሲሸኝ በተደጋጋሚ በራሱና በደጋፊዎቹ ሚዲያዎች ሲያስተላልፍ እንደነበር የሚያነሱ፣ ይህን ሃቅ እንዴት ሊዘለው እንደሚችል ግራ በመጋባት መግለቻውን ተከትሎ እያስታወቁ ነው።
የዚህ ሁሉ ሂደት ውጤት የሆነው የትግራይ መከላከያ ህያል ቲድኤፍ ተብሎ ተሰይሞ በዓለም ሚዲያ የሚታወቅ፣ ይህ ሃይል በፍጹም እንደማይበትን ምሎ የሚገዘትበት እንደሆነ እየታወቀ “አንድም ታጣቂ ሃይል የለኝም” የሚል ምላሽ መሰጠቱ ግራሞትን ፈጥሯል። ” ታዲያ የማን ሃይል ነው ውጊያ ሲከፍትና ድ፤ አገኘ እየተባለ ሲነገርለት የነበረው?” የሚል ጥያቄ ለሚያነሱ ምልሽ የሚሰጡ አልተሰሙም።
“በመሰረቱ ህወሓት የፓለቲካ ድርጅት እንጂ የሚያዘውና የሚያስተዳድረው ታጣቂ ሃይል የለውም ” ማለቱን ተከትሎ እስካሁን የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ ያለው ነገር የለም።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ በሱዳን የተፈጠረው አውዳሚ የአርስ በርስ ጦርነት የሚያስከትለው አደጋ በመረዳት የውጭ ሃይሎች በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ ጥሪ ሲያቀርብ፣ ዋናው ተዋንያን ግብጽ ሆና ሳለ በስም አልጠቀሳትም። ሻዕቢያንም አላነሳም። የሱዳን ጦርነት ለኢትዮጵያ ስጋት ሆኖ ሳለ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ያለውም ነገር የለም። መንግስትም ጭጭ ብሏል።
በሱዳን የስደተኛ ካምፕ ውስጥ የትህነግ ሃይሎች ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዱ እንደሆነ መረጃ እንዳለው ተመድ ማስታወቁ አይዘነጋም።
“በማይካድራ የተፈጸመው ግድያ ‘የጦር ወንጀል’ ሊሆን እንደሚችል ተመድ” ሲገልጽ ኢሰማኮ ከሕዳር 5 እስከ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በማይካድራ ከተማ፣ በአብርሀጅራ፣ በሳንጃ፣ በዳንሻ፣ በሁመራ እና በጎንደር ከተሞች ተዘዋውሮ ባደረገው ምርመራ የደረሰበትን ግኝት ይፋ ባደረገበት ሪፖርቱ፣ “ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በማይካድራ ከተማ የተፈጸመው ጭፍጨፋ በወቅቱ በስልጣን ላይ በነበረው የአካባቢው መስተዳድር የጸጥታ መዋቅርና ሳምሪ በተባለ ኢ-መደበኛ የወጣቶች ቡድን ነው” ብሏል።
ይህ ሃይል የትህነግን ሽንፈት ተከትሎ ወደ ሱዳን ማቅናቱን የሚተቅሱ የአገርና የውጭ መገናኛዎች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ነን የሚሉ ተቋማት በውቅቱ ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ይህ የሰለጠነ ሃይል በወልቃይት በኩል ተደጋጋሚ ጥቃት መስንዘሩን መንግስት መረጃ ጠቅሶ ሲያስታውቅ፣ የአካብቢ ነዋሪዎች ምስክርነታቸውን የሰጡበት ተደጋጋሚ ጉዳይ እንደሆነ ተሚታውስ ነው። እኛም በውቅቱ ይህንኑ መዘገባችን አይዘነጋም።
“ይህ ጥቃት፤ ግድያ፣ ጉዳትና ውድመት፤ ጠቅላላ ድርጊቱና ውጤቱ ግፍና ጭካኔ የተሞላበት በበንጹሃን ላይ የተፈጸመ የጭፍጨፋ ወንጀል” ያለው ኮሚሽኑ፣ አይይዞም “ጭፍጨፋውን የፈጸሙት ቡድኖች ‘አማሮችና ወልቃይቴዎች’ ያሏቸውን ከቤት ቤት እየዞሩ ነው የገደሉዋቸው” ብሏል። ደብቀው የተረፏቸው የትግራይ ተወላጆች እንደነበሩም ምስክሮችን ጠቅሶ ጠቁሟል።
አምነስቲ ስለ ጭፍጨፋው ባወጣው ሪፖርቱ “በየቦታው ወድቀው የሚታዩና በአልጋ ላይ የሚታዩ አስከሬኖችን አሰቃቂ ፎቶ ግራፎችና ቪዲዮዎችን የተረጋገጡ” ብሏል። ኢንተር ፖልም በተመሳሳይ መረጃ አውጥቷል።
ጄነራል አልቡርሃን የሚመሩት የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር በማለፍ በተደጋጋሚ ንጹሃን ላይ ጥቃት መፈጸሙ፣ ንብረት ማውደሙንና መዝረፉን፣ የኢትዮጵያን ድንበር በሃይል መያዙን ለሚያውቁ ኢትዮጵያዊያን ትህነግ ከዚህ ሃይል ጋር ማበሩ ይፋ መሆኑ መነጋገሪያ ሆኗል።
የሰሙትን ሁሉ ዜና የሚያደርጉ፣ ያልሰሙትን ” ውስጥ አዋቂ ነገረን” የሚሉ ሚዲያዎች የፈጣን ሃዩን መግለጫ እንደወትሮው አላስተናገዱም። ይልቁኑም አቶ ጌታቸው ያወጡትን ማስተባበያ አጉልተዋል። በዚህ መሃል ላይ ነው ” ትህነግ ከየትኛው ፋኖ ጋር ነው የሚሰራው? ከጎንደር ወይስ ከጎጃም” የሚለው ጉምጉምታ ይፋ እየሆነ የመጣው።
ትህነግ ወልቃይትን ለማስመለስ ውጊያ ለመክፈት ዕቅድ እንዳለው የሚናገሩ ደጋፊዎቹ ከአማራ ፋኖ ጋር ህብረት እንደሚፈጠር በተደጋጋሚ ቢናገሩም፣ ከየትኛው አማራ ክፍል ጋር እንደሆነ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይፋ አላደረጉም ነበር።
አሁን ላይ ይፋ እንደሆነው ግን በውስን የጎጃም አካባቢ ታጣቂዎች ጋር ስምምነት አለ። ስምምነቱም ወልቃይትን ትህነግ መልሶ እንዲወስድ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጦ ይሁን በሌላ አግባብ የታወቀ ነገር የለም። ትህነግ ግን በወልቃይት ጉዳይ እንደማይደራደር፣ ወልቃይት የውጭ ግንኙነት ኮሪዶር ማግኛ መስመር በመሆኑ የህልውናና የትግራይ እንደ አገር መቀጠል ዋና ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ የጎጃም ፋኖ ይህን አስመልክቶ የያዘው አቋም ሰፊ ጥያቄ አስነስቷል።
አማራ ክልልም ሆነ አሁን ላይ ወልቃይትን የሚያስተዳድሩ አካላት “ዳግም ለባርነት አንደራደርም” በሚሉበት ሁኔታ ትህነግ ከጀነራል አልብሃር ሃር አብሮ እንደሚዋጋ ይፋ መሆኑ “የጥሪ ደወል ነው” በሚል በአካባቢው ያለውን ቁጥጥርና ዝግጅት ጥብቅ አድርጎታል።
እንደሚሰማው ከሆነ መንግስት በወልቃይት በኩል ከህዝብ ጋር የተሰናሰለ ዝግጅት ካደረገ ከርሟል። ከሱዳን በኩልም ሆነ ከትግራይ አቅጣጫ የሚጀመር ትንኮሳ ካለ መከላከያ እርምጃ እንዲወስድ አቅጣጫ ተቀምጧል። እውነታው ይህ በመሆኑ በውይይት ይለቅ የሚሉ አካላት ከትግራይም በኩል እንዳሉና የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቅያቸው ተመልሰው አካባቢው ቀድሞ ከውጥረት ነሳ እንዲሆን ፍላጎት ያላቸው ስላሉ ጦርነት ይነሳል የሚለውን ስጋት የሚያቀሉም አሉ። (ኢትዮ12)
Leave a Reply