
አቶ በላይነህ ክንዴንና የተለያዩ የአማራ ባለሃብቶችን ስም በመጥራት መስዋዕትነት እየተከፈለበት ያለውን ትግል ለማኮላሸት የምታደርጉትን እንቅስቃሴ ደርሰንበታል፤ መንግሥትም ሆነ መከላከያ ንብረታችሁን አይጠብቅም፤ ንብረታችሁን የሚጠብቀው ሕዝብ ነው፤ ብታርፉ ይሻላችኋል ሲሉ “በባንዳነት” ፈርጀው እርምጃ እንዲወሰድባቸው የሚጠቁም መረጃ ራሳቸውን ኢትዮ 360 ብለው የሚጠሩት ሰጡ። ይህንን የሰሙ ከዚህ በፊት በዚሁ ሚዲያ አቶ ግርማ የሺጥላ “half caste ሃፍ ካስት” ወይም ዲቃላ ወይም ቅልቅል በማለት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወሰድ አስቀድሞ ካሰራጩት መረጃ ጋር አመሳስለውታል። ምናልባትም መረጃው የደረሳቸው ባለሃብቶች ጉዳዩ በሕግ እንዲታይላቸው የሚያደርጉበት ሁኔታ ይኖራል ተብሏል።
ሙሉ መረጃውን ቪዲዮው ላይ ይመልከቱ።
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply