ጃዋር የኦነግን ባንዲራ መጠቀሙ ሕገወጥ ነው ሲል የዳውድ ኦነግ ከሰሰ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው አንዱ ኦነግ ጃዋር መሐመድ ገለቶማ በሚለው የአውሮጳና የአሜሪካ ስብሰባ ላይ የኦነግን ባንዲራ መጠቀሙን ኮነነ። ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይጠቀም ትዕዛዝ አዘል ደብዳቤ ለኦፌኮ ጻፈ። በዳውድ ኢብሳ የሚመራውና በምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተብሎ የተመዘገው ፓርቲ ባንዲራዬን ጃዋር መሐመድ በሕገወጥ መንገድ እየተጠቀመ ነው ሲል መረራ ጉዲና ለሚመራው ኦፌኮ ቅሬታውን አሰምቷል። ከሁለት ቀናት በፊት በተጻፈውና በዳውድ ኢብሳ በተፈረመው ደብዳቤ ጉዳዩ በሚለው ርዕስ ሥር በሕጋዊ መልኩ በምርጫ ቦርድ የተመዘገበውን የኦነግን ባንዲራ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር ጃዋር መሐመድ በሕገወጥ መልኩ መጠቀሙን ስለማስቆም የሚል ነው። ደብዳቤው ሲያጠናቅቅም ከረር ያለ ማስጠንቀቂያ … [Read more...] about ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት
daud ibssa
ኦነግ በኦነግ ላይ ዕርምጃ ሊወስድ ነው
የትኛው ኦነግ ስለየትኛው ኦነግ መግለጫም ይሁን ተቃውሞ እንደሚሰጥ ግራ እስኪያጋባ የደረሰው ዕድሜ ጠገቡ ኦነግ ተከፋፍሎ አላልቅ ብሎ አሁን ደግሞ አንዱ በአንዱ ላይ ዕርምጃ እወስዳለሁ እያለ ነው። ኢትዮ ኤፍ ኤም ያጠናከረው ዘገባ እንዲህ ይነበባል። ኦነግ ከፖርቲው ህግና ስርአት ባፈነገጠ መልኩ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን አሳሳች መግለጫዎችን ሲሰጡ በነበሩ አመራሮቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ። የኦነግ ቃላ አቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የተወሰኑ ሰዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በመቅረብ አላስፈላጊ መግለጫዎችንና መልዕክት በማስተላለፋቸው ምክንያት በተፈጠረ ውዝግብ ላይ ብሔራዊ ምክር ቤቱ በጠቅላላ ጉባኤ በዲሲፕሊን እንዲጠየቁ የሚያስችል ውይይት ማድረጉን ተናግረዋል። በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በአመራሮች መካከል የርዕዮተ አለም ልዩነት እንዳለ … [Read more...] about ኦነግ በኦነግ ላይ ዕርምጃ ሊወስድ ነው
የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል
ኦነግ አወዛጋቢ ማንነቱና ያልረጋ የፖለቲካ ሩጫው ዛሬም መነጋገሪያ ሆኗል። ቀደም ሲል ለኦሮሞ ትግል እንደ አንድ ብቸኛና ልዩ ምልክት ተደርጎ የተወሰደው ኦነግ በአራት ጎራ ተከፍሎ ቢቆይም አገር ቤት ከገባ በኋላ አንድ መሆን አልቻለም። በኤርትራ በረሃ እያለ እርስበርስ ጎራ ለይቶ በጥይት የተጫረሰው ኦነግ፣ በአውሮፓና በአሜሪካ ባሉ የተለያዩ አመራሮቹ የስልጣን ሽኩቻ አንድ መሆን አቅቶት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት አስቆጥሮ አሁን አገሪቱ ውስጥ በተፈጠረው የፖለቲካ ለውጥ ሁሉም አካላት ወደ አገር ቤት ቢገቡም ልዩነታቸውን ማስወገድ አልቻሉም። ዳውድ ኢብሣ (ፍሬው ማሾ)፣ አባ ነጋ፣ ገላሳ ዲልቦና ጄኔራል ከማል ገልቹ የተቀራመቱት ኦነግ አራት መልክ ይዞ ወደ አገር ቤት ሲገባ ሕዝብ ጥያቄ ያነሳው “ለምን አንድ አትሆኑም? አንድ ሁኑና ኑ” የሚል ነበር። እነዚህ አራት ክንፎች እንኳን … [Read more...] about የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል