• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር

July 29, 2020 06:43 pm by Editor Leave a Comment

በወንጀል ተጠርጣሪ ሃምዛ ቦረና

በአቶ ሃምዛ ቦረና መዝገብ የተካተቱ 9 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

መርማሪ ፖሊስ የሰራውን ተጨማሪ የምርመራ ስራ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከዘጠኙ ተጠርጣሪዎች መካከል ስምንቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠባቂዎች ሲሆኑ በፖሊስ ምርመራ ላይ መቃወሚያ አቅርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ ሌሎች በርካታ የሰዎች እና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሳብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሎ ጠይቋል።

ፍርድ ቤት ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ 8 ቀን ፈቅዶ ተለዋጭ ቀጠሮ ለሃምሌ 29/2012 ዓ/ም ሰጥቷል።

መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 11 ቀናት፤

  • በተጠርጣሪዎች ላይ የተያዙ መሳሪያዎችን ምርመራ አድርጓል፤ 10 የተከሳሽ ፤ 20 የምስክር ቃል ተቀብሏል።
  • አንደኛ ተጠርጣሪ አቶ ሃምዛ ቦረና የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ብሄርን ከብሄርና የሃይማኖት ግጭት ያደረጉትን ቅስቀሳ የሚያመላክት የቪድዮ ማስረጃ ሰብስቢያለሁ ብሏል።
  • በተጨማሪ አንደኛ ተጠርጣሪ በኦሮሚያ ተለያዩ ቦታዎች የብሄርና የሃይማኖት መቀስቀሳቸውን የሚያስረዳ የምስክር ማስረጃ አግኝቻለሁ ብሏል።
  • ከሶስተኛ – ስምንተኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች በአ/አ ብቻ 14 ሰዎች እንዲሞቱ ምክንያት መሆናቸው በምስክር ተረጋግጧል። ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙንም ማስረጃ ሰብስቧል። 
  • በተጠርጣሪዎች በተፈፀመ ወንጀል ቡራዩ ላይ 4 ሰዎች ሲሞቱ 4 ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ማስረጃ ሰብስባል፤ ከባድ ጉዳት ያደረሰውን የህክምና ማስረጃ ና ህይወታቸው ያለፉትን ያስክሬን ምርመራ ውጤት የመቀበል ስራ እንደሚቀረው ገልጿል። 
  • ተጠርጣሪዎቹ በሚሰጣቸው ትዕዛዝ ከሰኔ 23ና ሰኔ 24 በፊት በተለያየ ጊዜ በተፈፀመ ወንጀል ሌላ ቅኝት አግኝቻለሁ ብሏል።
  • ሌሎች በርካታ የሰዎች እና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሳብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሏል።

የተጠርጣሪዎች ጠበቃዎች፤

  • ምርመራው ተገቢነት የለውም ብለዋል። የሚቀርበው ምክንያት ተጨማሪ ጊዜ የሚያሰጥ አይደለም ብለዋል።
  • በእጃቸው ተገኘ የተባለው መሳሪያ በየጊዜው የቁጥር ስህተት በመርማሪ ፖሊስ እየቀረበ ነው ግልፅ አይደለም ብለዋል።
  • 4 ተጠርጣሪዎች ከሌሎች ታሳሪዎች ባተለየ ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ ተደርጓል፤ በስልክ ቤተሰብ ማግኘት አልቻሉም ብለው አቤቱታ አቅርበዋል።
  • አንድ ተጠርጣሪ በተለይ የልጆች አባት በመሆኑ ልጆቹ በኪራይ ቤት እንደሆኑና የሚበሉትና ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ በስልክ መገናኘት አልቻልኩም ሲል አቤቱታ አስመዝግባል።
  • አቶ ሃምዛ ቦረና አክቲቪስትና ጋዜጠኛ ሆኜ በውጭ ሀገር ስኖር ነበር ለውጥ መጣ መባሉን ሰምቼ ወደሀገር ውስጥ የመጣሁት
  • የተለያዩ ሚዲያዎችን ተጠቅሜ ህገመንግስታዊ መብቴን ተጠቅሜ ራሴ ያመንኩበትን ሃሳብ ገልጫለሁ ከዚህ ወንጀል ጋር የሚያገናኘን ነገር የለም ሲሉ ተቃውመዋል።
  • አቶ ሃምዛ አካውንታቸው መታገዱን በመንግስት ግብርን እንድከፍልም ህጋዊ ውክልና ይሰጠኝ ሲሉ አቤቱታ አስመዝግበዋል።

ፍርድ ቤት፤

  • ተጠርጣሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገኛኙ (በስልክም ቢሆን እንዲገናኙ) ትዕዛዝ ሰጥቷል። 
  • አንደኛ ተጠርጣሪ ህጋዊ ውክልና የሚያገኙበትን /የሚሰጡበት መንገድ እንዲመቻችላቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል።
  • የምርመራው ሂደት ሰፊና ውስብስብ በመሆኑ ተጨማሪ 8 ቀን ፈቅዷል።

በወንጀል ተጠርጣሪ የህወሓት አመራሮች

ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ የሽብር ቡድኖች መረጃ አሳልፎ በመስጠት ወንጀል ተጠርጥረዋል ያለው ፖሊስ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ የጠየቀባቸው የህወሓት የአዲስ አበባ አገናኝ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወልደ ገብረፃዲያ፣ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሕግ እና ፍትህ ምርምር ተቋም ዳይሬክተር አቶ ተስፋአለም ይህደጎና ሌሎች ሁለት ሹፌሮች ናቸው።

ፖሊስ ዛሬ (ረቡዕ) ለፍርድ ቤት ባቀረበው ሪፖርት የባንክ ሂሳባቸውን እያስመረመርኩ ነው፣ በአቶ ተስፋአለም ቤት የተገኘው ክላሽ ህጋዊ ፍቃድ የለውም የሚል ሃሳብ አቅርቧል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ፖሊስ እስካሁን የሰራቸው ስራ የሚያሳይ ዝርዝር መዝገብ ይዞ አልቀረበም ስለዚህ ደንበኞቻችን በነፃ ሊሰናበቱ ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል።

ችሎቱ ለምን የምርመራ መዝገቡን ይዞ እንዳልቀረበ የጠየቀ ሲሆን ለሐምሌ 23 መዝገቡን ይዞ እንዲቀርብና የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ይሰጥ አይሰጥ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

በወንጀል ተጠርጣሪ ይልቃል ጌትነት

የዛሬው ቀጠሮ መርማሪ ፖሊስ ባለፈው በነበረው ቀጠሮ ተጠርጣሪዎችን ከወንጀሉ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለብቻ ነጥሎ ለማቅረብና የደረሰበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለፍርድ ቤት ለማሳወቅ ነው።

መርማሪ ፖሊስ ሰራኋቸው ያለው ስራ፤

  • ተጨማሪ ምስክሮችን ሰምቻለሁ፣ከወንጀሉ ጋር የተያዙ እቃዎቻቸውን ለምርመራ ለፌደራል ፖሊስና ለብሄራዊ ደህንነት ልኪያለሁ ውጤት እየጠበኩ ነው ብሏል።
  • የንብረት ግምት እንዲላክ ፣ የአስክሬን ምርመራ ሪፖርት እንዲላክልኝ ለሚመለከታቸው አካላት ልኬአለሁ ብሏል ፤ እነዚህ ስራዎች ስለሚቀሩኝ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሏል።

የአቶ ይልቃል ጠበቃ አዲሱ ጌታነህ፤

  • አቶ ይልቃል ከወንጀል ጋር ያላቸው ግንኙነት፣ በምን ሁኔታ፣ እንዴትና መቼ እንደተፈፀመ ፖሊስ እንዲያቀርብ ነበር የታዘዘው።
  • የ14 ሰው ህይወት አልፏል ለዛም ውጤት እጠብቃለሁ፣
  • ንብረት ወድሟል ከማለት ያለፈ ተለይቶ የተሳትፎ ደረጃቸው ስላልተገለፀ ለ27 ቀናት በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ሲያደርግ ነበር ተጨማሪ ጊዜ አያስፈልግም መዝገቡ ተዘግቶ በነፃ ይለቀቁ ብለዋል።

ፍርድ ቤት፤

  • የተጠርጣሪ ጠበቃን አቤቱታ ሰምቶ ፣ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀውን ጥያቄ ተመልክቶ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ  አስፈላጊነው፣ አይደለም የሚለውን ለመወሰን ለሐምሌ 24 ቀጠሮ ሰጥቷል።

በወንጀል ተጠርጣሪ እስክንድር ነጋ

የዛሬው (ሃምሌ 22/2012 ዓ/ም) መዝገብ የተቀጠረበት ጉዳይ ፖሊስ ምርመራ አልጨረስኩም ብሎ ፍርድ ቤትን በማስፈቀዱ የደረሰበትን የምርመራ ደረጃ ለማየት ነበር።

መርማሪ ፖሊስ፤

  • አሁንም ምስክሮችን እየሰማሁ ነው፤ በአዲስ አበባ ከተማ የደረሰውን ጉዳት የ6 ክፍለ ከተማ ነው የመጣልኝ የሌሎች ክፍለ ከተሞች እየተጣራ በመሆኑ እስካሁን አልደረሰልኝም።
  • አሁንም የምንይዛቸው አባሪዎች አሉን፣ የኤሌክትሮኒክስ ማስረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት ልከናል።
  • አቶ እስክንድር ነጋ በሚያዝበት ጊዜ ላፕቶፕ እንዲሁም ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮቻቸውን ልንይዝ አልቻልንም ይህ አፈላልገን ለመያዝ የጊዜ ቀጠሮ ያስፈልገናል።

የእስክንድር ነጋ ጠበቆች፤

  • ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠን ብሎ የጠየቃቸው ምክንያቶች በሙሉ በመጀመሪያው ቀን የቀረቡ ናቸው።
  • ፖሊስ ስራውን እየሰራ አይደለም።
  • በዚህ መካከል አቶ እስክንድር አላግባብ ታስረዋል።
  • ከመንግስት እና ለመንግስት ቅርበት ካላቸው ሚዲያዎች ውጭ ችሎት እንዳይገቡ መደረጉ ተገቢ አይደለም ብለዋል።

ፍርድ ቤቱ ሚዲያዎችን በሚመለከት የእስክንድር ጠበቆች አቤት ያሉትን ተመልክቶ ፍርድ ቤቱ ይህ ትክክል አይደለም፤ ፖሊስ ሁሉንም ጋዜጠኞች ማስገባት አለበት ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።

እስክንድር ነጋ በዚህ ጉዳይ እኛ የምንፈልገው የህዝብ ፍትህ ስለሆነ ጋዜጠኞች በነፃነት ገብተው መዘገብ አለባቸው ብሏል።

ፍርድ ቤት፤

ፍርድ ቤቱ ግራና ቀኙን ተመልክቶ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ ውድቅ በማድረግ 9 ቀን ፈቅዶ ለነሃሴ 1/2012 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

(ፋና ብሮድካስት፣ ዶቼቨለ እና ሌሎች ሚዲያ የተሰበሰበ መረጃ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Law, Left Column Tagged With: chilot, eskinder, hamza, jawar massacre, tesfalem, tplf, yilikal, ችሎት

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule