• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢትዮ 360 በገንዘብ ችግር ታንቄያለሁ፤ ራሴን ግምግሚያለሁና ዕርዱኝ አለ

July 4, 2020 11:40 pm by Editor 6 Comments

ከየአቅጣጫው ከተለያዩ ምንጮች ገንዘብ እንደሚለገሰውና የውክልና ፕሮፓጋንዳ እንደሚሠራ ይፋ የተደረገበት ኢትዮ 360 ሚዲያ ይህንኑ ለማስተባበል የገንዘብ ችግር አንቆናል፤ ዋናው ችግሬ ብር ነው እርዱኝ ሲል ባወጣው መግለጫ የልመና ድምጹን አሰማ። በተለይ ከቅርብ ጊዜ በኋላ በውስጥ በተከሰተ መከፋፈል ምክንያት የተለያዩ ምሥጢሮች እየወጡበት የተቸገረው ኢትዮ 360 አሁን ካለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ራሱን መገምገሙን በመግለጫው ጠቁሟል።

ቅዳሜ ዕለት መግለጫው እንደወጣ በዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ (በተለምዶ ዲኤምቪ በሚባለው) የተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ያነጋገረችው የጎልጉል መረጃ አቀባይ እንዳለችው መግለጫው ሌላ ገንዘብ የመሰብሰቢያ ስልት ነው በማት አስተያየት ሰጪዎች መናገራቸውን ገልጻለች።

“ሁሉንም እኮ እናውቃቸዋለን፤ ኮትና ከረባት አሳምረው ሲታዩ ትልልቅ ሰዎች ይመስላሉ እንጂ እዚህኮ በየቀኑ ስንጋፋ ነው የምንውለው፤ አዋዋላቸውንም ሆነ ማንነታቸውን አሳምረን እናውቃለን፤ ዐቢይን በመቃወም ገንዘብ መሰብሰብ ነው የሚፈልጉት፤ አሁን ደግሞ ሁኔታው ስላልተመቻቸው ወያኔ ተሃድሶ፣ ጥልቅ ተሃድሶ ምናምን እያለ ሲቀልድብን እንደነበር እነሱም በዚያው መልክ ሊያምታቱን እና ገንዘብ ሊሰበስቡ ነው የሚፈልጉት፤ እኔ አላዋጣም ግን እሰማቸዋለሁ፤ እና ሳስበው የአምባሳደር ፍጹም መግለጫም ያሳሰባቸውና ያስፈራቸው ይመስላል፤ ከመግለጫው በኋላ የተናገሩትና በፌስቡካቸው የለጠፉትን ስከታተል ዙሩ የከረረባቸው መሆኑን የተረዱ ይመስለኛል፤ በዚህ ላይ ደግሞ ከወያኔ ገንዘብ ይቀበላሉ ምናምን እየተባለ የሚነገረው አለ፤ እነ ዶ/ር ዐቢይ ደግሞ ተኳሹንም አስተኳሹንም ነው የምንመታው ስላሉ ስፖንሰር አድራጊዎቻቸው ሲመቱ ምንጩ ስለሚደርቅባቸው ቶሎ ብለው ወደ ሕዝብ ለመሽሸግ የፈለጉ ይመስለኛል፤ ያው ሁሉም ነገር ያገር ጉዳይ ምናምን ሳይሆን የጥቅም፣ የገንዘብ ጉዳይ ነው” በማለት አስተያየት የሰጠው በታክሲ ሥራ የተሰማራ መካከለኛ ዕድሜ ላይ የሚገኝ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ነው።

“ኑሮን ከብልሃቱ ለማሳካት በትርፍ ጊዜ ኡበር እነዳለሁ” ያለው ሌላው አስተያየት ሰጪ ስለ መግለጫው ሲጠየቅ እያነበበ ከነበረው አነስተኛ መጽሐፍ ራሱን በማገት “በግዕዙ ወይኩን ፈቃድከ ይላል፤ አቡነ ዘበሰማት ጸሎት ላይ ነው እንዲህ የሚል፤ ፈቃድህ ይሁን ማለት ነው፤ እኔም የምለው እንደፈቃዳቸው ይሁንላቸው ነው” በማለት መልስ ሰጥቷል።

“ኢትዮ 360 ውስጥ የሚሠሩት በጣም የማከብራቸው ጋዜጠኞች ያሉበት ሚዲያ ነው፤ ብዙ የታገሉ ናቸው፤ እነ ዐቢይን በመታገል የሚያደርጉትን እደግፋለሁ፤ ሊደገፉ ገባቸዋል፤ መስዋዕትነት እየከፈሉ ለእኛ ነጻነት የሚታገሉ ናቸው፤ መግለጫው ጥሩ ግምገማ እንዳደረጉና እንደታደሱ፣ ከስህተታቸው እንደተማሩና የአቅጣጫ መስመራቸውን ያስተካከሉ መሆናቸውን ነው የተረዳሁት። ሰዉ ብዙ ያወራባቸዋል፤ በወያኔ ብር ነው የሚሠሩት ምናምን ይላሉ፤ እኔ ግን የምለው ከማንስ ቢቀበሉ ምን ጣጣ አለው? ወያኔስ ቢሆን ዱሮ መጥፎ ነበር በሚለው ስሙ ብቻ ልንኮንነው አይገባም፤ በተለይ አሁን ከፌዴራሊስት ኃይሎች ጋር እየሠሩ እንደሆነ ወያኔዎች ይናገራሉ፤ ራሳቸውን ካስተካከሉና በትክክለኛው መንገድ እስከሄዱ በዱሮ ሥራቸው ብቻ ልንኮንናቸው አይገባም፤ እኔ እውነቱን ልንገርሽና ከግብፅም ገንዘብ ቢቀበሉ ግዴለኝም” ያለው ሲልቨር ስፕሪን ሜሪላንድ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩበት ሥፍራ የሚኖር አስተያየት ሰጪ ነው።  

“ጠሮባቸዋል እያለ ነው ፒፕሉ እዚህ አካባቢ የሚያወራው፤ ዐቢይ ደግሞ አይለቀንም ብለው የፈሩ ይመስላል፤ እኔ ምንም አስተያየት የለኝም ግን አይመቹኝም፤ በቃ አቦ ተፋቱን ነው የምለው” በማለት የተናገረው ዕድሜው እስከ 20ዎቹ አጋማሽ የሚገመተው ወጣት ነው።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንዲህ ይነበባል፤

ከኢትዮ 360 ሚዲያ የተሰጠ መግለጫ!!!

ኢትዮጵያ ሀገራችን በፈታኝ እና በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ በሰሞኑ የተፈጠረው ትርምስና ግድያ በእጅጉ ያመለክታል።

በብሄር ፖለቲካ ተከፋፍላ የምትገኘውን ሀገራችን እንደ ክፍተት በመጠቀም በውጭ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት የህዝቡ ችግር እለት እለት እየተወሳሰበና እየባሰበት መጥቷል።

ኢትዮ 360 ሚዲያ የሕዝብ ድምፅ ሆኖ ከተቋቋመበት ካለፈው አንድ አመት ወዲህ በሀገራችን የሚከናወኑ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች በመዘገብ እና በመተንተን ህብረተሰቡን በማገልገል ላይ ይገኛል።

የሚዲያ ተቋማችን ሕዝብን የሚጎዱ ተግባራትን በማጋለጥ የሞጋችነት ሚናውን ሲጫወትም ቆይቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በተቋማችን ውስጥ የተከናወኑ ስራዎችን ለመገምገም አመታዊ የስራ እና የፋይናንስ ሪፖርት ቀርቦ ሰሞኑን ጠቅላላ ጉባዔ ስናካሂድ መቆየታችንንም በይፋ መግለፃችን ይታወሳል።

በዚሁ ውይይታችንም ኢትዮ 360 ሚዲያን ስንመራ የቆየን በየደረጃው ያለን የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም አባላት በተቋሙ ውስጥ የነበሩ ጠንካራ እና ደካማ ሁኔታዎች ገምግመናል።

በዚሁም ምክንያት በአመራር ላይ የነበርን ሰዎች ሁላችንም በግላችን በወሰንነው መሰረት ሀላፊነታችንን በገዛ ፈቃዳችን ለቀን ለተተኪ ለማስረከብ የተናጠል ስምምነት ላይ ደርሰናል።

በዚሁ አጋጣሚ ተቋሙ የገመገማቸውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች ከግምት አስገብተው ባሉበት ሀላፊነት እንዲቀጥሉ ጉባኤው ያቀረበውን ጥያቄ የማኔጅመንት አባላቱ “ከምስረታው ጀምሮ በሀላፊነት አገልግለናል! አዲስ አመራር ሊተካ ይገባል!” በሚለው አቋማቸው ጸንተዋል። ዋና ስራ አስኪያጃችንም በሀላፊነቱ እንዲቀጥል መባሉን እንደሌሎች የአመራር አባላት በሃሳቡ ባለመስማማት በማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገፁ ከኢትዮ 360 መልቀቁን መግለፁ አይዘነጋም። ይህ ከሆነ በኃላም ኢትዮ 360 ሚዲያ እንዳይቀጥል የሚፈልጉ አካላት በመካከላችን በፖለቲካ አመለካከትና በፋይናንስ ምንጭ የተጣላን በማስመሰል የፈጠራና መሰረተ ቢስ ወሬ በማህበራዊ ሚዲያው እስከመንዛት ደርሰዋል።

ይህ ሁኔታ የኢትዮ 360 ደጋፊዎችና ህዝቡን ጥርጣሬ ውስጥ ለመክተት ሆነ ተብሎ ውዥንብር በሚነዙ ሀይሎች የተፈበረከ ወሬ ቢሆንም እኛ የሚዲያው አባላት በእልህና በቁጭት የበለጠ ጠንክረን እንድንወጣ የረዳን መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እንገልፃለን።

ያም ተባለ ይህ ግን በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ያለችበትን አሳሳቢ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት አንድም አባል በስብሰባው ሳይጎድል የተቋማችን ጠቅላላ ጉባዔ ቀጥሎ የኢትዮ 360 ሚዲያ ችግሮችን በውይይት በመፍታታችን ስራችንን በተጠናከረ መንገድ ለማስኬድ ስምምነት ላይ ደርሰናል።

በዚሁም መሰረት የዋና ስራ አስኪያጁን መልቀቂያ በመቀበል ጠቅላላ ጉባዔው አዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመሰየም እንዲሁም አዲስ የቦርድ አባላትን እና የዘርፍ ሀላፊዎችን በመምረጥ ስብሰባችንን አጠናቀናል።

ኢትዮ 360 በተቋሙ ውስጥ ያጋጠሙትን ችግሮች በውይይት በመፍታቱና ዓላማውንም ለማስቀጠል የፀና አቋም ያለው በመሆኑ መላው የድርጅቱ ደጋፊዎች እና የዝግጅታችን ተከታታዮች ይህን ለሕዝብና ለሀገር የቆመ ሚዲያ በገንዘብ እና በቁሳቁስ እንድትደገፉ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን። ሚዲያችን እና ሚዲያችሁ አሁን ካሉበት ፈታኝ ችግሮች ዋነኛው የፋይናንስ እጥረት ነውና ይህን ተግዳሮት እንቋቋመው ዘንድ ከጎናችን በመቆም አብሮነታችሁን ታሳዩን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን።

ኢትዮ 360 ሚዲያ መቼም ቢሆን ዓላማውን ይዞ ይቀጥላል።

እናመስግናለን። የኢትዮ 360 ሚዲያ አባላት!!

የመግለጫው ዓላማ ከማንም ገንዘብ አልቀበልም በሚል ሃሳብ ለማስቀየር ነው የሚሉ ወገኖች ጭንቀት የወለደውና ዋናው ትኩረቱ ገንዘብ እንደሆነ ራሱን ያጋለጠ መግለጫ ነው ይላሉ።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ፍጹም አረጋ የሰሞኑን ግጭት አስመልክቶ ከጽ/ቤታቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት የሚከተለውን ማለታቸው ይታወሳል ብለው ነበር፤ “በውጭ ሆናችሁ በጥላቻ ስሜት ተሞልታችሁ የሕዝባችንን በእኩልነት የመኖር ተስፋ በማጨለም … (በሕዝባችን ዘንድ) የማይገባ ልዩነትና ጠላትነት በመፍጠር እርስበርስ እንዲጨራረስ የምትሠሩ ሕዝቡ አቁሙ ይላችኋል” ካሉ በኋላ አምባሳደሩ ሲቀጥሉ ሕዝቡን እንዲጨራረስ ማድረግ በየትኛውም መልኩ “የሞራል ውድቀትና የሕግ ጥሰት ነው። በአሜሪካም የሚመለከተው አካል በጥላቻ መልዕክቶች ላይ የሚፈጸሙ ግጭቶችን እንደማይታገስ አረጋግጦልናል” ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Left Column, News, Politics, Slider Tagged With: Ethio 360

Reader Interactions

Comments

  1. ነፃ ሕዝብ says

    July 5, 2020 05:40 pm at 5:40 pm

    ጎልጉል ድኅረ-ገጽ በኢትዮ -360 ሚዲያ ላይ መርዛችሁን መጥፋት ከጀመራችሁ ውላችሁ አድራችሁዋል ፥ የጎልፉል ነገር በእጅጉ ያስገርማል ፥ የአብይን መንግሥት መቃወም እንደ ትልቅ ሃጢአት ቆጥራችሁ ያለ የሌለ የውሸት ድሪቶዋችሁን ትደርታላችሁ ፥ ኢትዮ-360 ሚዲያ አብይን በመቃወሙ ውሸታሙን የኦነግ አምባሳደር ፍጹም አረጋን ፈርተውታል … ድንቄም ፈርተውታል ! ከኢትዮ-360 ሚዲያ ጋር ሺዎች ኢትዮጵያውያን መኖራችንን እንዴት እንደዘነጋችሁት አላውቅም ፥ ጎልጉል ድኅረ-ገጽ በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት በሐረር ፥ በአርሲ -አሳሳ ፥ በዝዋይና በተለያዩ በኦሮሚያ ግዛት ውስጥ የተፈጸሙትን የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አንዳችም ትንፍሽ ያላችሁት ነገር የለም ፥ ይህም ከገዥው የአብይ መንግሥት ጋር ተለጥፋችሁ ያልበላችሁን ታካላችሁ ፥ እናንተ በጣም ልትወገዙና ድኅረ-ገፃችሁንም መዝጋት ነበር ፥ ምክንያቱም እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ ጥሰት እያያችሁ ለመፃፍ ያልፈለጋችሁ አሜሪካ ድረስ ኢትዮ -360 ሚዲያን ትወነጅላላችሁ ፥ በኦሮሚያ ግዛት ውስጥ የአማራ ሕዝብ እየተፈጀና ንብረቱ እየወደመ ለምን መናገር አልፈለጋችሁም ? ጎልጉል የኦነግን ዓላማ የምታራምድ በእነ ኢትዮጵያ ሱሴ የምትደገፍ ትመስላለች ፥ ጎልጉሎች በሩቅ ርቀት ስለአለው ኢትዮ-360 ሚዲያ ከማወራታችሁ በፊት እፊታችሁ የሚፈጸመውን ዘግናኝ ግድያና ዘረፋ አንድ ለማለት ሞክሩ በተረፈ ኢትዮ-360 ሚዲያ ያብባል ፥ ትልቅ ሚዲያ ሆኖ ይወጣል ፥ የኢዮጵያውያን ድምጽና አንደበት ሆኖ ይቀጥላል ፥ ፍጹም አራጋ ውሸት እንጂ ሌላ አያውቅም ፥ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ በኮቪድ-19 አልቀዋል ብሎ የዋሸ ቀጣፊ ነው ፥ ሰውየው ከማውራት በቀር ያውም የኢትዮጵያውያንን ሚዲያ ማዘጋት ይቅርና የእርሱን አንደበት ማዘጋት እንችላለን ፥ አትድከሙ ፥ የእናንተ ነገር አንዳንድ ጊዜ በእጅጉ ያስገርማል ፥ አንዴ በሚዲያው ላይ -ሌላ ጊዜ ደግሞ በጋዜጠኞቹ ላይ የውንጀላችሁ ጋጋት ጥግ ደርሶዋል ፥ ጋዜጠኛ ለእውነት መቆም እንጂ የገዥዎች ዕድሜ ማራዘሚያ መሆን መቆሸሽ ነው ፥ ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!

    Reply
  2. ethiopian secular humanist says

    July 7, 2020 07:14 am at 7:14 am

    ጎልጉል ኢትዮጵያ እና ኢትዩጵያን በሚመለከት በአገሪቱ ከሚወጡት ጋዜጦች ሁሉ እጅግ ተአማኒነት ያለው ጋዜጣ ነው። የሚሰማህ የለም። ለምን በaudio video እንደማይመጡ ሊገባኝ አልቻለም። የመጀመሪያው subscriber የምሆነው እኔ ነኝ።

    Reply
  3. who is ethiopian lover? says

    July 10, 2020 08:52 pm at 8:52 pm

    ጎላጉል፤ ኧረ እንዴት ነው ከኛ በላይ ኢትዮጵያዊ የለም ባይነታችሁ እንዲህ የተለጠጠው? ለምንድን ነው አስተያየት እየመረጣችሁ የምትሰርዙትና የምታቀርቡት? ከትግራይ ኦንላይን በምን ተሻላችሁ? ነው አገራችንን ለመውደዳችን አስተያታችን መለኪያ ሊሆን ነው? መኢሶንም እኮ በታሪኩ ይህንን ነው ያደረገው – አሁን ጥላው እንኳን የለም፤ ምን ሲል እነደነበር ላስታውሳችሁ? ሂሳዊ ድጋፍ እያለ ደርግ ሥር ተለጠፈ፤ ከዛ ከደርግ ፊት ሲያገኝ፤ ከእነሱ አምባገነኑ ደርግ በላይ ለኢትይጵያ የሚያስብ ሁሉ መለኪያ እንደ እናንት እንዳሁኑ ዐብይና መንግሥቱን እነሱም ደርግና መንግሥቱን ማን ተቃውሞት አሉ፤ ተቃውሞ መብት ነው ድሮም በደርግ ዘመን አሁንም በ አብቹ ጊዜም፤ በጎልጉል ላይ አስተያየት መስጠትም ተቃውሞ ነው፤ እባካችሁ ከታሪክ ተማሩ፤ “ፈጣን ነው ባቡሩ፤ ያልተሳፈሩ . . .” ይታውሳችሁአል?

    አሁን ላይ ኢትዮጵያን መወደድ መለኪያውና ለኪው ምንና ማን ይሆን?

    Reply
    • Editor says

      July 11, 2020 01:03 am at 1:03 am

      ስድብ፣ ስድነት፣ ወዘተ የሚታይበት አስተያየት ይሰረዛል። ከዚያ ውጭ ያለ አስተያየት ሰርዘን አናውቀም። እንኳን አሁን አይደለም በዘመነ ወያኔም ወያኔዎች እዚህ ገጻችን ላይ ከስድብ የነጻ አስተያየት ሰጥተው አልሰረዝንም። ይህ አስተያየትም የታተመው በዚሁ አግባብ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። አስተያየት ጽፎ “ፖስት” የሚለውን መጫን አስፈላጊ መሆኑ እያሳሰብን አጠቃላይ የኮምፒውተር ሥልጠና ስለማንሰጥ በዚህ ላይ ብዙ ለማለት የማንችል መሆናችንን ከይቅርታ ጋር ለመናገር እንወዳለን።

      ይህንን አስተያየት በተላከው መሠረት አትመነዋል። ተሰረዘብኝ የምትለው/የምትዪው ካለ መልሶ መጻፍ ይቻላል። ስድነትና ስድብ ያዘለ ከሆነ አሁንም ይሰረዛል።

      ከዚህ በፊት July 5, 2020
      “don’t see any hard evidence other than hearsay and accusations. Let Minalachew speak and provide irrefutable evidence. You get off from your high horses and stick to the journalism than being a mouth piece of others and your wishful thinking.”

      በማለት የተጻፈውን አስተያየት በተመለከተ ከሆነ አስተያየት ከሆነ እሱን አስተያየት የጻፍከው/የጻፍሽው “ኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ” ለሚለው ጽሁፍ ነው። ያንንም አስተያየት እዚያው ሥር አትመነዋል። እዚህ ላይ ማየት ትችላለህ/ትችያለሽ።

      ስለ መኢሶን ምናምን የተጻፈውን ብዙም የምናውቀው አይደለንም። ያኔ አልተወለድንም። አንድ በርግጠኝነት መናገር የምንችለው ግን የዚያ ዘመን ጦስና ፖለቲካ እናውቃለን ብለው ከውጭ አገር የተቀዳ “ጋርቤጅ” ሕዝባችን ላይ “ርዕዮትዓለም” በሚል የደፉበት ለችግራችን ግምባር ቀደም ተጠያቂዎች መሆናቸውን ነው። በዚህ አጋጣሚ ሻዕቢያ፣ ወያኔ፣ ኦነግ፣ ወዘተ የተባሉት መጻጉዎች የተፈለፈሉት በዚያው ዘመን አካባቢ ሆኖ ጥርሳቸውን የነቀሉትም በዚሁ የጥላቻና የወገንተኛ ፖለቲካ መሆኑን ማስታወስ እንወዳለን።

      መልካም ጊዜ
      አርታኢ

      Reply
  4. agolguay says

    July 11, 2020 10:42 pm at 10:42 pm

    አርታኢ/አርታኢት ወይስ አርታኢዎች? መቼም ማንነታችሁን ደብቃችሁ ስለሆን ምን ይደረግ? ለማንኛውም መልሳችችሁ ይበልጥ ማንነታችሁን ይገልፃል፤
    በዛ ጊዜ አልተወለድንም አናውቅም ነው ያላችሁት? ሕዝቅ ኤል ገቢሳን አስታውሳችሁኝ አፄ ሚኒሊክን አላውቀውም ያለውን፤ ታሪክን ማንበብ እንጂ በዛ ዘመን አልተውልድንም ምን ማለት ነው? በአፄ ቴዎድሮስ ወይስ ዮሐንስ ጊዜ ተወልደን ነው እንዴ ታሪካቸውን የምናውቀው? መለስ አላችሁና የዛ ዘመን ጦስ ነው አላችሁ እንዴት አውቃችሁት – የመንደር ወሬና ምንም ያልሠሩ የሚያወርት ይዛችሁ ነውና እንዚህም ከነፍሰ ገዳይ የደርግ ካድሬዎች ጀምሮ ብዙ ስለሆኑ አጥርቶ ማስተዋል ይጠይቃል “አርታኢ” እያሉ ራስን መሾም እንዲህ ያስገምታል፤ የውጭ ጋርቤጅ አምጥተው ማለት የታሪክ ድህነትና አለማውቃችሁ ሌላው ምሥክር ነው፤

    አስተያየት ለማቅርብ እንዴት እንደሆነ ማሰለጠን አይጠበቅብንም? አሽሙር ተሸሙሮ ተሙቷል? አስተያየት ቀርቦላችሁ እያለ? ይህቺም ዕውቀት ሆና ነው? አደብ ግዙ አስተያየት ሰጪዎችን መዝለፍ ማሽሟጠጥ ተራነት ነው፤

    የአስተያየት ሰጪውን ምንጭ ለማወቅ የሄዳችሁት እርቀት የሚገርም ነው፤ ዕድሜ ለቴክኖሎጂ የኢንተርኔትና ኢሜይል ልውውጦችን ፊርማ ማወቅ ይቻላል -ያንን ነው ሰላይ ድርጅቶች የሚሠሩት፤ እያንዳንዱ ለውውጥ ከአድራሻው ጀምሮ በየት በየት በኩል እንዳለፈ ይታውቃል እንደዛም እንዲሆን ተደርጎ ነው ኢንተርኔት እናንተ ባልተወልዳችሁበት ዘመን የተሠራው፤ እናንተ ግን አስተያተ መቀበል እንጂ ምርመራ ውስጥ ምን አገባቸሁ?

    በጠቅላላ የመልሳችሁ ቃና እንዸት ተደፈረን አይነት ነው፤ ተረጋጉ ጎበዝ፤ ስድብ አልተፃፍም በእኔ በኩል ለምን እንደዛ እንዳላችሁ እናንተው መልሱ፤ ለመሆኑ የምታውጧቸውን ፅሁፎች ነንባላችሁ? ስድብ፤ ውንጀላ፤ አሽሙር፤ ምኞት የተሞሉበት ነው፤ ዝም ብላችሁ ተቀበሉ መታበይ ነው?

    ተነስተው ውንደከሰሙትና የሌላ ወሬና ዜና ፍራሽ አሳዳሽ ሆነው እንደከስሙት ብዙ ሚዲያና ድረገፆች ከመክሰም ወይም አንባቢ ከማጣት ይሰውራችሁ፤ ሰብስክራይብ ያደረጉ ደንበኞቻችሁ ቁጥር 747 ብቻ መሆኑ አንዱ ምልክት ይሆን? እስቲ የድረ ገፃችሁን ጉብኝት ቁጥር አድርጉና እንየው፤ ይህንን ማሳየት አይጠበቅብኝም

    Reply
  5. Abrham says

    July 22, 2020 01:12 am at 1:12 am

    To hate prime minister Abiye, one must be qualified closer to evil.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule