በቅርቡ ጃዋር መሐመድን ማረሚያ ቤት ድረስ ሄደው ከጎበኙ መካከል አንደኛው ከጃዋር አንደበት የሰሙትን ማመን እንዳቃታቸው ይገልጻሉ። ጃዋር ያለፈበትን መንገድ እያሰላ በጸጸት ውስጥ ያለ ይመስላል። በአጭር ጉብኝታቸው “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ” በማለት ቅዝዝ ብሎ የነገራቸው ጠያቂው እሱን ከተሰናበቱ በኋላ ነበር ለጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ሁኔታውን ያጫወቱት። ለተለያዩ ሚዲያዎችና በጃዋር ዙሪያ ለነበሩ እንቅስቃሴዎች እንግዳ ያልሆኑት እኚሁ ሰው ለጎልጉል ዘጋቢ መነሻ ሃሳብ ከሰጡ በኋላ ዘጋቢያችን በርካታ መረጃዎችን አሰባስቦ የሚከተለውን ሪፖርት አዘጋጅቷል። በሪፖርቱ አስቀድሞ የተሰባሰቡና ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩ መረጃዎች ተካተዋል። ሪፖርቱ አንባቢያን የራሳቸውን ስሌት እንዲያሰሉና አቅም ያላቸው ይበልጥ ጉዳዩን እንዲያጠኑት የሚያነሳሳ ይሆናል። ጃዋርና “የአንድነት ኃይሎች” የት፣ … [Read more...] about ጃዋር “የአንድነት ኃይሎች ከዱኝ”
yilikal
ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር
በወንጀል ተጠርጣሪ ሃምዛ ቦረና በአቶ ሃምዛ ቦረና መዝገብ የተካተቱ 9 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። መርማሪ ፖሊስ የሰራውን ተጨማሪ የምርመራ ስራ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከዘጠኙ ተጠርጣሪዎች መካከል ስምንቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠባቂዎች ሲሆኑ በፖሊስ ምርመራ ላይ መቃወሚያ አቅርበዋል። መርማሪ ፖሊስ ሌሎች በርካታ የሰዎች እና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሳብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሎ ጠይቋል። ፍርድ ቤት ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ 8 ቀን ፈቅዶ ተለዋጭ ቀጠሮ ለሃምሌ 29/2012 ዓ/ም ሰጥቷል። መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 11 ቀናት፤ በተጠርጣሪዎች ላይ የተያዙ መሳሪያዎችን ምርመራ አድርጓል፤ 10 የተከሳሽ ፤ 20 የምስክር ቃል ተቀብሏል።አንደኛ ተጠርጣሪ አቶ ሃምዛ ቦረና የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ብሄርን ከብሄርና የሃይማኖት ግጭት … [Read more...] about ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር