ባለፈው ሳምንት ሰኞ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. አሥር የተለያዩ ክሶች የተመሠረተባቸው አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 24 ተከሳሾች ክሱ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 ድንጋጌ መሠረት የተሰጣቸው ቢሆንም፣ በሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 129 ድንጋጌ መሠረት ክሱ ለተከሳሾቹ በችሎት መነበብ ስላለበት፣ በችሎት ለማንበብ ለመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጣቸው። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾን ለመስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፣ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ያልቀረቡ ተከሳሾችን የፌዴራል ፖሊስ እንዲያቀርብና ክስ እንዲነበብላቸው የነበረ ቢሆንም ሳያቀርብ ቀርቷል። በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ አምስተኛ ተከሳሽ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ 14ኛ ተከሳሽና በአሜሪካ አገር ነዋሪ የሆኑት አቶ ብርሃነ መስቀል አበበና አውስትራሊያ እንደሚኖሩ የሚነገረው አቶ ፀጋዬ … [Read more...] about ለተከሳሽ ጃዋርና ግብረአበሮቹ “ማንኛውም ሰው በሕግ ፊት እኩል ነው” የሚል ምላሽ ተሰጠ
hamza
ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ወደ እስር ቤት እንዲዛወሩ ታዘዘ
ባለፈው ሰኞ በዋለው ችሎት እነ ጃዋር ሲራጅ መሐመድ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት የክስ ፋይላቸው መቀየሩ ተዘግቦ ነበር። የዚያን ዕለት የቀረበባቸውም ክስ ሃይማኖትና ብሔርን መሠረት በማድረግ፣ በተለይም በአማራ ብሔር ተወላጆችና በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም የተለያዩ መገናኛ ብዙኃንና የትስስር ድረ ገጾችን በመጠቀምና በአካል በመገኘት፣ በተገለጸው አግባብ ባስነሱት የእርስ በርስ ግጭት በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች የ13 ሰው ሕይወት እንዲያልፍና 48,026,526 ብር የሚገመት ንብረት እንዲወድም አድርገዋል፣ በኦሮሚያ በተለያዩ ዞኖችና ከተሞች የ167 ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ፣ 360 ሰዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸውና 4,673,031,142 ብር ግምት ያለው ንብረት እንዲወድም ማድረጋቸውን በመጥቀስ ነበር ዐቃቤ ሕግ ክሱን … [Read more...] about ተከሳሾቹ እነ ጃዋር ወደ እስር ቤት እንዲዛወሩ ታዘዘ
“በርቱ አገሪቱ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጋችሁ አድርጉ” ጃዋርና ግብረአበሮቹ
የእርስ በርስ ጦርነት በማስነሳት፣ የሽብር ወንጀል ለመፈጸም በማቀድና በመዘጋጀት፣ እንዲሁም የፀና ፈቃድ የሌለው የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተመሠረተባቸው 24 ተከሳሾች አንዱ ጃዋር መሐመድ፣ እሱን ጨምሮ እስክንድር ነጋና ልደቱ አያሌው የተከሰሱት መንግሥት በምርጫ ያሸንፋሉ የሚል ሥጋት ስላለው እንጂ ወንጀል ፈጽመው አለመሆኑን ለፍርድ ቤት ተናገረ። ጃዋር ይኼንን የተናገረው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመዝገብ ቁጥር 260215 መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም. የከፈተውን ክስ፣ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ለተከሳሾች ሲሰጣቸው ነው። በሽብርተኝነት ሲከሰስ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን በማስታወስ የመጀመርያው በኢሕአዴግ ሥርዓት ውስጥ የቀረበበት ክስ ሲሆን፣ ሁለተኛው አሁን የተከሰሰበት መሆኑን ጠቁሞ፣ በዚህም ኩራት እንደሚሰማው … [Read more...] about “በርቱ አገሪቱ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጋችሁ አድርጉ” ጃዋርና ግብረአበሮቹ
ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር
በወንጀል ተጠርጣሪ ሃምዛ ቦረና በአቶ ሃምዛ ቦረና መዝገብ የተካተቱ 9 ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። መርማሪ ፖሊስ የሰራውን ተጨማሪ የምርመራ ስራ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከዘጠኙ ተጠርጣሪዎች መካከል ስምንቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ ጠባቂዎች ሲሆኑ በፖሊስ ምርመራ ላይ መቃወሚያ አቅርበዋል። መርማሪ ፖሊስ ሌሎች በርካታ የሰዎች እና የሰነድ ማስረጃ ለማሰባሳብ ተጨማሪ 14 ቀን ይሰጠኝ ብሎ ጠይቋል። ፍርድ ቤት ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ 8 ቀን ፈቅዶ ተለዋጭ ቀጠሮ ለሃምሌ 29/2012 ዓ/ም ሰጥቷል። መርማሪ ፖሊስ ባለፉት 11 ቀናት፤ በተጠርጣሪዎች ላይ የተያዙ መሳሪያዎችን ምርመራ አድርጓል፤ 10 የተከሳሽ ፤ 20 የምስክር ቃል ተቀብሏል።አንደኛ ተጠርጣሪ አቶ ሃምዛ ቦረና የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ብሄርን ከብሄርና የሃይማኖት ግጭት … [Read more...] about ችሎት! ሃምዛ፣ የህወሓት አመራሮች፣ ይልቃልና እስክንድር