1. የገዳ ሥርዓት ጥንታዊ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች (Primitive Oromo pastoral tribes) ለከብቶቻቸው ተጨማሪ የግጦሽ መሬትና የውሃ ምንጭ (natural resources) ለማግኘት ጎረቤቶቻቸውን ይወሩበት የነበረ ባህላዊ አደረጃጀት ሲሆን ጉዲፈቻና ሞጋሳ ደግሞ የኦሮሞን ባህል እና ቋንቋን በተወረረው ማኅበረሰብ ላይ ለመጫን የሚያገለግሉ ማስፈጸሚያ ስልቶች ናቸው። የአርብቶ አደሩን ማኅበራዊ፣ ወታደራዊና መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመሩ፣ የሚያደራጁ፣ ተዋጊዎችን ለጦርነት መርቀው የሚልኩና በመሳሰሉት የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ የስርዓቱ የገዢ መደቦች አባ ገዳ፣ አባ ዱላ፣ አባ ላፋ፣ ሞቲ፣ ሉባ ወዘተ ተብለው ይጠራሉ። የገዳ ሥርዓት የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ለሆነው አርብቶ አደር ብቻ የሚያገለግል የአንድ ማኅበረሰብ ባህላዊ አደረጃጀት … [Read more...] about የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ
oromo
መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!
የዐቢይ ንግግር አምቦን ወደ ቀልቧ መልሷታል የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር (ህወሓት/ትህነግ) መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ ከ300 በላይ ዜጎችን/በብዛት ኦሮሞዎችን/ ጨፍጭፎ በአንድ ጎድጓድ በቤተመንግሥት ቀብሯቸው እንደነበር ታወቀ። አጽማቸው ተለቅሟል። ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ በአምቦ የተመረጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ካነጋገሩ በኋላ ከተማዋ ወደ ቀድሞ ቀልቧ፤ ሕዝቡም ወደ ልቡ መመለሱ ተሰማ፡፡ የጎልጉል የአዲስ አበባ የመረጃ ሰዎች እንዳሉት ህወሓት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ደብዛቸው የጠፋ ዜጎችና ባብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች በመለስ ውሳኔ ተገድለው በአንድ ጉድጓድ አፈር ተመልሶባችዋል። የእነዚህ ዜጎች አጽም የተገኘው ሆን ተብሎ በተካሄደ ቁፋሮ ሲሆን እንደ መረጃ አቀባዮቹ ከሆነ ከአጽሙ ጋር መረጃ ሰነዶችም ተገኝተዋል። በዘመነ ህወሓት ለሚዲያ ፍጆታ ደርግ … [Read more...] about መለስ በ300 ዜጎች አጽም ላይ ነግሦ ተገኘ፤ አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ናቸው!
“ቄሮ አልሸባብ” ነው – ህወሓት!
“ስድስት ሚሊዮን ወጣት በጠላትነት ፈርጀህ ማንን ልታስተዳድር ነው?” ለማ መገርሳ ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵ የተለያዩ ክፍሎች በተለይም በምሥራቅ ሐረርጌ “ቄሮ” በመባል የሚታወቅ ሕገወጥ እንቅስቃሴ እመረምራለሁ፤ ለፍርድ አቀርባለሁ ብሎ ዝቷል። “አመራሩ ብቃት የለውም” በማለት ራሱን የገመገመው ህወሓት/ኢህአዴግ ብቃት አልባነቱን ተገንዝቦ ራሱን ከሥልጣን ማግለል ሲገባው አሁንም የማሰርና የማሰቃየት ግፉን በስፋት ለመቀጠል በዕቅድ ለመቀንቀሳቀስ ማሰቡን ነው በዚህ ዜና የገለጸው። የኢትዮጵያ ወጣቶችን በሥራ በማሰማራት ለአገር እንዲጠቅሙ ከማድረግ ይልቅ “አደገኛ ቦዘኔ” በማለት ሲፈርጅና ሲስር የነበረው ህወሓት አሁን ደግሞ በኦሮሞ ወጣቶች “ቄሮ” ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ለመሰንዘር ጎራዴውን እየሳለ ነው። ግፉ የበዛባቸው ወጣቶች ታላቁ ሩጫ በተካሄደበት ባንድ ወቅት ላይ “አደገኛ ቦዘኔ … [Read more...] about “ቄሮ አልሸባብ” ነው – ህወሓት!
መልስ ለዶ/ር በያን አሶባ ቃለ መጠይቅ
የተከበራችሁ አንባቢያን፤ ይህችን መጣጥፍ ለመከተብ የተነሳሁት የዶ/ር በያን አሶባን (የኦሮሞ ዴሞክራሲ ግንባር ቃል አቀባይ) ቃለ መጠይቅ ካደመጥኩ በኋላ ነው፤ አመለካከታቸው ብዙ መልካም አስተሳሰቦችን በውስጡ ያካትታል፤ መልካም የምላቸው አመለካክቶች የኢትዮጵያ ችግር መፈታት ያለበት እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑ፤ መሰረታዊ ለውጥ ማስፈለጉ፣ በሙሉ እከሌ ከእከሌ ሳይባል የፖለቲካ እስረኞች የመፈታትን ሃሳብ፣ የውጭው ትግል አጋዥነት እንጂ መሪ ቦታ መያዝ እንደማይገባው፤ የሚሉትን ሲሆን ትልቁ ተቃውሞዬ ወያኔን የሽግግሩ አካል ማድረጉ ላይ ነው፤ (በሰላምና እርቅ ሰበብ) ፍራቻቸው ወያኔ አጓጉል አወዳደቅ ከወደቀ አገሪቱ የማትወጣበት ችግር ውስጥ ትገባለች ነው፤ {አገሪቱ የማትወጣበት ችግር ውስጥ ከገባች ሰንብታለች}። ወደ በያን አሶባ ማንነት ስመለስ ለዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በመለሱት ደብዳቤ … [Read more...] about መልስ ለዶ/ር በያን አሶባ ቃለ መጠይቅ