መሃል ሰፋሪ አሊያም ገለልተኛ ይመስል የነበረው የኦሮሞ አክቲቪስቶች በሙሉ የጃዋር ግልገል መሆናቸው የምታውቀው፤ ልክ እንደ አይን-አፋር ሴት እየተቅለሰለሱ፣ እንደ ሽምግሌ ምሳሌ እያበዙ ከሄዱ በኋላ በማጠቃለያው ላይ “ጃዋር መሃመድ በይቅርታ ከእስር ቢፈታ ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማል!” ሲሉ ነው። በእርግጥ በእስር ላይ ያለ ሰው እንዲፈታ ማሰብ፣ አማላጅ መላክ ወይም Lobby ማድረግ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር ውስጥ የተለመደ ነው። በዚህ ረገድ በሰኔ15ቱ ግድያ ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች መፈታታቸው በተደጋጋሚ እንደ ማሳያ ተጠቅሷል። ነገር ግን በሰኔ 15ቱ ግድያ የተሳተፉ አካላት በስልጣን ሽኩቻና አለመግባባት ምክንያት የተፈጠረ ነው። በዚህ ምክንያት የተጎዱ ሰዎች መኖራቸው እርግጥ ነው። ነገር ግን በአማራ ክልል የሚገኙ አማራዎችን ወይም ሙስሊሞችን ለማጥፋት ታቅዶ የተፈፀመ … [Read more...] about ይቅርታና ምህረት አድራጊው ይወገዳል! የተደረገለትም ይሞታል!
jawar
እነ ጃዋር መሐመድና ተቋማቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናል አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ
“በግል ሐኪሜ ካልሆነ አልታከምም ማለታቸው እንድንጠራጠር አድርጎናል” ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ “አዕምሮዬን ብስት እንኳን በማላውቀው ሐኪም መነካት አልፈልግም” ተጠርጣሪ አቶ ጃዋር መሐመድ “ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ የሚሰጠው ትዕዛዝ እየተከበረ አይደለም” ተጠርጣሪዎች “መርህ አክብረን ሁሉንም ነገር በአግባቡ እየፈጸምን ነው” የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በተጠረጠሩበት የአመፅ ጥሪ ማድረግ፣ የሰው ሕይወት ማጥፋት፣ የእርስ በርስ ግጭት መፍጠር፣ የንብረት ውድመትና ሌሎችም የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኘው እነ አቶ ጃዋር መሐመድና ሁለቱ የመንግሥት ተቋማት (ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግና ፌዴራል ፖሊስ) የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናልና አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ። ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች “ፈጽሜያለሁና አልፈጸሙም” በሚል … [Read more...] about እነ ጃዋር መሐመድና ተቋማቱ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ “ፈጽመናል አልፈጸሙም” በሚል ተካካዱ
የእነ ጃዋር ጉዳይ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት እያመራ ነው
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቶ ጃዋር መሀመድና እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ የቅደመ ምርመራ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጠ። አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች በዛሬው ዕለት (ሐሙስ) በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል። የዐቃቤ ሕግ ጥያቄ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋርን ጨምሮ አጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች አቶ ጃዋር መሃመድ በሚል መዝገብ በመዝገብ ቁጥር 215585 ላይ የቅድመ ምርመራ መዝገብ የከፈተ ሲሆን፥ በዚህ መዝገብ ላይ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል የተጠረጠረ ጋዜጠኛም ተካቷል። አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 215585 የቀዳሚ ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠይቋል። በተጨማሪም የፌደራል … [Read more...] about የእነ ጃዋር ጉዳይ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት እያመራ ነው
የበቀለ ገርባ የክስ ዝርዝር
ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ከወር በፊት በቁጥጥር ሥር ውለው በምርመራ ላይ ያሉት አቶ በቀለ ገርባ፣ የእርስ በርስ ግጭት በማነሳሳትና ሌሎች ወንጀሎች እንደሚከሰሱ መወሰኑን ዓቃቤ ሕግ ረቡዕ ዕለት አስታወቀ። አቶ በቀለ በበኩላቸው እንደተናገሩት የሃጫሉ ሞትን ምክንያት በማድረግ የተቀሰቀሰው ሁከትና ግጭት፣ በራሱ በሕዝቡ የተመራ እንጂ እሳቸው ይህንን ማድረግ የሚያስችል ሠራዊት እንደሌላቸው ገልጸው፣ መንግሥት ፍርድ ቤትን በመጠቀም ተቀናቃኙን ለማጥፋት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቢያነ ሕግ ማክሰኞ ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ልደታ ማስቻያ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው እንደተናገሩት፣ ተጠርጣሪው አቶ በቀለ በምን እንደሚከሰሱ ተወስኗል ብለዋል። ክስ የሚመሠረትባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት … [Read more...] about የበቀለ ገርባ የክስ ዝርዝር
ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀረቡ
አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ገድለዋል ተብለው የተጠረጠሩት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በከሰአት በኋላ በነበረው ችሎትም የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ በቡራዩና አዲስ አበባ በተፈጠረ አመጽና ሁከት በደረሰ የሰውና የንብረት ጉዳት የተጠረጠሩ 8 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በጠዋቱ ችሎት በቀዳሚነት የቀረቡት ጥላሁን ያሚ እና አብዲ አለማየሁ ላይ መርማሪ ፖሊስ የሰራውን የምርመራ ስራ ይፋ አድርጓል። በዚህም የምስክር ቃል መቀበሉን፣ ወንጀሉ የተፈጸመበት ስፍራን በቴክኒክ ማስረጃ ማረጋገጡን፣ ግብረ አበሮቻቸውን በቁጠጥር ስር አውሎ ምርመራ እየሰራ መሆኑን፣ አርቲስት ሃጫሉ የተገደለበትን ሽጉጥ ከተጠርጣሪዎች ቤት ከተቀበረበት ጓሮ ማውጣቱን እና በምርመራ ማረጋገጡን አስረድቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ስልካቸውን … [Read more...] about ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚና አብዲ አለማየሁ ፍርድ ቤት ቀረቡ
በወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር ለፍርድ ቤቱ፤ “ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው፤ የሚበጀው ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው” አለ
ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ጃዋር ሲራጅ መሃመድ የተከሰሰበት ጉዳይ “ፖለቲካዊ ነው፤ ይህ ችግር የሚፈታው ቁጭ ብሎ በመወያየት ነው” በማለት ለፍርድ ቤቱ ተናገረ። የወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ከጃዋር ጋር አብሮ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎችም ተጠርጣሪዎች ሐሙስ ዕለት ነው ልደታ ምድብ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እና አራዳ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት። ይህንንም ተከትሎ የጃዋር ጠበቃ ደንበኛቸው በዋስ ከእስር ቤት ውጪ ሆኖ ጉዳዩን መከታተል እንዲችል እንዲፈቀድለት ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ተቀብሎታል። በዚህ … [Read more...] about በወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር ለፍርድ ቤቱ፤ “ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው፤ የሚበጀው ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው” አለ
ኦኤምኤን ሕጋዊ ክስ ተከፈተበት፤ ለጊዜውም ሊታገድ ይችላል
በአሜሪካ አገር በትርፍ አልባ ድርጅትነት የተቋቋመውና ለበርካታዎች ሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ተጠያቂ ነው የሚባለው ኦኤምኤን (የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ) ክስ ተመሥርቶበታል። ከሚዲያው ጋር ታደለ ኪታባ (የሚዲያው ሹም እንደመሆኑ)፤ እንዲሁም አያንቱ በከቾ በግል የክስ ተመሥርቶባቸዋል። ክሱን ያቀረቡት ጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ እንደሚሉት ይህ ፋይል የማስከፈት ዓይነት ተግባር ነው እንጂ በትክክል በዐቃቤ ሕግ ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ክስ አልተመሠረተባቸውም። የጉዳዩ ባቤት የሆኑት አቶ ጥበበ ሳሙኤል እንዲህ ይላሉ፤ ከበርካታ ሰዎች እና የሚድያ አውታሮች፤ 'OMN and its employees are Charged in District Court የሚል የዜና ዘገባ እየተራገበ መሆኑ እና እንዳብራራ ጥያቄ እየተጠየቅኩ ነው። በአጭሩ ለማብራራት "they are sued not … [Read more...] about ኦኤምኤን ሕጋዊ ክስ ተከፈተበት፤ ለጊዜውም ሊታገድ ይችላል
ሕልመኛና የቆሰለው አውሬ ጃዋር [እና] ዋኤል ጎኒም
[ጁን 8፤ 2010] ዋኤል ጎኒም (ዕድሜ 28) እንደወትሮው ዜናዎችን ለመቃረም፣ ከዘመድና ወዳጅ ጋር ለመወያየት ዱባይ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ተቀምጦ በፌስቡክ መስኮት ወደ ትውልድ ሀገሩ ግብጽ ዘለቀ፤ በዚያን ዕለት ያነበበው ዜና እና የተመለከተው ፎቶ ስሜቱን አወከው፣ እረፍት ነሳው፣ ዜናው አሌክሳንድሪያ ውስጥ በሙባረክ የጸጥታ ሀይሎች በግፍ ስለተገደለው ካሊድ ሰይድ (ዕድሜ 28) ነበር፡፡ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የነበረው የካሊድ አስከሬን በዐይን ለማየት ይከብዳል፡፡ “በዛ አሰቃቂ የካሊድ ፎቶ ውስጥ ራሴን አየሁት፣ በካሊድ ቦታ እኔም ልሆን እችል ነበር ብዬ አሰብኩ” ይላል ዋኤል በዚያች ቅጽፈት የተሰማውን ስሜት ሲገልጽ፣ ከቁጭትና ንዴት ባለፈ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት አሰበ፤ ጊዜ ሳያጠፋ ማንነቱን ደብቆ "We are all Khaled Said/ሁላችንም ካሊድ ሰይድ ነን" … [Read more...] about ሕልመኛና የቆሰለው አውሬ ጃዋር [እና] ዋኤል ጎኒም
ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ
አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ዘገበ። ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ከደቂቃዎች በፊት በሰራው ዘገባ እንዳለው ጀዋርን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጥረት የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ከፌዴራል የጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር። በሁለቱ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ፍጥጫ ጉዳት ስለመድረሱ የዘገበው ኦኤምኤን ተጨማሪ ማብራሪያ ግን አልሰጠም። የፌዴራል የጸጥታ አስከባሪዎች ኃይል ጨምረው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራሮችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉ የቴሌቭዥን ጣቢው ዘግቧል። ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ «ለጊዜው የታሰሩበት ቦታ አልታወቀም» ብሏል። በውጭ አገር የተመሠረተው እና አቶ ጀዋር መሐመድ በኃላፊነት ሲመሩት የነበሩት … [Read more...] about ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ
ኦፌኮ መጋጨት ጀመረ – ጃዋር በጸሃፊው በኩል የተሳሳተ መረጃ አሰራጨ
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እያወቁ ሕግን በመጣስ የወሰኑት ውሳኔ ወደ ሌላ ቀውስ ሊያመራ እንደሚችል ስጋት የገባቸው ወገኖች የተማጽንዖ ጥሪ አቀረቡ። ኦፌኮ ስህተቱን ከማረም ይልቅ እርስ በርስ የሚጣረስ መረጃ ማሰራጨቱ በፓርቲው ውስጥ መለያየት እየፈጠረ መሆኑና ጃዋር ደጋፊዎቹን በጅምላ ወደ አመጽ ለመምራት ዝግጅት እያደረገ መሆኑ ታወቀ። ጸሃፊው ያሰራጩት የተሳሳተ መረጃ በጃዋር መመሪያ ነው። ስጋቱ የተነሳው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀነ ገደብ አስቀምጦ ለኦፌኮ በድጋሚ የላከው የጃዋር ዜግነት ጉዳይን የሚመለከተውን ደብዳቤ ተከትሎ አዲስ “አስተምህሮት” መጀመሩ ነው። ለዚሁ የሕግ ይከበር ጥያቄ ቅድሚያ መልስ የሰጡት ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ነበሩ። በምላሻቸው “(ጃዋር) መልኩም ሲታይ ኢትዮጵያዊ ይመስላል” በማለት ስላቅ አዘል መላምት ካስቀመጡ በኋላ ጃዋር መልስ እንዲሰጥበት ደብዳቤው … [Read more...] about ኦፌኮ መጋጨት ጀመረ – ጃዋር በጸሃፊው በኩል የተሳሳተ መረጃ አሰራጨ