ኦነግ አወዛጋቢ ማንነቱና ያልረጋ የፖለቲካ ሩጫው ዛሬም መነጋገሪያ ሆኗል። ቀደም ሲል ለኦሮሞ ትግል እንደ አንድ ብቸኛና ልዩ ምልክት ተደርጎ የተወሰደው ኦነግ በአራት ጎራ ተከፍሎ ቢቆይም አገር ቤት ከገባ በኋላ አንድ መሆን አልቻለም። በኤርትራ በረሃ እያለ እርስበርስ ጎራ ለይቶ በጥይት የተጫረሰው ኦነግ፣ በአውሮፓና በአሜሪካ ባሉ የተለያዩ አመራሮቹ የስልጣን ሽኩቻ አንድ መሆን አቅቶት ሁለት ዐሥርተ ዓመታት አስቆጥሮ አሁን አገሪቱ ውስጥ በተፈጠረው የፖለቲካ ለውጥ ሁሉም አካላት ወደ አገር ቤት ቢገቡም ልዩነታቸውን ማስወገድ አልቻሉም። ዳውድ ኢብሣ (ፍሬው ማሾ)፣ አባ ነጋ፣ ገላሳ ዲልቦና ጄኔራል ከማል ገልቹ የተቀራመቱት ኦነግ አራት መልክ ይዞ ወደ አገር ቤት ሲገባ ሕዝብ ጥያቄ ያነሳው “ለምን አንድ አትሆኑም? አንድ ሁኑና ኑ” የሚል ነበር። እነዚህ አራት ክንፎች እንኳን … [Read more...] about የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል