ባለፈው ሳምንት ሰኞ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. አሥር የተለያዩ ክሶች የተመሠረተባቸው አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 24 ተከሳሾች ክሱ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 ድንጋጌ መሠረት የተሰጣቸው ቢሆንም፣ በሥነ ሥርዓት ሕጉ አንቀጽ 129 ድንጋጌ መሠረት ክሱ ለተከሳሾቹ በችሎት መነበብ ስላለበት፣ በችሎት ለማንበብ ለመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጣቸው። ፍርድ ቤቱ ተከሳሾን ለመስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፣ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ያልቀረቡ ተከሳሾችን የፌዴራል ፖሊስ እንዲያቀርብና ክስ እንዲነበብላቸው የነበረ ቢሆንም ሳያቀርብ ቀርቷል። በእነ አቶ ጃዋር የክስ መዝገብ አምስተኛ ተከሳሽ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ 14ኛ ተከሳሽና በአሜሪካ አገር ነዋሪ የሆኑት አቶ ብርሃነ መስቀል አበበና አውስትራሊያ እንደሚኖሩ የሚነገረው አቶ ፀጋዬ … [Read more...] about ለተከሳሽ ጃዋርና ግብረአበሮቹ “ማንኛውም ሰው በሕግ ፊት እኩል ነው” የሚል ምላሽ ተሰጠ
tsgaye ararssa
“በርቱ አገሪቱ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጋችሁ አድርጉ” ጃዋርና ግብረአበሮቹ
የእርስ በርስ ጦርነት በማስነሳት፣ የሽብር ወንጀል ለመፈጸም በማቀድና በመዘጋጀት፣ እንዲሁም የፀና ፈቃድ የሌለው የጦር መሣሪያ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተመሠረተባቸው 24 ተከሳሾች አንዱ ጃዋር መሐመድ፣ እሱን ጨምሮ እስክንድር ነጋና ልደቱ አያሌው የተከሰሱት መንግሥት በምርጫ ያሸንፋሉ የሚል ሥጋት ስላለው እንጂ ወንጀል ፈጽመው አለመሆኑን ለፍርድ ቤት ተናገረ። ጃዋር ይኼንን የተናገረው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በመዝገብ ቁጥር 260215 መስከረም 6 ቀን 2013 ዓ.ም. የከፈተውን ክስ፣ መስከረም 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ለተከሳሾች ሲሰጣቸው ነው። በሽብርተኝነት ሲከሰስ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን በማስታወስ የመጀመርያው በኢሕአዴግ ሥርዓት ውስጥ የቀረበበት ክስ ሲሆን፣ ሁለተኛው አሁን የተከሰሰበት መሆኑን ጠቁሞ፣ በዚህም ኩራት እንደሚሰማው … [Read more...] about “በርቱ አገሪቱ የቄሮ በመሆኗ እንደፈለጋችሁ አድርጉ” ጃዋርና ግብረአበሮቹ