• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የእነ ጃዋር ጉዳይ ከተጠርጣሪነት ወደ ተከሳሽነት እያመራ ነው

August 6, 2020 08:04 pm by Editor Leave a Comment

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቶ ጃዋር መሀመድና እና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ የቅደመ ምርመራ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጠ።

አቶ ጃዋር መሀመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ሐምዛ አዳነን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች በዛሬው ዕለት (ሐሙስ) በፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።

የዐቃቤ ሕግ ጥያቄ

ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ጃዋርን ጨምሮ አጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች አቶ ጃዋር መሃመድ በሚል መዝገብ በመዝገብ ቁጥር 215585 ላይ የቅድመ ምርመራ መዝገብ የከፈተ ሲሆን፥ በዚህ መዝገብ ላይ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል የተጠረጠረ ጋዜጠኛም ተካቷል።

አቃቤ ህግ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ በመዝገብ ቁጥር 215585 የቀዳሚ ምርመራ እንዲደረግባቸው ጠይቋል።

በተጨማሪም የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በዚህ መዝገብ ላይ በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ 15 ምስክሮች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን፤ እንዲሁም 5 ምስክሮች ደግሞ ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲል አቤቱታ አቅርቧል።

በተጨማሪም በዝግ ችሎት ምስክሮቹ ቃላቸውን እንዲሰጡም ጠይቋል።

የጠበቆች ምላሽ

የሁሉም ተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው አቃቤ ህግ ያቀረበው አቤቱታ ላይ መቃወሚያቸውን አቅርበዋል።

በዚህም በዝግ ችሎት ተብሎ ለቀረበው አቤቱታ በግልፅ ችሎች ምስክሮቹ እንዲሰሙ እንደሚፈልጉ እና አቃቤ ህግ የሚያቀርባቸው ምስክሮች ጭብጥ ለመከላከል እንደሚያመች እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

እንዲሁም ምስክሮቹ ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃል መስጠት እንደሌለባቸው እና ስም ዝርዝራቸውም ተለይቶ ተሰጥቷቸው አውቀዋቸው የምስክርነት ቃላቸውን ሊሰጡ እንደሚገባም ገልፀዋል።

ክሱ ስልጣን ባለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚቀርብ መሆኑን ተከትሎ የቀዳሚ ምርመራ የምስክር ቃልም ለክሱ መከላከል እንዲያስችላቸው አስቀድመው ሊያውቁት እንደሚገባም በመቃወሚያዎችን አንስተዋል።

ተጠርጣሪ አቶ በቀለ ገርባ፥ “የማስመዘግበው አቤቱታ አለኝ፤ ሀሳቤን ፍርድ ቤቱ ይቀበለኝ” ያሉ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ “በጠበቆቻችሁ በኩል በቂ ሀሳብ ተነስቷል” ሲል አልተቀበላቸውም።

ብይን

የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ብይን ሰጥቷል።

በተለይም በስነ ስርዓት ህጉ መሰረት የቀረበው የቅድመ ምርመራ የአቃቤ ህግ ምስክሮች በዝግ ችሎት ቃላቸው እንደሚሰማ እና ይህም ክስ ከመመስረቱ በፊት የሚደረግ የቅድመ ምርመራ በዝግ ችሎት እንደሚሆን አብራርቷል።

የምስክሮችን ዝርዝር እና ጭብጥ ጉዳይ ይሰጠን ተብሎ በቀረበ መቃወሚያ ላይም ለደህንነታቸው ታሳቢ ተደርጎ እንደማይሰጥና አምስቱ የአቃቤ ህግ ምስክሮችም ከመጋረጃ በስተጀርባ ቃላቸውን እንዲሰጡ ብይን ሰጥቷል።

የፌደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በቅድመ ምርመራ መዝገቡ ላይ የምስክሮች ቃል እንዲሰማ ለነሃሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። (ምንጭ፤ ታሪክ አዱኛ – ፋና)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Law, Middle Column Tagged With: bekele gerba, chilot, jawar, jawar massacre, ችሎት

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule