በአሜሪካ አገር በትርፍ አልባ ድርጅትነት የተቋቋመውና ለበርካታዎች ሕይወት መጥፋትና ንብረት መውደም ተጠያቂ ነው የሚባለው ኦኤምኤን (የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ) ክስ ተመሥርቶበታል። ከሚዲያው ጋር ታደለ ኪታባ (የሚዲያው ሹም እንደመሆኑ)፤ እንዲሁም አያንቱ በከቾ በግል የክስ ተመሥርቶባቸዋል።
ክሱን ያቀረቡት ጥበበ ሳሙኤል ፈረንጅ እንደሚሉት ይህ ፋይል የማስከፈት ዓይነት ተግባር ነው እንጂ በትክክል በዐቃቤ ሕግ ጥፋተኛ ናቸው ተብሎ ክስ አልተመሠረተባቸውም። የጉዳዩ ባቤት የሆኑት አቶ ጥበበ ሳሙኤል እንዲህ ይላሉ፤
ከበርካታ ሰዎች እና የሚድያ አውታሮች፤ ‘OMN and its employees are Charged in District Court የሚል የዜና ዘገባ እየተራገበ መሆኑ እና እንዳብራራ ጥያቄ እየተጠየቅኩ ነው። በአጭሩ ለማብራራት “they are sued not charged”.
ይህ ዜና እየሰራጨ ያለው በስሕተት ከሆነ ይታረም፤ ግን ህን ተብሎ፤ የምናደርጋቸውን ነገሮች ተአማኒነት ለማሳጣት ከሆነ ደግሞ አይሳካም። ስለዚህ በስህተት ይህን የምታሰራጩ፤ እባካችሁ እርማት አድርጉ።
ሃቁ የሚከተለው ነው።
በኦኤምን እና በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ክስ ተመስርቷል፤ የተመሰረተው ክስ ግን፤ የፍትሃ ብሄር ክስ ነው በእንግሊዘኛው አጠቃቀም መሆን ያለበት “sued” እንጂ “charged” አይደለም፤ ምክንያቱም በአማርኛው ክስ/ክስ ቢሆንም፤ በእንግሊዝኛ አጠቃቀሙ ግን ይለያያል፤ “charge” የሚለ ቃል የሚሰራው፤ አቃቤ ሕግ በወንጀል ክስ ሲመሰረት ነው። ክሱን ስመሰርት፤ ፍርድ ቤቱን ከጠየኩት ጥያቄ አንዱ፤ ለሚኒሶታ የፌደራል አቃቤ ሕግ በኦኤሜን ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲያደርግ ትእዛዝ ይሰጥ የሚለውን ይጨምራል።
አቶ ጥበበ ይህንን ከተናገሩ በኋላ በፍርድ ቤት ስለተከፈተው ጉዳይ ሲያስረዱ በፌስቡክ ገጻቸው እንዲህ ብለዋል።
በመጀመሪያ ለትብብር እና ድጋፋችሁ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። ይህ ግን ገና አንድ ስንዝር የተሄደበት መንገድ እንጂ ብዙ ይቀረናል። አሁን ካለብኝ የሥራ ውጥረት፤ ብዙ ነገር አልልም። ግን በጥቂቱ፤ ሂደቱን ልግለጽ። ይህ የተመሰረተው ክስ፤ የፍትሃ ብሔር ክስ ነው። ይህም ማለት ከግለሰብ ጉዳት ጋር በተያያዘ የቀረበ ክስ ነው። አንድ ሰው፤ በፍትሃ ብሔር፤ ለመክሰስ፤ መክሰስ የሚችልበት የግል ጉዳት ማሳየት ይኖርበታል፤ ከሳሹ legal standing ሊኖርው ይገባል፤ ይህም ክስ የተመሰረተው ይህንን legal standing በሚያሟላ መልኩ ነው።
የኮረና ቫይርሰ ጉዳይ ባይኖር ኖሮ፤ በተለይ፤ ክሱ እስኪታይ፤ አሁን ለፍርድ ቤቱ ባቀረብኩት መጠነኛ መረጃ መሰረት፤ ተከሳሾቹ፤ በምንም ሚድያ የጥላቻ፤ እና የጥፋት መልዕክታቸውን እንዳያስተላልፉ፤ ትላንትናውኑ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ሰምቶ፤ ጊዜያዊ እገዳ ትላንትናውኑ ያስተላልፍ ነበር፤ ግን በኮሮና ምክንያት፤ በስልክ ቀጠሮ ተሰጥቶ ጉዳዩ ስለሚሰማ፤ የተወሰነ ጊዜ መውሰዱ አልቀረም።
ይህ ጊዜያዊ እገዳ ከተጣለ፤ ለ20 ቀን ብቻ የሚቆይ ይሆናል ከዛ በፊት፤ ግን የፍርድ ቤት ክርክር ይደረግ እና በቂ መረጃ አቅርቤ ፍርድ ቤቱን ማሳመን ከቻልኩ፤ አጠቃላይ ክሱ እስኪታይ እና ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ፤ ተከሳሾቹ፤ ለጊዜው የጥላቻ መልዕክታቸውን እንዳያስተላልፉ ይታገዳሉ። ክሱን ካሸነፍኩ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ይታገዳሉ። ሂደቱ ይህን ይመስላል።
ክሱን በጥቅሉ ካሸነፍኩ፤ በተከሳሾቹ ላይ ፍርድ ቤቱ እንዲወስን የጠየኳቸው በጥቂቱ፤
(1) የገንዘብ ካሳ እንዲከፍሉ፤
(2) ንብረታቸው ተሽጦ እና ከህዝብ ያሰባሰቡት ገንዘብ ተነጥቆ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ጉዳት ለደረሰባቸው ካሳ እንዲከፍል፤ ለዚህም ፍርድ ቤቱ ትረስቲ እንዲመድብ፤
(3) በሚኒሶታ ለሚገኘው የፌደራል አቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ የወንጀል ምርመራ እንዲያካሂድ ትዕዛዝ እንዲሰጥ፤
(4) ተከሳሾሹ በIRS ኦዲት እንዲደረጉ፤ የሚሉ እና ሌሎችም ይገኙባቸዋል።
በኢሜልም በቴክስትም፤ በሌላም መንገድ ልታገኙኝ የሞከራችሁ አላችሁ። ቀደም ብዬ እንዳልኩት፤ በጣም የተወጣጠረ የስራ ሁኔታ ላይ ስላለሁ፤ በቶሎ መልስ ስለማልሰጣችሁ ቅር እንዳትሰኙ፤ በትህትና እጠይቃለሁ፤ መረጃ በማቀበል የተባበሩኝ 3 ሰዎች አሉ፤ ፍቃዳቸውን ጠይቄ ስማቸውን እገልፃለሁ።
ብዙዎች፤ ምን እንርዳ ብላችኋል፤ ከዚህ በፊትም የጠየኩት፤ አሁንም የምጠይቀው፤ የምታገኙትን መረጃ በኢሜሌ እንድትልኩልኝ፤ ነው፤ የኦሮሚፋ ቋንቋ መረጃ ያላችሁ፤ አስተርጉማችሁ ብትሰጡኝ፤ ይቀለኛል። ለትብብራችሁ አመሰግናለሁ። ቸሩ እግዚአብሔር ሃገራችንን እና ሕዝባችንን ይጠብቅ። ጊዜ ሲፈቅድልኝ፤ በበለጠ አብራራለሁ። tibebefsamuel@gmail.com
የእንግሊዝኛው መረጃ እንዲህ ይነበባል።
Today 07/13/2020, a civil suit against the following defendants commenced IN THE UNITED STATES DISTRICT COURT FOR THE DISTRICT OF MARYLAND
1. OromiaMedia Network (OMN)
2. PrincipalOfficer: Taddele M. Kitaba (in his OMN official capacity); AND
3. Ayantu Bekecho, in her personal capacity(individually);
The defendants, in this case, have violated 18 U.S.Code § 956, 18 U.S. Code § 878, and 26 USC Code § 501 (c). Each of these statutes provides an independent basis for entering the requested preliminary injunction. The OMN is served this lawsuit 5minutes ago through its email. This Posting is to let the defendants know that a lawsuit against them filed and to let them know to contact me to get the documents filed in court. Because EMERGENCY MOTION FOR A PRELIMINARY INJUNCTION OR Temporary Restraining Order is filed, the defendants have the legal right to present their defense. To get the document, contact me at: tibebefsamuel@gmail.com.
This posting is required by the district court as part of the legal process to get the documents to the defendants as soon as possible since the defendants are residents of the State of Minnesota.
The lawsuit in part indicates: “Pursuant to Rule 65 of the federal rules of Civil Procedure, Plaintiff Tibebe Samuel move for preliminary relief against Defendants OMN, Ayantu Bekecho, in her personal capacity, and Taddele M. Kitaba, (together, the “Defendants”), their agents, servants, employees, and attorneys, directing Defendants to stop and terminate their broadcasting services on TV, and all Social media platforms and deliveries of their message and services, mode of deliveries of their messages, fundraising activities and support services they provide to the Ethiopian community at large anywhere in the world, their direct broadcast and service to Ethiopia; and most of all to stop broadcasting any hateful messages, messages that call for the assassination of high government officials and well-known personalities in Ethiopia, the killing of any individual and any member of any ethnic group and the burning and destruction of properties in Ethiopia. In support thereof, the Plaintiff state as follows: ………”
Tibebe F. Samuel (aka Tibebe SamuelFerenji)
ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ
Gi Haile says
በማንኛውም መመዘኛ ኦ .ኤም. ኤን የሚያስተላልፈው ዜናና የቃለ መጠይቆች እንግዶቻቸው ስኘ ስርዓት የጎደለው ተማሩ ከሚባሉ ሰዎች የማይጠበቅ የወደቀ፣የረከሰና የተበላሸ ኣስተያየቶች በሙሉ የጥላቻ ዘመቻ ነው። በተለይም በአገሪቱ መንግሰት መሪ በጠቅላይ ምኒስትር ዶ/ረ ኣቢይን የሚሳደብ የሚያዋርድ ግላዊ ጦርነት ነው። የአገር መሪ መስደብ እጅግ ፀያፍ ነገር ነው ለትውልድ የምናስተላልፈውን ንግግሮች ትውልዱን ጎዳቸው ወደፊትሞ ጥሩ ያልሆነ ምሳሌ ነው።
Tazabihaile says
Ethiopian embassy in US should be helping him.Also we should help him financially a gofund me account need to be setip.Thank you Tibebe for taking this action
DC resident Ethiopian wake up and help him.