• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ

July 2, 2020 10:34 pm by Editor 5 Comments

ከኢሣት ከተባረሩ/ፈቃዳቸው ከመልቀቁ በኋላ “ኢትዮ 360” የሚል የቱቦ (የዩትዩብ) ቲቪ የተከፈተው “ሚዲያ” የወያኔ መሆኑ ተረጋገጠ። በኢትዮጵያ ለውጥ ከተካሄደ በኋላ በርቀት የተመኙት የውሃ ሽታ ሆኖ ሲቀርባቸው በዶ/ር ዐቢይ ላይ ፍጹም ጭፍን የሆነ የጥላቻ ዘገባ በመሥራት ከህወሃት በላይ አገር በማፍረስ ተግባር ተጠምደው የነበሩት ቀዳሚው አገልግሎታቸው ለህወሃት እንደነበር አብሯቸው ሲሠራ የነበረው አጋልጧል። (ጎልጉልም ይደርሰው ከነበረው መረጃ በመነሳት ሚዲያው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከተነሱ ኃይሎች እና ከጽንፈኛ ቡድኖች የቀጥታና ተዘዋዋሪ የጥቅም ተካፋይ እንደሆነ መዘገቡ አይዘነጋም)  

ሁለቱ የህወሓት አገልጋይ የነበሩት ኤርምያስና ሃብታሙ ከኢሣት አፈንግጠው ከወጡ በኋላ በኢትዮ 360 እስካሁን ያላቋረጠ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በዶ/ር ዐቢይ ላይ እንደከፈቱ ነው። ሃብታሙ ከህወሃት አገልጋይነቱ ወደ ተቃዋሚው ጎራ ከገባ በኋላ ወያኔ መልሶ ለመጥቀስ የሚከብድ የአካል ጉዳት ካደረሰበት በኋላ ወደ ትፋቱ መመለሱ የብዙዎች ጥያቄ እንደሆነ ነው። ከሃብታሙ በተጨማሪ በአንድ የዜና ዘገባ የጋዜጠኛነት ማዕረግ ተጎናጽፋ “ጀግና” ለመባል የበቃችው ርዕዮት እንዲሁ በህወሓት ሎሌነት፣ በዐቢይ ጥላቻ መዘፈቋ ሌላ ግራ የሚያጋባ ጉዳይ ነው።   

በረከት ስምዖን ጠፍጥፎ የሠራው ኤርምያስ አሁንም ታማኝነቱን በዚያው መስመር መቀጠሉ የሚገርም ባይሆንም ከዚህ በፊት በተሰራጨ ጽሁፍ እንዲህ የተባለለት ነው። “በሕይወት በነበረበት ጊዜ ኢትዮጵያን ጠርንፎ የነበረውን ኢህአዴግን እንዲያገለግሉ የሚመለመሉ በርካታ ወዶገብ ጥቅመኞች ነበሩ። በአንድ ወቅት ተስፈኛ ካድሬዎችን ለመመልመል ሲኒየሮቹ ካድሬዎች በሄዱበት ክፍለከተማ ከተሰበሰቡት መካከል አንዱ ኤርሚያስ ለገሰ ነበር። በወቅቱ አብሮት የነበረ የቅርብ ወዳጄ እንደሚለው ከሆነ “ደርግን ገረሰስን” የሚሉት ተጋዳላዮች በወቅቱ ደረሰብን በማለት ከመድረኩ ሲያወሩ ኤርሚያስ ከሥር ሆኖ በአራት መዓዘን ያለቅስ ነበር። አገር ለመገንጠል የተነሱት የወንበዴዎች ክምችት “ቁርጠኝነታቸው፣ በቦምብ ላይ መረማመዳቸው፣ አንዱ ለሌላው ልሙት ማለቱ፣…” ነበር ኤርሚያስን ተንሰቅስቆ ያስለቀሰው፤ ይህንኑ ቃል በሌላ ጊዜ ደግሞታል። ይህንን እንስፍስፍ እጩ ካድሬ ማንነት የጠየቁ መልማዮች ወዲያውኑ በብርሃን ፍጥነት ኤርሚያስን ከክፍለከተማ አስፈነጠሩትና መድረሻውን አሁን በእስር ላይ የሚገኘው በረከት ስምዖን መ/ቤት አደረሱት”። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)

ከኢትዮ 360 አብሮ ከሠራ በኋላ ለቅቄአለሁ የሚለው ምናላቸው ስማቸው ከተናገረውና የተጨመቀው ከዚህ በታች ቀርቧል።

  • 360 የሚባለው የሚዲያ ፕሮግራም በቀጥታ ከሀገር ደህንነት ስጋት ከሆኑና ለጥፋት ከተሳሰሩ ሰዎች ጋር ውሎ ማደር ሲጀምር በቃኝ አልኩ።
  • ስንጀምር በሙሉ የራስ አቅም ለመንቀሳቀስ ነበር፣ ሆኖም በተደጋጋሚ ኤርሚያስ ከህወሃት ጋር እየተገናኘ ሲመጣ መጠራጠር ጀመርኩ።
  • እኔ ምናላቸው ለራሴ ክብር ያለኝ ነኝ፤ ህወሃትን የገንዘብ ምንጭ አድርጌ ምንም ሥራ መስራት አልፈልግም። ሃብታሙ በአንድ ስብሰባ ከማንም ገንዘብ ካገኘን እንወስዳለን ሲል ደነገጥኩ። ያን ቀን የእኔ 360 ቆይታዬ አበቃ አልኩ።
  • የህወሃት ዋነኛ አቋም ግብፅን መደገፍንም እንደሚጨምር በማስረጃ አውቀን፤ በውስጥ የደረሱን መረጃዎች ብዙ ነገሮችን ቢያሳዩንም ከሁለቱም የማልጠብቀውን ጉዳይ ሲያበረታቱ በተለይ ርዕዮትና ኤርሚያስ ውስጤን ሰበሩት።
  • ርዕዮት በተለይ የወያኔ ቁስሏ እንዳልደረቀ ትናገራለች፤ ሆኖም ዶክተር ዐቢይን የሚጎዳ ከሆነ ከህወሃት ተላላኪው አሉላ የመጣን ዕርዳታ ለመቀበል ዓይኗን አላሸችም። ይህ ጤነኛ ጉዳይ አይደለም።
  • የሆነ ጊዜ የኢሳቱ ሲሳይ አጌና የህወሃት አሜሪካ ክንፍ ሚዲያ ስለማቋቋም እንዳሰበና ከፍተኛ ገንዘብ በታዋቂነት ደረጃ ላሉ ሰዎችም ለማደል እንደተዘጋጁ ሲናገር ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር። አሁን በቀጥታ ለ360 ማኔጅመንት እየተባለ የሚጎርፈው ገንዘብ ምንጭ ላይ ማንም በእኛ ውስጥ መነጋገር አይፈልግም። 360 የዶክተር አብይ ተቃውሞን በከበሮ የሚያደምቅ ወያኔ ስፖንሰር የምታደርገው የአማርኛ ተናጋሪ ሚዲያ ነው።
  • የግብፅ ጉዳይ ላይ በጋራ ዶክተር አብይን እናጥቃው በማለት አብረው ሊሰሩ የማይችሉ ፅንፈኞችና እርስ በእርስ ለመጠፋፋት የሚፈላለጉ ቡድናት ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ሳይ ከበደኝ፤ ትንሽም ቢሆን ህሊና ያለኝ ሰው ነኝ ከሀገሬ ጥቅም ጋር አልደራደርም ብዬ ወጣሁ።
  • የገንዘብ ምንጮቻችን በአብዛኛው ከቀድሞ የህወሃት ቡድን ነው። ይህንን ምንም ሳልጠራጠር እናገራለሁ ብሏል ምናላቸው ስማቸው።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Politics, Right Column

Reader Interactions

Comments

  1. ነፃ ሕዝብ says

    July 4, 2020 12:22 am at 12:22 am

    golgul ድህረ-ገጽ አዘጋጆች በእጅጉ የምታስዝኑና የምትከረፉ ሆናችሁዋል ፥ እንዴት ሆኖ ነው ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ ሆኖዋል የምትሉት ? ከመንግሥት ጋር ተለጥፋችሁ የመንግሥት ተቃዋሚ የሆነን ሚዲያ ብትወነጅሉ ምን ያስደንቃል ! የወሬ ማባያ ይዛችሁ አትዝፈኑ ! ምናላቸው እንደዚህ ብሏል ብላችሁ ፍጹም ውሸት በሆነና ባልተጨበጠ ነገር አትዋሹ ! ውሸት ቅሌት ነው ! ምናላቸው ከኢትዮ 360 ያፈነገጠበት ምክንያት ወደፊት በግልጽ ይገለፃል ፥ ያገሬ ሰው “ትንሽ ቆሎ ይዘህ ወደ አሻሮ ተጠጋ ይላል ” እንደ ጎልጉል ድህረ-ገጽ ዓይነት ማለት ነው ፥ እናንተ ጎልጉሎች ደጋፊዎች እንደሆናችሁ ሁሉ ኢትዮ 360 ሚዲያም የመንግሥት ተቃዋሚ ነው ፥ መደገፍ እንዳለ ሁሉ መቃወምም አለ ! ጎልጉሎች በግልሰቦች ላይ ያላችሁ አመለካከት ፍጹም የተሳሳተና የወረደ ነው ኤርምያስ ለገሰ እንደማንኛውም ሰው በሥርዓቱ ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ አገልግሎ በመጨርሻም አራግፎዋቸው ወጥቶዋል ፥ እናንተ በኤርምያስ ለገሰ ላይ ያላችሁ ፍጹም የተሳሳተ አመለካከት ከመንግሥት ጋር መወገናችሁን በግልጽ ያሳያል ፥ ምክንያት እርሱ መንግሥታችሁን ሲቃወም እናንተ ደግሞ የእርሱን ስም ማጥፋት የዘወትር ተግባራችሁ ነው ፥ በሥርዓቱ ውስጥ እስካሁን ያለና እየዘረፈ ያለውን ህወሃት-ኦነግ ወንጀለኞች ስታጋልጡ አትታዩም ፥ ነገር ግን ከመንግሥት ጋር ያልወገነውንና የሚቃወመወን የስም ማጥፋት ዘመቻ የምታካሂዱበት የእናንተን አፋሽ አጎንባሽነት ያሳብቅባችሁዋል ፥ ለማንኛውም ጎልጉል እውነቱን እያጋለጠች የሕዝብ ዐይንና ጆሮ ሆና በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅና ተፈቃሪ እንድትሆን መሥራት ይኖርባችሁዋል ፥ ፍጹም ሚዛናዊ ሁኑ ፥ መንግሥትን መደገፍ ሳይሆን እውነታውን በማውጣት ለሕዝብ መረጃ መስጠት ነው ፥ እስኪ ያለ ምንም ዓይነት ጥፋት ተዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሲታሰር መንግሥትን ተቃወሙ ፥ እውነቱን ተናገሩ ፥ መንግሥት እየሄደበት ያለው መንገድ ስህተት መሆኑን ፃፉ ፥ ኢትዮ 360 ሚዲያ ወያኔ ነው ፥ ቀለብ ይሰፈርለታል … ውሸትና ያልተጨበጠ የወሬ ጋጋታ ትርፉ መዝቀጥ ነው ።

    Reply
    • Tadesse says

      July 7, 2020 10:28 am at 10:28 am

      I don’t read them,Ethiopiawi charater yelewm

      Reply
  2. Spectator says

    July 5, 2020 09:05 pm at 9:05 pm

    I don’t see any hard evidence other than hearsay and accusations. Let Minalachew speak and provide irrefutable evidence. You get off from your high horses and stick to the journalism than being a mouth piece of others and your wishful thinking.

    Reply
  3. yilmab says

    July 6, 2020 06:42 am at 6:42 am

    Dear Editor, do you really think it is such a good idea to accuse an organization or individual in such manner without presenting a single piece of evidence? You are entitled to your opinion but leveling such an accusation deserve to be accompanied with evidence so the reader can weigh the facts and make a determination. It is distressful to see you using your media to trample on the right of others and spread unfounded theories and opinions as fact. It will take away credibility from your journal and make all what you write suspect. I do not follow the media in question on a regular manner but I very much doubt all those folks that work in the organization could be associated with Woyane and any such accusation should be substantiated. Your charges are very grave and all I can say is you better have the evidence or a very good attorney, you have left yourself open to defamation and other charges.
    .

    Reply
  4. Zemen says

    July 6, 2020 03:37 pm at 3:37 pm

    ይሄ ድረ ገፅ በቀጥታ በአብይ አህመድ ተደጉሞ የሚንቀሳቀስ የኦሮሙማ ክንፍ እንደሆነ ኢትዮ 360ን በመተቸት ፀረ ኢትዮጵያ መሆኑን በሚገባ ያረጋገጠ የዘመኑ ሆድ አደር ቅጥረኞች እንደሆነ አለ ጥርጥር ያስመሰከረ የባንዶች ተረት ተረት የሚዘከርበት ደጀ ሰላም እንደሆነ የሚጠራጠር ካለ በውነት የአድር ባይ ካድሬዎችን አካሄድና አረማመድ ያልተረዳ መሆን አለበት ። ጎልጉል በውነት አይና አንጀታችሁ ይጎልጎል ከንቱዎች ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule