የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት HR6600/S3199 ሕግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ኃሳብ እንዲቋረጥ ወሰነ። HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት ውሳኔ ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ረቂቅ ህጉ እንዲቋረጥ ለጊዜው ከስምምነት የተደረሰበት ውሳኔ በቀጣይም ህግ ሆነው እንዳይፀድቁ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ካውንስሉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫና በመቃወምና ዳያስፖራ ማህበረሰቡን ጭምር በማስተባበር ከፍተኛ የህዝብ ዲፕሎማሲ ስራ በመስራት ላይ ያለ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ ተቋም ነው። (AMN) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከሽፏል!