የቀድሞው ኢህአዴግ ካድሬዎች እና የህወሓት ጀነራሎች ሂሳብ አስተማሪው ኤርሚያስ ለገሰ ሆን ብሎ በቁጥር ሊጫወት ሞክሯል፡፡ አላማው ኢዜማ የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ሊያሸንፍ እንደማይችል አስመስሎ መሳል ነው፡፡ ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ሆኖበት ነው፡፡
የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም፡፡ ምናልባት እንዲገባው ከዚህ በፊት ከነበረው የተቃዋሚዎች ዕጩዎች ቁጥር በ11% እድገት አሳይተናል እንበለው ይሆን?? ምንም እንኳን [ለእንደዚ አይነቱ አውቆ አበድ መፍትሄው] ንቆ መተው ቢሆንም ያቀረበውን የተንኮል መረጃ እንደ እውነት ሊወስዱ የሚችሉ ቅኖችን ከስህተት ለማዳን ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁ፡፡
ምርጫ የሚደረገው በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ፦
አዲስ_አበባ – ለክልልም ሆነ ለተወካዮች ምክር ቤት ሙሉ ዕጩዎችን ያስመዘገበው ብቸኛው ፓርቲ ኢዜማ ብቻ ነው፡፡ (ከአብን እና ከመኢአድ ጋር በጋር ዕጩዎችን አቅርቦ በስሙ የሚወዳደሩት ባልደራስም ሆነ ገዢው ፓርቲ ሙሉ ዕጩዎችን አላቀረቡም!)
ደቡብ ክልል – በፌደራልም ሆነ በክልል ምክር ቤት በሁሉም ወንበሮች እንወዳደራለን።
አማራ ክልል – በፌደራልም ሆነ በክልል ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ እንወዳደራለን።
ጋምቤላ – ያለው የክልል ም/ቤት ወንበር 155 ነው በ114 የክልል ም/ቤት ተወዳዳሪ አቅርበናል የተቀሩት 41 ላይ በምዝገባ ችግር ስለተፈጠረብን ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ አቅርበናል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሙሉ በሙሉ እንወዳደራለን።
ሀረሪ – 36 ወንበር ነው ያለው – በአንደኛው ምርጫ ክልል ሙሉ 18 ዕጩዎች ያቀረብን ሲሆን በሌላኛው ምርጫ ክልል ለአደሬ ብሄረሰብ ብቻ የተተወውን 9 ወንበር ጨምረን ዕጩ አቅርበናል የጎደለን 4 የክልል ምክር ቤት ዕጩ ብቻ ነው፡፡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ለአደሬ ብሔረሰብ የተተወውን ወንበር ጭምር ዕጩ አቅርበንበታል፡፡
ሲዳማ – ካሉት 19 ወረዳዎች በ16ቱ አብላጫውን ዕጩዎች አቅርበናል በተቀሩት በ3ቱም ዕጩ ብናዘጋጅም በምርጫ ቦርድ ምክኒያት አልተመዘገቡም ቅሬታ ለምርጫ ቦርድ አስገብተናል።
አፋር – በተቃዋሚዎች ታሪክ ለመጀመሪያ ግዜ ለክልል ምክር ቤት 50 ሲደመር 1 ወንበር ማሸነፍ የሚያስችል ዕጩዎች አቅርበናል በሕዝብ ተወካዮ ምክር ቤትም አባላ ከምትባል ወረዳ እና በትግራይ ድንበር አካባቢ ካለ አንድ ወረዳ ውጪ በሁሉም ዕጩ አቅርበናል።
ቤኒሻንጉል_ጉምዝ – በፀጥጻ ችግር ምክኒያት በ4 ወረዳዎች ዕጩ ማቅረብ አልቻልንም በ5 ወረዳዎች የተወካዮ ምክር ቤት እና ከፊል የክልል ምክር ቤት ዕጩ አቅርበናል።
ኦሮሚያ – በሕዝብ ተወካዮችም ሆነ በክልል ምክር ቤት ዕጩዎችን ለማስመዝገብ ከፍተኛ ተግዳሮት ገጥሞናል ለምርጫ ቦርድ በዝርዝር ቅሬታ ያቀረብን በመሆኑ መልስ ስናገኝ ዝርዝሩን እመለስበታለሁ።
ሱማሌ – ለክልል ምክር ቤት ያቀረብናቸው ዕጩዎ 50 ሲደመር አንድ አይሞሉም ለፓርላማም ያቀረብናቸው 11 ዕጩዎን ብቻ ነው። (13 ቦታ ላይ ዕጩ አላቀረብንም)
በክልል ምክርቤት ብቻችንን የክልል መንግስት የመመስረት ዕድል የሌለን በኦሮሚያ፤ በሶማሌ እና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ብቻ ነው፡፡ እነሱንም የፀጥታው ችግር ሲስተካከል አሻሽለን በሚቀጥለው አናሻሽላለን፡፡
ሰውን ተስፋ አስቆርጦ በምርጫው ተስፋ እንዲቆርጥ ለማድረግ ያደረከው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም፡፡ ከቻልክ ከቻልክ የራስህን ፓርቲ ለማጠንከር ሞክር፤ የእኛን ለኛ ተውልን፡፡
ኢዜማ የተስፈኞች ቤት ነው፡፡ እንኳን ባንተ አይነቱ ከሩቅ ተኳሽ አጠገባችን ባሉት ገዳዮቻችን እንኳን ተስፋ አንቆርጥም፡፡
ኢዮብ መሳፍንት፤ የኢዜማ ዓለም አቀፍ አባላት ተጠሪና የሕግ ባለሙያ
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
ነፃ ሕዝብ says
ኢዮብ መሳፍንት ፦ ድንቄም ሶሻሊዝም ነበር ያሉት እማማ ዝናሽ ! ኢዜማ የተረኞቹ ፋሽስቶችና አፓርታይዳዊ አገዛዝ ኦሮሙማው ምርኩዝ ወይም የነዳያን ስብስብ ፓርቲ ነው ፥ ኢዜማ በአማራ ሕዝብ ጥላቻ የሰከረና መድረሻውም ሆነ መነሻው አማራ ጠል መሆኑን በሰሞኑ “አማራ መጣልህ” ቅስቀሳ በግልፅ አሳይቶዋል ፥ ኢዜማ ከዘመነኞቹ ደናቁርት ኦሮሙማዎች አስተሳሰብ ያልተለየ ድሁር መሆኑን እየተመለከትን ነው ፥ ሌላው የኢዜማ ዓለም አቀፍ አባላት ተጠሪና የሕግ ባለሙያ ነኝ ብሎ ወደ ነገረን ኢዮብ መሳፍንት ሳመራ የቀድሞው ኢህአዴግ ካድሬዎች እና የህወሓት ጀነራሎች ሂሳብ አስተማሪው ኤርምያስ ለገሰ እያልክ ለመሸርደድ የሞከርከው የቅሽምናህን ጥግ ያመለክታል ፥ ሂሳብ ማስተማር የሚቻለው እውቀት ሲኖር ብቻ ነው ፥ ኤርምያስ የሚናገረው እውነትና ተአማኝነት ያለው ነው ፥ ኢዜማዎች ፋሽስቱና ነፍሰ_ገዳዩ አብይ አህመድ አሊ የሚጠላውን ሰው እናንተም በኢዜማ አመካኝታችሁ የጥላቻ ድሪቶ ለመደረት ትሞክራላችሁ ፥ አየህ ጌታው ጎባጣ ከሆነ አሽከሩም ጌታውን ለመምሰል ጎባጣ ሆኖ ለመሄድ ይሞክራል ይባላል ፥ ፋሽስቱና አፓርታይዳዊ አገዛዝ ኦሮሙማው በፀረ_አማራነት የቆመበትን ዕኩይ ዓላማ ኢዜማ እንደ አስፈፃሚ ሆኖ አዲስ አበባ ላይ “አማራ መጣልህ” እያለ ቅስቀሳውን መጀመሩ የኦሮሙማውን ድኩማን አስተሳሰብ ተጋሪ ሆኖዋል ፥ ስለዚህ ኤርምያስ የመሰለውንና የታዘበውን በሚዲያው ለማለት ሞክሮዋል ፥ ኦሮሙማውን ወይም አብይን መስሎ በጥላቻ ታጭቆ መልስ መስጠትና ያልተፃፈ ማንበብ አስፈላጊም አይመስለኝም ፥ እኔ በግሌ ኢዜማ የብል*ግና ሌላኛው ክንፍ አድርጌ የምቆጥረው ፥ ነፍሰ_ገዳዩና አስገዳዩ አብይ ሲያስነጥሰው ኢዜማ ማሃረብ አቅራቢ እንጂ ተቃዋሚ ፓርቲ ተብሎ ሊጠራ አይገባውም ፥ ለዚህም ማሳያው በተከታታይ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደረገውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተቃውሞ አንድም ጊዜ መግለጫ ሲያወጣ አላየሁም ፥ አልሰማሁም ፥ ኢዜማ አ/አበባ ላይ አማራ መጣልህ ፥ ባህርዳር ላይ ግን አማራ ጀግና እያሉ መቀሳፈት ለውርደት ይዳርጋል ፡፡
Mr Frank Talk says
This guy doesn’t seem to know what he is talking g about. He is simply bent on using all the hateful words and phrases and tarnish the images of our PM and our beloved country. He must be one of the Juntas running for their lives or Egyptian agents wanting to destroy Ethiopia.
TVPDF says
የፓለቲካ ዝሙት ገና ብዙ ዋጋ ያስከፍለዋል። ይልቅስ ለእርሱ የሚያዋጣው ከፓለቲካ ርቆ ንስሓ ገብቶ አንድ የእርዳታ ሰጪ ድርጅት መስርቶ ችግረኛ ቢረዳ ይሻለዋል። ከሕዝብ ወጥቶ ሕዝብን ማምታታት ነውር ነው።
TVPDF
George says
ምንድር ነዉ ነገሩ? ዋና ቁምነገሩ ላይ ከማተኮር ይልቅ ፤ሙያዉንና በአንድ ወቅት የተሰማራበትን ሥራ እንደወንጀል ተቆጥሮ በግለሰቡ ዙሪያ ማተኮር የሀሳብ ድህነት በገጠማቸዉ ተሞአጉዋቾች የሚከወን ልክስክስ ተግባር ነዉ፡፡
ከሁሉ በላይ የሚደንቀዉ ደግሞ “የኢዜማ ዓለም አቀፍ አባላት ተጠሪና የሕግ ባለሙያ” ነኝ በሚል ግለሰብ መፈጸሙ ነዉ፡፡
ግለሰቡ ተሸከምኩት ከሚለዉ ሀላፊነትና ሙያ ለተመለከተዉ ሁሉ የገዘፈ ቢሆንም ግለሰቡ የሰጠዉ አስተያት ግን ፤ምን ነካዉ የሚያሰኝ ድርጊት ነዉ፡፡ በመሆኑም፤ኤርምያስ ለገሠ ማንም ጠበቃ ሳያስፈልገዉ ኢዮብ መሳፍንት በፈጸመዉ በዚህ ልክስክስ ተግባር ከበቂ በላይ ምላሽ መስጠት እንደሚችል ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚገነዘብ ቢሆንም ፤እንደተመልካች ዝም ብሎ ማለፍ ተገቢ ባለመሆኑ የተወሰኑ ነገሮችን ለማለት ተገደድሁ፡፡ ኢዮብ መሳፍንት ለምን እንዲህ አለ ? ለሚለዉ ጥያቄ ብዙ መልስ የሚሆኑ ሀሳቦችን መሰንዘር ቢቻልም፤ ዋናዉ ግን በኢዜማ በኩል “አለሁ የእናንተ ጠበቃ ” በማለት ሙገ ሳን ለማግኘት የአድርባዮች ዓይነተኛ ጠባይ ነዉ፡፡
ኤርምያስ ለገሠ ከኢሕአደግ ጋር በነበረበት ወቅት የሰራዉን ሁሉ አንድ በአንድ ዘርዝሮ ይቅርታ ጠይቆአል፡፡አሁን ምን ይጠበስ ተብሎ ነዉ በመደጋጋም መነሳቱ፡፡ የብልጽግና አባላትና የመንግስት አመራሮች ሁሉም ከኢሕአደግ የመጡ ናቸዉ፡፡በአንድ ወቅት ጠ/ሚኒስትሩ በአጋጣሚ ቅርታ ለማለታቸዉ በስተቀር ፤ ደንቡን በጠበቀ መልኩ /formal procedure/ ይቅርታ አልጠየቁም፡፡እናወዳደር ካልን፤ ኤርምያስ ለገሠ ከፈጸመዉ ጉዳት ይልቅ ጠ/ሚኒስትሩ የኢንሳ መሪ ሆነዉ በስለላ የፈጸሙት ወንጀል በጣም ያመዝናል፡፡ሌላም ማለት ቢቻልም ልተወዉ፡፡
እስከዛሬ ኢዜማ ከፈጸመዉ ክህደት ሁሉ ገዝፎ የወጣዉ ደግሞ በቅርቡ ያስተዋወቀዉ “አማራ መጣልህ” የሚለዉ በተስፋ መቁረጥ የተፈጸመ ክህደትና ወንጀል ነዉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ድርጊቱ ኢዜማን ከድጡ ወደማጡ ከመክተቱ በስተቀር ምንም የሚያስገኝለት ፓለቲካዊ ትርፍ አይኖርም፡
ሌሎች የጎሳ ፓርቲዎች አሊያም ጽንፈኞች ቢሉት ባልደነቀን፤ የተለመደ ነዉና ፡፡
እንደ ንጉሡ አጎንብሱ ሆነና በኢዜማ ተፈጽሞአል፡፡ በኢዘማ መባሉ ግን፤ እጹብ ድንቅ ሆኖብናል፤መጨረሻዉንም አሳዉቆናል፡፡ አሁንም፤ጊዜዉ አልረፈደምና ቢታረም መልካም ነዉ፡፡
Mr Frank Talk says
This is written by Ermias himself. I can see his style and language in this ‘reply’.
chacha says
ወይኔ ግዜዬ ይኼን ጽሁፍ ብዬ ማንበቤ ይህን ውዳቂ ጽሁፍ በማንበቤ የበለጠ ኢዜማን እንድጠላው ነው ያደረከኝ ። ኤርሚ ሁሌም ጀግና ነው ። አአ ውስጥ ኢዜማና ህወሀት ቢወዳደሩ እንኳን ቁዘማ አንድ ወንበር አያገኝም ። ቁዘማ አአ የካደ ከሀዲ ነው