• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ

November 5, 2025 12:06 pm by Editor Leave a Comment

* “እኛ የገባነው ልናፈርሰው ነው” ሕዝቅኤል ገቢሣ

በሰላማዊ ትግል መንግሥት ለመጣል ማቀዱን አስታውቆ ሃያ አንድ ቦርድ አባላትን ሰይሞ የሰነበተው የ-አብሮነት ማኅበር ሰባት ሥራ አስፈጻሚዎችን መምረጡ ታወቀ። ማኅበሩ “ለቦርድ አባላት” በሚል ባሰራጨው የ“እንኳን ደስ አላችሁ” መልዕክት አቶ ልደቱ፣ ከአማራ የማኅበሩ ፕሬዚዳንትና ሊቀመንበር ሆነዋል። መቅደስ አዳነ ከወላይታ (ምክትል)፣ አሸናፊ አብርሃም ከደቡብ (ጸሐፊ)፣ ሙሉጌታ ዘለቀ ከአማራ (ገንዘብ ያዥ)፣ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር ሕዝቅኤል ገቢሣ /በተለይ እንግሊዘኛና ትግርኛ ጠንቀቀው ስለሚያውቁ/ ከኦሮሞ፣ የድርጅት አስተባባሪ እስማኤል ጎርሴ ከሶማሌ፣ የውጭ ግንኙነት ኦፊሰር መስፍን አየነው ከትግራይ መመረጣቸው ይፋ አድርጓል።

ቀደም ሲል ምርጫው ከመደረጉ በፊት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው አባላቶች ሕቡዕ እንደሚሆኑ ተመልክቶ እንደነበር የስብሰባው ተሳታፊዎችን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። ያለፈው ሳምንት ባለመግባባት ምርጫው ሳይካሄድ ከቀር በኋላ ሃሳብ ተቀይሮ ሕቡዕ እንዲሆኑ ተወስኖ የነበረው የሥራ አስፈጻሚዎች ዝርዝር ታውቋል።

በተከታታይ ለዲሲ የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ መረጃ የሚሰጡት ወገኖች እንዳሉት ከሆነ ሰኞ ዕለት በተካሄደው ምርጫ ቀደም ሲል አቶ ልደቱ በግል እንዳይመረጥ ቅስቀሳ ያደረጉበት የርዕዮት ሚዲያ ባለቤት ቴዎድሮስ ጸጋዬ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሳይሆን ቀርቷል።

ቴዎድሮስ ባለፈው ሳምንት ባለመግባባት ምርጫ ማድረግ ሳይቻል በተበተነው ስብሰባ ላይ እጁን ሳያወጣ በተደጋጋሚ በመናገር ስብሰባውን በመበጥበጡ፣ ከሁሉም በላይ ግን ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ያላቸውን አጥብቆ ስለሚቃወም፣ በተቃራኒው ሻዕቢያን የሚቃወሙትን ስለሚደግፍ ነበር አቶ ልደቱ በግል ስልክ እየደወሉ ምርጫ ውስጥ እንዳይገባ የቀሰቀሱበት።

ያለፈው ስብሰባ ከተበተነ በኋላ ቴዎድሮስ ሥራ አስፈጻሚ ውስጥ እንዳይመረጥ አቶ ልደቱ ካነጋገሯቸው መካከል ሁለቱ ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት “ቴዎድሮስ ከሰማ የሚዲያ ዘመቻ ስለሚከፍትብን ምሥጢር ይሁን” ሲሉ አቶ ልደቱ መናገራቸውን አመልክተዋል። አቶ ልደቱን በግል ስልካቸው በማግኘት ለማነጋገር ተባባሪያችን ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሣ ምርጫው እየተደረገ ሳለ “diversity (ብዘሃነትን) አትከተሉም” በማለት አስቀድመው ተቃውሞ አሰምተው እንደነበር የተናገሩት የመረጃው ባለቤቶች፣ ስብሰባው ካለቀ በኋላ እንደሰሙት ከሆነ መመረጣቸው ከተነገራቸው መካከል መልቀቂያ ያስገቡም አሉ። (የሕዝቅኤል ተቃውሞ ሰባት አባላት ባሉበት ቡድን ሁለት አማራ እንዴት ይሆናል ከሚል የመነጨ ነው በሚልም ተወስዷል)

ከአቶ ስብሃት ነጋና ከሻዕቢያ ሰዎች ጋር አብረው እንደሚሠሩ፣ በምስራቅ ኢትዮጵያ አቅጣጫ የተጀመሩ ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን ለማስተጓጎልና ጦርነቱን ለማስፋት በግብጽ መሾማቸው የተሰማባቸው ሕዝቅኤል፣ ከሚቀርቧቸው ሰዎች ጋር ሆነው የ-አብሮነት እንደሚፈርስ ስብሰባ በተደረገ በአንድ ቀን ውስጥ መናገራቸው ተሰምቷል።

“እኔና መስፍን አየነው የገባነው ስብስቡን ለማፍረስ ነው” በማለት ፕሮፌሰሩ መናገራቸውን የሰሙት እነ አቶ ስብሃት ነጋ የሚመሩትን ቡድን የሚቃወሙ ሌላኛው የትግራይ ቡድን ደጋፊዎች ሲሆኑ፣ ሕዝቅኤል “አዲስ የተቋቋመ አደረጃጀት አለ። ከአብሮነት ውስጥ የሚፈለጉትን ወደዚያ እንወስዳለን። የ-አብሮነት ነገር አይታመንም። የሌሎችን መብትና ስብጥር አያከብርም” ማለታቸው ታውቋል። እሳቸውንም በግል ስልካቸው ለማግኘት በተደጋጋሚ የተደረገው ሙከራ አልተሳካም።

እነዚሁ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የመረጃ ምንጮች ለተባባሪያችን እንዳሉት ሕዝቅኤል አዲስ እየተመሠረተ ነው ያሉት አደረጃጀት እሳቸው ያሉበት ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ያደራጁትና እነ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ከኋላ የሚመሩት ነው።

ከሃያ አንዱ የቦርድ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ታምራት ላይኔ፣ አስቀድመው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለመሆን ፈቃደኛ ሆነው የነበሩ ቢሆንም፣ በሰላማዊና የትጥቅ ትግል ስልት ላይ ክርከር ከተካሄደ በኋላ በሰኞው ዕለት ምርጫ ርሳቸውን ከሥራ አስፈጻሚነት ተወዳዳሪነት ማግለላቸውን በስብሰባው የተካፈሉ አስታወቀዋል።

የ-አብሮነትን አብረው አጅበው የነበሩት እነ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ኢተና ወዘተ የመሳሰሉት ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ማግለላቸውን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም። ይህም የሆነው በአገር ውስጥ የኦሮሞ ተወላጆች በሰነዘሩባቸው ተቃውሞ መሆኑ አይዘነጋም።

ቡድኑ ሥራ ሲጀምር በአገር ውስጥ የሕቡዕ አደረጃጀት በማስፋፋት የተቃውሞና ዓድማ እንደሚያደራጅ አቶ ልደቱ በተደጋጋሚ መናገራቸው አይዘነጋም። የ-አብሮነት ከአገር ውስጥ አብሮ ካሉ የተወሰኑ ድርጅቶች ጋር እንደሚሠራ፣ አንዳንዶቹም በጅምሩ ወቅት በይፋ በዙም (Zoom) ስብሰባ ይካፈሉ እንደነበር የሚታወስ ነው። (አዲስ ሪፖርተር)

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News, Politics Tagged With: ezikiel gebissa, issac ephraim, lidetu ayalew, operation dismantle tplf, sebhat nega, ye-abronet

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule