የወንበዴው ቡድን አምበል በሆነው መለስ ዜናዊ በያኔው “ፓርላማ” ፊት ሌብነቱ ተዘርዝሮ እና የሥነምግባር ብልሹነቱን አምኖ ከፓርላማው የተባረረው ታምራት ላይኔ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን እየተመኘ ነው። ከበረኻ ወዳጆቹ እነ ሰዬ አብርሃ ጋር በመሆን ነው በዚህ ሥራ የተጠመደው።
ታምራት በመለስ ትዕዛዝ በፓርላማው ፊት ሌብነቱን፣ ሥነ ምግባሩ የጎደፈና መሪ መሆን የማይችል መሆኑን አምኖ መባረሩ ትክክል ነው በማለት ተቀብሎ የላሰውን ስኳር ሳያጣጥም ወዲያውኑ ወደ እስር ቤት ነበር የተወረወረው።
ጥያቄያችን ያኔ በዚህ መልኩ ብቃት የለኝም፣ ሥነ ምግባሬ ለተቀመጥኩበት የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር አይመጥንም፤ ስለዚህ ልባረር ይገባኛል፤ ካልተባረርኩ ራሴ በገዛ ፈቃዴ እለቅቃለሁ ያለው ታምራት ዛሬ በምን ችሎታውና ሥነምግባሩ ነው ተመልሶ የኢትዮጵያ መሪ ለመሆን የሚመኘው?
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
ነፃ ሕዝብ says
ጎልጉል ዛሬ እውነት ይዛችሁ ብቅ ብላችኋል ፥ ልትመሰገኑ ይገባል ፥ ታምራት ላይኔ በመጀመሪያ የአማራ ተወላጅም አይደለም ፥ አቶ ገ/መድኅን አርአያ የከምባታ ተወላጅ እንደሆነና ስሙም ታምራት እንዳልሆነ በጽሁፍ አረጋግጦ ነግሮናል ፥ ጅብ በማያውቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት (ጀንዲ) አንጥፉልኝ አለ ይባላል ፥ ወንጀለኛው ታምራት ላይኔ በዘመኑ ጉደኞች ኢትዮ 360 ሚዲያ ላይ እየቀረበ በተደጋጋሚ ሲቀሳፍት ሰምቼው ለአቅራቢው ሀብታሙ አያሌው በኢሜልና በእነርሱ fb ላይ ሃሳብ አቅርቤለት ነበር ፥ ነገር ግን ሚዲያው ከፋሽስቱ ህወሃትና ግብረ_አበሮቹ ቀለብ እንደሚሰፈርለት ባለማወቄ እውነተኛ ኢትዮጵያውያን መስለውኝ የአቅሜን ለማለት ሞከርኩ ፥ አልተሳካልኝም ፥ ኢትዮ 360 ሚዲያ የእነቴዎድሮስ ፀጋየ የህወሃቱ አፈቀላጤ መሆኑንም ለመረዳት በጣም ዘግይቼ ነበር ፥ ለማንኛውም ታምራት ላይኔ ዳግማዊ ኢህዲን ሆኖ ለመምጣት ከመሰሎቹ ጋር ሴራውን እየሸረበ ይገኛል ፥ እኔ የገረመኝ የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዴት ቢንቁት ይሆን በድጋሚ ወደ ሥልጣን ለመምጣት ያሰቡት ? ለማንኛውም ጊዜ ከሰጠን እናየው ይሆናል ፡፡