“በብዙ እብዶች መካከል ጤነኛ ያብዳል” ይባላል ይህን እውነታ ኡመር ሱሌማን ነው ከ18 አመት በፊት የተናገረው። ብዙ ሰዎች የወደዱት እምቢ ካለ ወይም እነሱ የጠሉትን ከወደደ “እብድ” ወይም “ከሃዲ መባሉ አይቀርም። በዚህ ውስጥ አልፈን ነው የመጣነው እኔ ጤንነቴን በደንብ አውቀዋለሁ የሰውም ማረጋገጫ አልፈልግም ለሰውም እንደዛው ትልቅና አስቀያሚ በሽታ ነው ያለው። ይህን ለማከምና ለማስተካከል መታገል ትክክል ነው ግን ደግሞ ትግሉ አገር በሚያፈርስ መልኩ መሆን የለበትም። የፈለገ ችግር ቢኖር ከየመን ከሊቢያና ከሶሪያ ኢትዮጵያ ትሻላለች! የመንን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት እንጂ ኢትዮጵያን ወደ የመን መውሰድ ጤንነት አይደለም። ሩዋንዳን የዘነጋ ሰው በራሱ በሽታ ነው። ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆመው ማውረድ ይቸግር ይሆናል። ያጣነውን ብቻ ሳይሆን ያለንንም ማስታወስ ተገቢ ነው … [Read more...] about ያበደውን አድረን ማወቃችን አይቀርም!
jawar
እንግዲህ ቢመርም እውነት ሊነገር ግድ ይላል!!!
በመጀመሪያ "የለውጡን (ሥሌት) የሰራሁት እኔ ነኝ" አለ - በዝምታ "አዎ ነህ" ተባለ ቀጠለና "እዚህ ሀገር ሁለት መንግሥት ነው ያለው የአብይ እና የቄሮ [የኔ]" አለ አሁንም በዝምታ "አዎ ልክ ነህ" ተባለ መንግሥት በዝምታ ያገነነው ኢመደበኛው የጃዋር መንግሥት በንግግር ብቻ ሳይገታ ውሳኔዎችን መሻር ማሳለፍ ጀመረ - በዝምታ መንግሥትነቱ ተረጋገጠለት እነሆ አሁን ደግሞ ለውጡ በመጣባቸው ጥቅመኛ የመንግሥት ሰዎች፣ አኩራፊዎች እና ጥገኛ ባለሀብቶች በተቀነባበረ ሴራ "ኢመደበኛው መንግሥታችሁ ሊገረሰስ ነው" ተብሎ (“የመግደል ሙከራ” በሚል ፈጠራ) 67 ንፁሃን ምስኪኖች ያልተገራው ኢመደበኛ ስልጣኑ ይፀና፤ ምሽጉም ይጠነክር ዘንድ መስዋዕት ሆነው ቀረቡለት። ይሄን ጊዜ በዝምታ አያልፉም ስንል - ተናገሩ! ምን አሉ "አንተ ዐይን ነህ - እንደ ብሌናችን … [Read more...] about እንግዲህ ቢመርም እውነት ሊነገር ግድ ይላል!!!
“የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ
ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የኢትዮጵያ ወዳጆች! የኢትዮጵያን ሕዝብ በአፈና፣ ዝርፊያና ሰብዓዊ ጥሰት ሲገዛ በነበረው ህወሓት እና በሌሎች ጽንፈኛ ብሄረተኞች ትብብርና ቅንጅት የታየውን የለውጥ ተስፋና እየተካሄዱ ያሉ ለውጦችን ለማደናቀፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ቡድኖች በገዥነት ዘመናቸው ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን ሀብትና ንብረት በመጠቀም የተለያዩ ቡድኖችን በገንዘብ በመደለል አገርን ከማተራመስ በላይ ወደ ማፍረስ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ተረድተናል። በተለይም አሁን አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው በጠ/ሚ/ር ዐቢይ የሚመራው ኢህአዴግ ሌሎች አጋር ፓርቲዎችን ጨምሮ በቅርቡ የሚያደርገው ውህደት ያልተዋጠላቸው የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ይኼን የውህደት እንቅስቃሴ በሚዲያ ፕሮፖጋንዳ ከማጣጣል ጀምሮ፣ የተለያዩ የትርምስ እና የሽብር እንቅስቃሴዎችን … [Read more...] about “የህወሓት ባለሥልጣናትንና አጋሮቻቸውን” መረጃ እየተረከክን ነው – ባለሙያዎቹ
ለህወሓት ሽማግሌ የላከ ሰው በኢትዮጵያ ላይ መዓት ያወርዳል!
በተለያየ አጋጣሚ ከሚያጋጥሙኝ አስተያየቶች አንዱ ጃዋር መሃመድን መነጋገሪያችን ማድረጉን እንተው፤ግለሰቡ የሚሰጠንን አጀንዳ አንስተን በመተንተን ሰውየው የሚፈልገውን ክብር በመስጠት ተፅኖ ፈጣሪነት እንዲሰማው አናድርግ የሚል ነው። በግሌ ስራየ ብሎ ሰውን ማጉላትንም ሆነ ሆን ብሎ ሰውን ማሳነስን ብቻ አላማ አድርጎ መጓዙ የብልህ መንገድ አይመስለኝም። ጠቃሚው ነገር የሰው ስራ የሚያመጣው ተፅዕኖ ላይ ትኩረት አድርጎ መነጋገሩ ይመስለኛል። በዚህ ሁኔታ ግባችን ግለሰቦች ሳይሆኑ የግለሰቦች ሃሳብ እና አካሄድ የሚያመጣው በጎ ወይ መጥፎ ተፅዕኖ ነው። በጎ ወይም መጥፎ ተፀዕኖ ያመጣውን የሰዎችን ስራ በተመለከተ ስንነጋገር የሰዎችን ስም ማንሳታችን ደግሞ አይቀርም። በጎውን ስራ ስናወድስ፤ መጥፎው ስራ ወደ ባሰ መጥፎ እንዳያድግ ልንነጋገርበት ስናነሳሳው ከግለሰቦች ጋር የተለየ ፀብ ወይም … [Read more...] about ለህወሓት ሽማግሌ የላከ ሰው በኢትዮጵያ ላይ መዓት ያወርዳል!
ጃዋር፤ ለኦሮሚያ የተጠመደ ፈንጂ!
“… ስሙን መጥቀስ ባያስፈልግም አንድ ጎረምሳ ልንለው እንችላለን። ጃዋር ዜግነቱ አሜሪካዊ በመሆኑ የጃዋር ሚዲያ የተመዘገበው በዚህ ጎረምሳ ስም ነው። ከየአቅጣጫው የሚሰበሰበው ገንዘብ የሚቀመጠው በዚሁ ልጅ ስም ነው። መኪኖችና አንዳንድ ንብረቶች የሚገዙትም በዚሁ ስም ነው። ይህ ጎረምሳ አዲስ አበባ እጅግ መንዛሪና በከፍተኛ ቅንጦት እንደሚኖር የሚያውቁት ነገረውኛል። የቄሮ አካልም አልነበረም። ቄሮ ከድል በኋላ ቤቱ ሲመለስ የጠበቀው ማሳውና መደቡ ሲሆን እነ ጃዋርና ስማቸውን የሚጠቀሙባቸው ጎረምሶች በሚሊዮኖች እየረጩ ዘመናዊ ተሽከርካሪ ይሸምታሉ፤ ንብረት ያከማቻሉ፤ ሰዎች ሰላም ሰፍኖ በተረጋጋ መልኩ እንዳያስቡ ቀውስ ይመረትላቸዋል። ልክ ከዚህ በፊት ተደርጎ እንደማይታወቅ በዓሉንም፣ ልደቱንም፣ በሚዲያ እያስጮሁ ያሳብዱታል። ይህ ወጣት የሰከነ ዕለት ለጃዋር የሚቀርብለት ጥያቄ ስለሚታወቅ … [Read more...] about ጃዋር፤ ለኦሮሚያ የተጠመደ ፈንጂ!
መንግሥትና ኦዲፒ የጃዋርን የድጎማ በጀት ጥያቄ ውድቅ አደረጉ
የኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ሥራ አስኪያጅና ባለቤት ጃዋር መሃመድ ለድርጅቱ በጀት እንዲመደብና በቋሚነት እንዲረዳ ለመንግሥት ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ታወቀ። የጎልጉል የኦዲፒ የመረጃ ምንጮች እንዳሉት የድጎማ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ ጃዋር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና በኦዲፒ ላይ የጥላቻ ሪፖርት ተጠናክሮ እንደሚሠራ መናገራቸውን አመልክተዋል። በተያያዘ ጃዋር የሚመራው ኦ.ኤም.ኤን. ለሸዋ ተወላጅ ኦሮሞዎች መድረክ እንደማይሰጥና ኦነግ በንጹሃን ላይ እየፈጸመ ያለውን ግድያም ሽፋን እንዲሰጥ እንደማይፈቅድ ተገልጿል። እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ጃዋር ለሚመራው “የትግል ሚዲያ” ከፍተኛ በጀት የጠየቀው ሚዲያው ለተገኘው ለውጥ ትልቁን ሚና ተጫውቷል በሚል ነው። ኦ.ኤም.ኤን. በትግሉ ወቅት የአንበሳውን ድርሻ በመጫወቱ የኦሮሚያ ክልልም ሆነ መንግሥት ሊደጉመው እንደሚገባ በተደጋጋሚ … [Read more...] about መንግሥትና ኦዲፒ የጃዋርን የድጎማ በጀት ጥያቄ ውድቅ አደረጉ
በ’ርግጥ በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል ጥላቻ፣ በደልና ቂም በቀል አለ?
የትላንቱ እንቅፋት፣ ዛሬም ይመታናል የትላንቱ ገመድ፣ ዛሬም ይጠልፈናል ፤ ሰምተንም - አልሰማን፣ ሳሰማም ሰምተናል አይተንም - አላየን፣ ሳናይም አይተናል ላለመማር - መማር እኛ ተምረናል። አሁን… አሁን ''ከልሂቃኑ እስከ ኢ-ልሂቃኑ'' ድረስ፤ ቀድም ብሎ ሙሰላዊያንና ሂተለራዊያን፤ ካለፉት ሃምሳ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ሻአቢያዊያንና ወያኔያዊያን እንዲሁም ኦነጋዊያን ከባንዳ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው የተቀበሉትን የፈጠራና የጥላቻ ታሪክ ስላወሩትና የስልጣን ኮርቻውን ስለተፈናጠጡት፤ የሚንናገሩትና የሚጽፉት ሁሉ እንድ ዕውነት ተቆጥሮ ፤ “በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል ጥላቻ፣ በደልና ቂም-በቀል አለ!" መባሉ ነው። ሌላውን ሁሉ ትተን ባለፉት 26 ዓመታት ብቻ ሻአቢያዊያን፣ ወያኔያዊያንና ኦነጋዊያን የሰሩትን ግፍና በደል፣ የዘሩትን ጥላቻና በቀል ብናስብ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ 'ርስ-በርሱ … [Read more...] about በ’ርግጥ በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል ጥላቻ፣ በደልና ቂም በቀል አለ?