ጃዋር የኦነግን ባንዲራ መጠቀሙ ሕገወጥ ነው ሲል የዳውድ ኦነግ ከሰሰ
ዳውድ ኢብሳ የሚመራው አንዱ ኦነግ ጃዋር መሐመድ ገለቶማ በሚለው የአውሮጳና የአሜሪካ ስብሰባ ላይ የኦነግን ባንዲራ መጠቀሙን ኮነነ። ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይጠቀም ትዕዛዝ አዘል ደብዳቤ ለኦፌኮ ጻፈ።
በዳውድ ኢብሳ የሚመራውና በምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተብሎ የተመዘገው ፓርቲ ባንዲራዬን ጃዋር መሐመድ በሕገወጥ መንገድ እየተጠቀመ ነው ሲል መረራ ጉዲና ለሚመራው ኦፌኮ ቅሬታውን አሰምቷል።
ከሁለት ቀናት በፊት በተጻፈውና በዳውድ ኢብሳ በተፈረመው ደብዳቤ ጉዳዩ በሚለው ርዕስ ሥር በሕጋዊ መልኩ በምርጫ ቦርድ የተመዘገበውን የኦነግን ባንዲራ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር ጃዋር መሐመድ በሕገወጥ መልኩ መጠቀሙን ስለማስቆም የሚል ነው።
ደብዳቤው ሲያጠናቅቅም ከረር ያለ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፤ ይህ ደብዳቤ ከደረሳችሁ ቀን ጀምሮ አቶ ጃዋር የኦነግን ባንዲራ ከመጠቀም እንደምታስቆሙት፣ ጥያቄያችንን በተግባር ፈጽማችሁ እንደምታስታውቁን እናምናለን፤ ተስፋም እናደርጋለን ይላል።
የሸኔን አሸባሪ ተግባር ከውጭ በገንዘብም ሆነ በማስተባበርና በፕሮፓጋንዳ የሚረዱት እነ ጸጋዬ አራርሳ ከጃዋር ጋር ሆድና ጀርባ መሆናቸውን ተከትሎ ይህ ደብዳቤ መውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
የጃዋር የምስጋና ገለቶማ ጉዞ ገና ከመጀመሩ ይህ ዕንቅፋት መደንቀሩ ጉዞውንና ስብሰባዎቹን ወዴት አቅጣጫ እንደሚወስዳቸው በቀናት ውስጥ የሚታይ ነው። ሆኖም ግን ይህ የኦነግ ማስጠንቀቂያ ጃዋር በክፍሉ ውስጥ የሰቀለውን የሚጠቀልል መሆን አለመሆኑን ባይጠቁምም የዳውድ ኦነግ ግን ከእንግዲህ ባንዲራውን ማንም በምንም መልኩ እንዳይጠቀም ማስደረግ አለበት የሚሉ ኃይሎች ደብዳቤውን ደግፈው አስተያየት ሲሰጡ ተሰምተዋል።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ኦፌኮ ለደብዳቤው ምላሽ አልሰጠም።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
gi haile says
ለካስ ጀዋር ሆሮሞ አይደለም በኦነጉ መሪ? ታዲያ ኦሮሞ ነፃ ኣውጭ ብሎ እራሱን የሰየመው የሆሮሞ ነፃ ኣውጪ መሪ በኦነግ ባንዲራ ሰበብ ጀዋርን መኮነኑ ኦነግ ለሆሮሞ ሕዝብ የቆመ ሳይሆን ለባንዲራው ነው ማለት ነው። ጀዋር የሆሮሞ ተወላጅና ኦሮሞ ከሆነ ባንዲራው የሆሮሞን ሕዝብ ይወክላል ካለ የኦፌኮ መሪ ባንዲራውን ቢይዘውና ስብሰባ ቢያደርግ ሆሮሞው ጀዋርን ስብሰባ ቢጠራው ዳውድ ኢብሳ የፈሩት ባንዲራውን ጀዋር ይቀይራል ብለው ነው ወይስ የኦነግ ባንዲራ የንጉስ ዳውድ ኢብሳ የንግስና ኣርማቸው ነውና ከኔ በቀር ማንም በዚህ ባንዲራ ስር አይሰብሰብ የተባለ ይመስላል። ለማንኛውም 90%የሆሮሞ ሕዝብ ኦነግ ምን እንደደረገለት ቢጠየቅ ኣለ እንዴ? ከማለት ይልቅ የተሰራ ነገር ለሕዝቡ ኣለመኖሩን የሆሮሞ ሕዝብ ያውቀዋል። የዳውድ ኢብሳ ፍራቻ ያለችን ሁሉ ይቀሙኛል ብሎ ፈርቶ ከሆነ ከድጡ ወደ ማጡ መግባታቸውና የመጨረሻው የውድቀት ደረጃ ላይ መሆናቸውን ያሳያል።
Somer Hamera says
ባንድራ መያዝ ማለት በራሱ ትርጉሙ ምንድን ታውቃላችሁ? እውቅና ሰጪው ምርጫ ቦርድስ ምን እያደረገ እንዳለ ያውቃል ወይ? እኔን የሚያሳስበኝ ይሄ ነው? የትጥቅ ትግልን ባንዲራ ሕጋዊነት ማረጋገጥ የለየለት የሀገር ክህደት ነው።