• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ልደቱ አያሌውን ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት

September 13, 2021 11:23 am by Editor Leave a Comment

አቶ ልደቱ አያሌው የፖለቲካ ህይወቱን አሀዱ ብሎ የጀመረው 1983ዓ.ም. ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ የከተማዋን ወጣቶች የማደራጀት ስራ ላይ ከተሰማሩ ወጣቶች አንዱ ሆኖ ነው። በዚያ ወቅት ወጣቱ ልደቱ ለወያኔ መንግስት የመወገን ጫና በነበረበት የወጣት ማህበር ምስረታ ሂደት ንቁ ተዋናይ ነበረ። በመሆኑም የማህበሩ ሊቀመንበር የመሆን ፍላጎት እንደነበረው በወቅቱ አብረውት የነበሩ የመሰከሩት ነገር ነው። ነገር ግን በ1990 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በይፋ ሲመሰረት ወጣቱን በማደራጀት ምንም ተሳትፎ ያልነበረው የዳዊት ዮሃንስ (አፈጉባዔ የነበረ) ሚስት ወንድም የሆነው ወጣት ታጠቅ ካሳ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ።

ይሄኔ ነው እንግድህ የልደቱ የመጀመሪያው የፖለቲካ አቋም እጥፋት የተጀመረው። የታጠቅን በሊቀመንበርነት መመረጥ አሚን ብሎ መቀበል አልፈለገም። የተመሰረተው ማህበር ግን እንደታሰበው ከፖለቲካ ፓርቲዎች ገለልተኛ እንደማይሆን እና ይልቁንም የኢህአዴግ የወጣት ክንፍ ሊባል የሚችል ነው። ያዛኔው ልደቱን ያበሳጨው ጉዳይ የወያኔ አገልጋይ ለመሆን አለመታመኑ ብቻ ነው። በመሆኑም ቀጥሎ የሄደው አዲስ ወደ ተመሰረተው የፕ/ር አስራት ወልደየስ ፓርቲ መአሕድ ነው። ልደቱ በይፋ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ሆኖ ሲወጣ ኃላፊነቱን የጀመረው በተመሳሳይ የመአሕድ ወጣት ክንፍ አመራርነትን ሲቀላቀል ነው።

ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ጥሎ ወጥቶ እስከ አሁን ድረስ የሚመራውን የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን (ኢዴፓ) መሠረተ። ፓርቲው በታሪካዊው ምርጫ-97 ወቅት ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ የተባለውን ዋነኛ የተቃዋሚ ጎራ ከመሰረቱት አምስት ድርጅቶች አንዱ ነበር። በቅድመ-ምርጫ የክርክር መድረኮች ላይ አንደበተ-ርቱዕው ልደቱ አያሌው በተለየ ሁኔታ ጎልቶ ወጣ። ከአዲስ አበባ አልፎ የወጣቱ ፖለቲከኛ ስምና ዝና በመላ ኢትዮጵያ ገነነ።

ሆኖም ግን መጨረሻው እንደታሰበው ሳይሆን ቀርቶ የድህረ-ምርጫ ኩነቶች በህዝባዊ አመፅ እና የመንግስት የፀጥታ ኃይል በወሰዳቸው ዘግናኝ እርምጃዎች በውዝግብ የተሞላ ሆነ። ከዚህ ሂደት ጋር በተያያዘ የቅንጅት አመራር ከፍተኛ ጫና ውስጥ ገብቶ ተከፋፈለ። አብዛኛዎቹ የምርጫውን ውጤት ባለመቀበል ፓርላማ ላለመግባት ከህዝብ የተደረገባቸው ግፊት ተቀብለው አሻፈረን ሲሉ አቶ ልደቱ የቅንጅትን ማህተም ይዞ በተቃራኒዉ ቆሞ። ይሄን የቅንጅት አመራር አቋም ተከትሎ ፓርላማ አልገባም ያሉት ወደ ማረሚያ ቤት ሲላኩ አቶ ልደቱ ከተራው የድርጅቱ ተመራጮች ጋር ፓርላማ ገባ።

የቅንጅት መፍረስ እስከ አሁን አነጋጋሪ እና የአቶ ልደቱን የፖለቲካ ስብዕና የቀበረ ሆኖ በማለፉ ሁኔታውን ለኢትዮጵያ ህዝብ ካላስረዳሁ በማለት ዛሬም ላይ ታች ሲል ይታያል። ቅንጅቱን በመበተኑ የማን ሚና የጎላ ነበር? ለሚለው ጥያቄ ህዝብ በአገኘው መረጃ ልክ ብያኔ ሰጥቶበት ያለፈው ምናልባትም በሀገራችን ታሪክ ከፍተኛ የህዝብ ትኩረት አግኝቶ የነበረ ክስተት ነው። ቢሆንም ልደቱ እስከ ዓለም ፍጻሜ የእርሱን “እውነት” ለማወቅ የምንጨነቅ የሚመስለው ለምንድን ነው? መጻሕፍት ጽፎ፣ መቶ መግለጫ ሰጥቶ ወዘተ እውነቱን ያስረዳ ካልመሰለው እስኪ ምናልባት እነዚህ ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት።

ይሆናል 1፤ ምናልባት የምታስረዳው “እውነት” የለ ይሆናል፤ ወይም ከሌላ አንጻር ቆመው ሲያዩት የሚጠቅም ታሪክ እና እውነት አይደለም ይሆናል። እርግጠኝነትህን ተጠራጠረው።

ይሆናል 2፤ “እውነቱ” ባንተ ብቃት/ቁመና ሊገለጽ፣ ሊሰበክ የማይችል ሆኖ ይሆናል። እስቲ ሌሎች ይህንን እውነት እንዲያስረዱት ተውላቸው። መለኮታዊ ተልእኮ ተሰጥቶህ እንኳን ቢሆን ለላከህ አካል “አልቻልኩም፣ አልሰሙኝም” ብለህ ንገረው። ነቢያት አድርገውታል።

ይሆናል 3፤ እንዲሰሙህና እንዲለወጡ የምትፈልጋቸው ሰዎች ያንተን “እውነት” ለመስማት ወይም/እና ለመቀበል አይፈልጉ ወይም አልበቁ ይሆናል። ተዋቸው። ግዴታ አታድርግባቸው። ያንተን እውነት ማወቅም ሆነ መቀበል አንተ የምታስበውን ያህል ጠቃሚ ላይሆን ይችላል። አይደለምም።

ይሆናል 4፤ ሕይወትህን ወይም ትርጉሟን በአንድ ያንተ እውነት ላይ ብቻ አንጠልጥለሃት፣ እረፍት ነስቶህ ይሆናል። የፖለቲካም ሆነ ሌላ ሕይወትህን (ወይም ትርጉሙን) ከዚህ ከምትለው እውነት/ትርክት ለማፋታት ሞክር። ሌላው ቀርቶ፣ የፖለቲካ ሕይወትንም ጭምር ከዚህ ከምትለው “እውነት” ውጭ እንደ አዲስ ልትገነባ ትችላለህ፤ ከፈለግህ። እውነት የምትለው ጉዳይ/ትርክት እስረኛ አትሁን። ራስህን ፍታ።

ይሆናል 5፤ ፖለቲካ ጨዋታ መሆኑን ረስተኸው ይሆናል። በማንኛውም ጨዋታ መብለጥ፣ መበለጥ ያለ ነው። አንድ ግጥሚያ በፍትሕ በርትእ ይዳኝም አይዳኝም አጠቃላይ ጨዋታው ይቀጥላል። ያለፈውን ግጥሚያ ወደኋላ ተመልሶ መቀየር አይቻልም። ስላለፈው ግጥሚያ ስሕተቶች ያልካቸውን ለማስረዳት ሞክረሃል። ከዚያ በላይ ማድረግ አትችልም። ጨዋታው ካንተ የግል ውጤትና ስሜት ይበልጣልና መቀጠሉ አይቀርም። ወደ ጨዋታው ተመለስ፤ ወይም ጨዋታ ቀይር፤ ወይም ጨዋታ ተው።

ይሆናል 6፤ ስፖርተኛ ሆነህ ከተጎዳህ ቢያንስ ሕመምህ እስኪድን ጉዳት ካደረሰብህ ጨዋታ ማረፍ አለብህ። አንተ ከፖለቲካ በቂ እረፍት ሳትወስድ እየተመላለስክ ሕመምህ እንዳይሽር አድርገኸው ይሆናል። ካስቻለህ በቂ እረፍት አድርግ። ካላስቻለህ፣ ለቅሶህን አቁመህ፣ ወደምትወደውና ወደምትችለው የፓርቲ ፖለቲካ በቀጥታ ግባ። አለዚያም ከፓርቲ ፖለቲካ ውጭ ባለ መድረክ ለምሳሌ ትንተና ወደ መስጠት፥ ወደ ማጥናት ወዘተ ዙር። በአንድ ነጠላ ጉዳይ ላይ ጊዜህን፣ ስሜትህን እና አቅምህን አታባክን።

ነገሩ እንዲህ ነው።

(ይህን አስተያየቴን የሆነ ባንተ ላይ የተሸረበ ሴራ አካል አድርገህ እንደማታየው ተስፋ አደርጋለሁ። ያው ተስፋ ነው።)

መስፍን ነጋሽ፤ 10 Oct 2018 የተፃፈ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Filed Under: Opinions, Right Column Tagged With: lidetu ayalew, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule