
ምዕራብ ጎንደርን ጨምሮ ሰፊ እርሻ መሬት ያላቸው አካባቢዎች ሰብል የሚሰበስብ ሰራተኛ ማስታወቂያ ሲያወጡ ይህ የመጀመርያቸው አይደለም። ማህበራዊ ሚዲያ በማይታወቅበት ጊዜ በኢቲቪና አማራ ቲቪ ጭምር በሚሊዮን የሚቆጠር ሰራተኛ እንፈልጋለን ብለው ማስታወቂያ ሲያስነግሩ ኖረዋል።
ባለፈው አመት በዛ ቃውጢ ጦርነት ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ በርካታ ሰብል የሚሰበስብ ሰራተኛ በማስታወቂያ ጠርተዋል። በሌላ አካባቢ ያለው አርሶ አደር የራሱ ሰብል እስኪደርስ ለአንድና ሁለት ወር ሰርቶ እንደሚመለስ ይታወቃል። በቋሚነት በርሃ ወርዶ የሚሰራ፣ ካምፕ ተሰርቶለት በአካባቢው የሚከርም ሞልቷል። የሰብል ስብሰባን ብቻ ስራቸው አድርገው በቆላማ አካባቢዎቹ የሚኖሩ በርካታ ወጣቶች አሉ። ለረዥም አመታት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚቀበሉት ወጣት በላይ የቋራ፣ የመተማ፣ አርማጭሆ፣ ወልቃይት ጠገዴ አካባቢዎች ሰብል የሚሰበስብ ወጣት ይቀበላሉ። በርካታ ህዘብ የሚሳተፍበት ስለሆነ አዲስ ገቢዎቹ ጎፈር፣ የለመዱት ሳሉግ እየተባሉ ይጠራሉ። በቆላማ አካባቢዎች በሰራተኞች የተመሰረቱ ከተሞች አሉ።
ከ1950 በኋላ የትግራይ ወጣት ሳይቀር ተከዜን ዋኝቶ ተሻግሮ ሰርቶ ወደ ትግራይ ይመለስ ነበር። በዚህ ወቅትም ከደቡብ ኢትዮጵያ ድረስ ለሰብል ስብሰባ የሚመጡ ወጣቶች አሉ። አይደለም ሰብል ስብሰባው ሙጫና እጣን ለቀማው በሺህ ለሚቆጠር ወጣት የስራ አድል ይፈጥራል። ሰብል ለመሰብሰብ ብቻ አይደለም እያንዳንዱ አራሽ አካባቢውን የሚጠብቁለት ሚሊሻዎች ይቀጥራል። ስራ አስኪያጅ ይቀጥራል። አንዳንዱ ካምፕ ከትንንሽ ሰፈሮች አይተናነስም። አንድ አርሶ አደር በርካታ ሰራተኞች ይዞ ይከርማል። አንድ አርሶ አደር ለስድስት ወር ያህል ለአንድ የሰራተኞች አስተባባሪ ከፍተኛው እስከ 120 ሺህ ብር ድረስ እየከፈለው ነው። በወር 20 ሺህ ብር ማለት ነው። ምግብና መጠለያ ተችሎት።
አንድ ሚሊሻ ለስድስት ወር እስከ 80 ሺህ ብር እየተከፈለው ነው። በወር ከ10 ሺህ ብር በላይ ነው። ምግብና መጠለያን አሰሪው ችሎ ጎን ለጎን የተወሰነ ሄክታር ይታረስላቸዋል። ሚሊዮን ሰራተኛ ወደ አካባቢው የሚሄደው እንዲህ አዋጭ ስለሆነ ነው።
ይህ ሆኖ እያለ ታዲያ ለሰብል ስብሰባ ማስታወቂያ ሲወጣ የመከላከያ ምልመላ አስመስሎ መጀመርያ ያቀረበው ትህነግ ነው። ከእሱ ጋር የሚሰሩና በሱዳን በኩል ሰርገው እየገቡ ህዝብን ለማጥቃት ሲጥሩ የከረሙ ተላላኪዎችም ቀስቅሰውበታል። እነዚህ አካላት ሰብል ሲያቃጥሉ፣ የአርሶ አደሩን ከብት ሲገድሉ የሚታወቁ ናቸው።
አሁንም የሰብል ስብሰባ ማስታወቂያውን ሆን ብለው በሀሰት ወታደራዊ ምልመላ አስመስለው የሰሩበት ህዝብ ሰብሉን እንዳይሰበስብ ነው። አካባቢውን ወርረው ሰብሉን ማቃጠል ባይችሉ ሳይሰበሰብ እንዲቀር የሀሰት ዘመቻ ከፍተዋል። ኢትዮ 360 የሚባል ሚዲያ ይህን የህወሓት አጀንዳ እያራገበ ይገኛል። ይህን ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ሆን ብሎ ካላስተላለፈ በአስቸኳይ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል። ህወሓት የአማራን ባለሀብት የሰሊጥ ነጋዴ ወዘተ እያለ ሲፈርጅ ከርሟል። አሁን ሰሊጡ እንዳይሰበሰብ ሲቀሰቅስ 360 ተደርቦ በህዝብ ጥቅም ላይ ዘምቷል።
ለሰራዊት አፈሳ ቢፈለግ ወጣቱ ያለ በየከተማውና በየቤቱ ነው። ምዕራብ ጎንደር ድረስ መሄድ አይጠበቅበትም። ምዕራብ ጎንደር ማንንም አታልሎ ወደ ጦር ግንባር የሚያስገባ አይደለም። አርሶ አደሩ ብቻውን ሱዳንን ቀጥ አድርጎ የያዘ የእነ ባሻ ጥጋቡ ቀዬ ነው። ኢትዮጵያም አንድ ሚሊዮን ምልምል አያስፈልጋትም።
ምዕራብ ጎንደርንና አካባቢውን የማያውቁ ይህን ያህል ሰራተኛ ምን ሊሰራ ነው ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ። በህወሓት አላማ ወይንም በምቀኝነት ግን ሰብል እንዳይሰበሰብ ሊቀሰቅሱ ባልተገባ ነበር። ኢትዮ 360 በጦርነቱ ምክንያት መሬት ጦሙን አደረ ሲል ከርሞ፣ አሁን ለሰብል ስብሰባ የሰራተኛ ቅጥር ሲወጣ የህወሓትን አጀንዳ እያራገበ በህዝብ ላይ ሌላ ጦርነት ከፍቷል። በአንድ ዞን ሚሊዮን የስራ እድል ሲፈጠር እንዲስተጓጎል እየሰሩ ነው። ይህን የተናገሩ ሰዎች በግብታዊነት ከሆነ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። አርሶ አደር ሰብል እንዳይሰበስብ ቅስቀሳ ማድረግ በህዝብ ላይ ጦርነት መክፈት ነው። ሚሊዮን ወጣት ስራ እንዳይሰራ መቀስቀስ ወንጀል ነው። ያፈጠጠ የህዝብ ጠላትነት ነው። (ጌታቸው ሽፈራው)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በህዋላ ዓለም በሁለት የአስተሳሰብ ምልከታ ተገምሳ ይህም ያም ሲታመስ ከነበረው የቀዝቃዛው ጦርነት ይልቅ አሁን በምድር ላይ የሚደረገውና ሊሆነ የታሰበው አስፈሪ ነው። አንድ በኳስ ጫወታ ዙሪያ በተፈጠረ ግርግር ተጨፍልቆ ሲሞት ሌላው ለሃገርህ ለወገንህ ለዘርህ ነው እየተባለ ወደ ቄራ እንደሚወሰድ ከብቶች ያለ ልቡ ይጨፈጨፋል፤ ይጨፈጭፋል። አሁን ዪክሬንን አይዞአችሁ የሚሉ የምዕራባዊያን ሃገሮች ሁሉ ለራሳቸው ሥጋት እንጂ ለዪክሬን ህዝብና ምድር ደንታ የላቸውም። ያ ቢሆን ኑሮ በ 2014 በነጮች ክሬሚያ ስትያዝ ጦራቸውን ባሰለፉም ነበር። የሰሜን ኮሪያው እብድ በጃፓንና በደቡብ ኮሪያ ጭንቅላት ሚሳኤል አሳልፎ ባህር ላይ ሲጥል፤ የራሽያው መሪና ደጋፊዎቹ ታክቲካል የኒኩሌር መሳሪያ ጦር ሜዳ ላይ እንዲውል ሲወተውቱ ረጅም ድላ ባይመቱበት ያስፈራሩበት እንዲሉ ዋሽንግተን ደግሞ ዋ እንዳታረገው በማለት አስጠንቅቃለች። እውቁ የቲዎሮቲካል ፊዚክስ ምሁር Stephen Hawking ስለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ባንድ መድረክ ተጠይቆ እንዲህ ብሎን ነበር። “I fear that AI may replace humans altogether. If people design computer viruses, someone will design AI that improves and replicates itself. This will be a new form of life that outperforms humans”. አሁን እሱ በህይወት የለም እየሆነ ያለው ያ ነው። ዛሬ በድሮን ውጊያ ከመግደል በፊትና ከተገደሉ በህዋላ እያዪ መጨፈር የተለመደ ሆኗል። ጀግና ተኳሽና አታኳሽ የሚባለውም እየከሰመ ይገኛል። ሁሉም በቴክኖሎጂ እየታገዘ ከሩቅና ከቅርብ ነገሮችን ያወድማል። Deep fake and doctored up Video and Audio የሰውን አስተሳሰብ ለማዛባት ያለ ልክ ይረጫሉ። በዚህ ላይ ረሃቡ፤ በሽታውና የተፈጥሮ ቸንፈር ባለጠጋና ድሃ ሳይል እያጠረገው ይገኛል። ባጭሩ ዓለማችን አረንቋ ውስጥ ለመግባት በመንደርደር ላይ ትገኛለች። ጫፉ ላይ ደርሳለች።
ወደ አፍሪቃ ስንመለስ ይበልጡ ችግራችን ራሳችን በራሳችን ላይ የምናደርሰው ነው። ሰው በገንዘብ ታውሮ የህክምና ባለሙያው በችኮላ አንዷን ቀዶ ሳትነሳ ሌላ ሊቀድ የሚሄድ፤ የሚታዘዘው መድሃኒት በእጅ አዙር ከራሱ ወይም ከዘመድ የመድሃኒት መደበር እንዲገዛ የሚያዝ፤ ለዚያውም የማያድን የቻይና መድሃኒት! ቆመው ክሊኒክና ሆስፒታል ሊታከሙ ወይም ለወሊድ ገብተው አስከሬናቸው የወጣ እልፎች ናቸው። ብቻ ነገር ሁሉ አስረሽ ምቺው ሆኗል። ወያኔ የእህል ክምር የሚያቃጥል፤ የቁም ከብቶችን በጥይት ተኩሶ የሚገል የበድኖች ጥርቅም ስለሆነ ከወያኔ መልካም ነገር አይጠበቅም። ግን ሰው በሸፍጥና ሌላውን በማሰቃየት እስከ መቼ ነው የሚኖረው? ዘመናችን እኮ የተወሰነ ነው። እስከ መቼ ነው ለትግራይ ህዝብ ለአማራ ህዝብ እየተባለ ህዝቡ በስሙ የሚነገድበት? እንዴት ሰው ቤት እያቃጠለ፤ ሰው እያረደ፤ ሃገር እያፈረሰ፤ ምርት እያወደመ ተራብን ድረሱልን በማለት ይጣራል? ህዝባችን የሚያልፍለት መቼ ነው? የተመድና የአሜሪካ ተራዶ ድርጅቶች ተጠዋሪ ከመሆን መቼ ነው የሚድነው? ግን እብዶች ለብሰው ሰው ነን በሚሉበት ሃገር ማን ማንን ይሰማል? መጋደል መገዳደል ነው። በሁመራ፤ በመተማ፤ በሌሎችም ሰሊጥ፤ ጥጥ፤ ሌላም የተለያዪ አዝዕርቶችን በሚያበቅሉ ቦታዎች ሰዎች ለጉልበት ሥራ መጠራታቸው ዛሬ የተጀመረ አይደለም። በፊትም ነበር። ሰው ከሃገሪቱ ልዪ ልዪ ክፍሎች ወደዚያ በመጓዝ የቀን ሥራ አይነት (በጊዜአዊነት) ስርቶ ጠቀም ያለ ገንዘብ ይዞ ያኔም ይመለስ ነበር። አሁን ይህን ጥሪ እንደ ጦር መሳሪያ የሚጠቀሙበት ድርቡሾች ሁሉ ለሃገር የማያስቡ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚሉ ብቻ ናቸው። እኛም እናልፋለን። መቼ ነው ከእውነት ጎን የምንቆመው? ያ ጊዜ ይመጣ ይሆን? አላውቅም። ከስር ባለው የ19ኛ ክፍለዘመን የእንግሊዘኛ ግጥም ሃሳቤን እደመድማለሁ።
To every man upon this Earth
Death cometh soon or late.
And how can man die better
Than facing fearful odds
For the ashes of his fathers
And the temples of his gods? Thomas Babington Macaulay – Horatius
You have lost credibility big time.