• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል

May 27, 2022 02:51 am by Editor Leave a Comment

ራሱን ኢትዮ 360 ብሎ ስለሚጠራው ቡድን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በመረጃ ማንነቱን እና ለማን እንደሚሠራ አጋልጠናል። የትህነግ ተከፋይ ቡድን መሆኑን ከሁለት ዓመት በፊት በማስረጃ ተናግረናል። ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች ይመልከቱ።

“ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳ

የበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው

የ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”

ኢትዮ 360 በገንዘብ ችግር ታንቄያለሁ፤ ራሴን ግምግሚያለሁና ዕርዱኝ አለ

ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ

በዚህ ቡድን ውስጥ ያሉት ግለሰቦች ሲሻቸው መንፈሣዊ ሆነው በመቅረብ የሰውን ቀልብ ለመሳብ ይሞክራሉ። ሃብታሙ አያሌው አንዱ ተጠቃሽ ሲሆን ዘመድኩን በቀለ የተባለው ተባባሪያቸው እንዲሁ በፈጣሪ ስም አማትቦ፣ መስቀሉን አንገቱ ላይ አንጠልጥሎ ከአፉ የሚወጣው ስድብ፣ በራሱ ማኅበራዊ ሚዲያ የሚተፋው ብልግና የፈጣሪን መኖር የማይቀበል ሰው እንኳ የማይለው ነው። እዚህ ላይ የእርሱን ጸያፍ ንግግር መድገም ራስን ማዋረድ ነው። ዘመድኩንም ሆነ ሃብታሙ የሚያመሳስላቸው የሃይማኖት ካባ የተከናነቡ መሆናቸው ነው። ከዚሁ ጋር ብሩክ ይባስም አብሮ ይመደባል። የሃይማኖት ጭምብል የለበሰ ሌላው የውሸት ቋት ነው – ቪዲዮው ይመሰክራል።

እነዚህ ግለሰቦች ሰዎችን ለማታለል በሚመቹ ቃላት መደለል ይችላሉ። “እኛ የምንናገረው እውነትንና እውነትን ብቻ ነው” ይላሉ፤ ለዚህም ይምላሉ፣ ይገዘታሉ፣ ያማትባሉ። ዘመድኩን “ነጭ ነጯን” ነው በማለት ከወደ አውሮጳ በየቀኑ በፈጣሪ ስም የሃሰት ምላሱን ይዘረጋል። የኤርምያስ ከሁሉ የተለየ ነው። ከበረከት የተማረውን መስመር በመስመር ነው የሚተገብረው። በስሙ የከፈተው ዩትዩብ እስካለው ድረስ ባለማተቦቹን በመጠቀም ዓላማውን ማሳካት የተካነበት ነው።

ዝርዝሩን እዚህ ላይ መናገር ባያስፈልግም ሁሉም ትዳር መሥርተናል ይላሉ፣ ልጆች አሏቸው፣ ስክሪን ፊት ቀርበው ግን እጅግ የሚሰቀጥጥ ውሸት ሲያወሩ የዘሩትን እንደሚያጭዱ ለጊዜው የዘነጉት ይመስላሉ። የትዳር ጓደኞቻቸውም “ተው፣ እንዲህ አታውራ፣ …” ወይም በገሃድ ሲሳሳቱ “ይቅርታ ጠይቅ” አይሏቸውም። የኤርምያስ እንኳን ሃይ ባይ ያለው አይመስልም። አንድ ነው ያለው፤ እሱም እስር ቤት እየማቀቀ ነው።

ስለ ባለከዘራው ጄኔራል ሻምበል በየነ እና ጄኔራል መካሻው ጀምበሬ የዋሹት ግልጽና አሳፋሪ ውሸት ምንም አያሳስባቸውም። ባከዘራው ስለ እነርሱ በገሃድ የተናገሩት ተቀባይነት የሌለው ብቻ ሳይሆን የዐቢይ አለቅላቂ ሆነው ነው ተብለው የሰሞኑ አጀንዳ ይደረጋሉ። ጄኔራል አበባው ላይ የጀመሩት የስድብና የማጠልሸት ዘመቻ በባለከዘራውም ላይ ሰሞኑን ይቀጥላል። ከዚህ ሌላ እነዚህ ኅሊናቢሶች “ስህተት ፈጽመናል፣ ይቅርታ እንጠይቃለን” የሚሉበት ምንም የሞራል ልዕልና የላቸውም።

እነዚህ የኢትዮጵያ እንግዴ ልጆች እስከሚከስሙ ይንንኑ ትፋታቸውን በየቀኑ መቀጠላቸው አይቀርም። እጅግ የሚያሳዝነው ግን ይህንን ሁሉ ቅጥፈት እያዩ ምንም ሳይሰማቸው በገንዘባቸው እነርሱን የሚደግፉት ናቸው። ከሁሉ በላይ ዓላማውና ግቡ ምንም ግልጽ ያልሆነው የመረጃ ቲቪ ባለቤቶች ነው። ባንድ በኩል አገር ወዳድ መስለው በየመድረኩ ይታያሉ በሌላ ደግሞ እንደዚህ ዓይነት እጅግ የዘቀጠ ፕሮግራም በሳተላይት ቲቪያቸው በኩል ያስተላልፋሉ። ፍርድ ከፈጣሪ ለሁሉም በጊዜው ይደርሳል።

ከዚህ ሌላ በአማራ ሕዝብ አንቂነታቸው የታወቁና በጦርነቱ እስከ ግንባር ድረስ ሄደው ሲዋጉ የነበሩና አሁንም ሕዝባቸውን እያገለገሉ ያሉ በዚህ ራሱን ኢትዮ 360 ብሎ የሚጠራ የወረበላ ቡድንና በተባባሪዎቹ በየቀኑ ከስድብ ያለፈ ዛቻም እየቀረበባቸው ነው። የ360 ደጋፊና ተባባሪዎች ጌታቸው ሽፈራው፣ ቶማስ ጀጃው፣ ሙሉዓለም ገብረመድኅን፣ አምደማርያም ዕዝራ፣ ወዘተ በተገኙበት እንዲገደሉ በማስባል በየማኅበራዊ ሚዲያ እየለፈፉ ይገኛሉ።

ቶማስ ጀጃው በዚህ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያው የጻፈው ጉዳዩን በጥሩ ሁኔታ የገለጸው ነው።

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ለራሱ ፍፁም ክብር የሌለው ምን ያህል ነውረኛ እንደሆነ ለማሳየት ነበር አብን የዘጋውን የሐሳብ መስጫ እኔ ከፍቼ የስድብ ሜኑው ተገልጦ እንዲታይ ያደረግኩት። እንደተለመደው ጋጠወጦቹ ፌስቡክ ስለሆነ ያሻቸውን ስድብ ነውረኝነት ለመግለፅ ችለዋል።

በነገራችን ላይ በፌስቡክ ከሚሳደበውና ከሚዝተው ውስጥ አንድም ሰው መሬት ላይ ፌስቡክ ላይ ያለው አቋም መድገም አይችልም። ከፌስቡክ ጀግኖችና ተሳዳቢዎች መካከል መሬት ላይ ፊት ለፊት ወይም መንገድ ላይ እንዳጋጣሚ ብታገኛቸው ቀድመው ራሳቸውን ለመደበቅ የሚጥሩ ናቸው። አንተ ሳታውቃቸው በፌስቡክ ስራቸው።

ፌስቡክ ላይ ከሚያሽላላው ውስጥ መሬት ላይ አንድም ደፋር ጀግና አታገኝም። ሲጀመር ጀግና አይዝትም። ባገኘው ሚዲያ ሁሉ አይለፈልፍም። ጀግና የማድረግ አቅም ያለው ስለሆነ ጀግንነቱን የሚገልጸው በተግባር ነው። ላደርግ ነው ብሎ ሳይሆን አድርጎ ነው ስራዬ ምስክር ይሁን የሚለው።

ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ፌስቡክ ላይ እንዴት ቶማስ ላይ እርምጃ የሚወስድ አንድ ሰው ይጠፋል ይላል እንጅ ራሱ እርምጃ ለውሰድ አይሞከርም ቀርቶ ሊያስበው የማይችል የቦቅቧቃ ጥርቅም ነው።

የአየር ላይ ወከባውን ያዬ ሰው ግን አቤት በቀጣዩ ቀን በሕይወት ስለመኖሩ ብቻ ሳይሆን አስከሬኑ ስለመገኘቱ ሁሉ እስከመጠራጠር ይደርሳል። ወያኔያዊ የአማራ ብሔርተኛ ምኞት እንጅ የማድረግ አቅም የለውም። የማድረግ አቅሙ በሌሎች ትክሻ ላይ የተንጠለጠለ ነው። ዘወትር ሌሎች ያደርጉለት ዘንድ የሚወተውት እንጅ በራሱ አንድ ኢንች የሚራመድ አይደለም። ይህ ባይሆን እንደምኞቱማ እስካሁን በስንት ሰው ላይ እርምጃ መውሰድ በቻለ ነበር። ጠጋ ብሎ ነገር ከመለኮስ ሐሜት ከማመላለስ ያለፈ ፈፅሞ አቅም የሌለውና መቼምም የማይኖረው የቡታ ሰዳጅነት ሚና ብቻ ያለው ስብስብ ነው። (ቶማስ ጀጃው)

ኢቲቪ በባለከዘራውና በሥራ ባልደረባቸው ላይ የሠራውን አጠር ያለ ዘጋቢ ፊልም በመመልከት ራሳችንን ከእንግዴ ልጆች የስንፍና ንግግር እንጠብቅ።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Opinions, Politics Tagged With: Ethio 360, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule