
1. የገዳ ሥርዓት ጥንታዊ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች (Primitive Oromo pastoral tribes) ለከብቶቻቸው ተጨማሪ የግጦሽ መሬትና የውሃ ምንጭ (natural resources) ለማግኘት ጎረቤቶቻቸውን ይወሩበት የነበረ ባህላዊ አደረጃጀት ሲሆን ጉዲፈቻና ሞጋሳ ደግሞ የኦሮሞን ባህል እና ቋንቋን በተወረረው ማኅበረሰብ ላይ ለመጫን የሚያገለግሉ ማስፈጸሚያ ስልቶች ናቸው። የአርብቶ አደሩን ማኅበራዊ፣ ወታደራዊና መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመሩ፣ የሚያደራጁ፣ ተዋጊዎችን ለጦርነት መርቀው የሚልኩና በመሳሰሉት የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ የስርዓቱ የገዢ መደቦች አባ ገዳ፣ አባ ዱላ፣ አባ ላፋ፣ ሞቲ፣ ሉባ ወዘተ ተብለው ይጠራሉ። የገዳ ሥርዓት የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ለሆነው አርብቶ አደር ብቻ የሚያገለግል የአንድ ማኅበረሰብ ባህላዊ አደረጃጀት በመሆኑ ለአፋሩ፣ ለሲዳማው፣ ለከንባታው፣ . . . ወይም በግብርና፣ በንግድ፣ በሸክላ ሥራ እና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ህይወቱን ለሚመራው ማኅበረሰብ የሚያገለግል አይደለም። ምንም እንኳን የዘመናችን የኦሮሞ ብሔርተኞች ስርዓቱን ሜካፕ ቀባብተው እና የዘመናት ገበናውን ሸፋፍነው በቆረጣ ዩኔስኮ ቢያስመዘግቡትም እንኳን “ውስጡን ለቄስ” እንደሚባለው በሌሎች የሃገራችን ማህበረሰቦች (ብሔሮች) በታሪክ ያስከተለው ጠባሳ የሚታወቅ ነው። ለምሳሌ የሃድያ፣ ሲዳማ፣ ሶማሌ፣ ሃረሪ (አደሬ)፣ ጉራጌ፣ ከንባታ፣ የም፣ የጊቤ አካባቢ ህዝቦች ስለራሳቸው ክልልና ዞን ታሪክ በፃፏቸው ሰነዶች እና በትውፊት በየማህበረሰቡ ውስጥ የሚነገሩ ታሪኮች የስርዓቱን ጭካኔ የሚያረጋግጡ ናቸው።
~
2. በገዳ ሥርዓት የስነ መንግሥት መዋቅርም ሆነ የስነ ህንጻ ጥበብ ውጤት የሆኑት ቤተ መቅደስ፣ ቤተ መንግሥት፣ ሃውልቶች እና የመሳሰሉት ግንባታዎች ባይገኙም፣ የስነ ጽሁፍ ባህል በማህበረሰቡ ባይታወቅም እንኳን በየጊዜው እየጨመረ ለሚመጣው የከብት ብዛት ማሰማሪያ የሚሆን ተጨማሪ የግጦሽ መሬትና ውሃ በሃይል ለማግኘት የሚያስችል ጠንካራ ባህላዊ የሆነ ወታደራዊ አደረጃጀት ነበረው። የማህበረሰቡን ወንዶች ለጦርነት ማደራጀት በሁሉም የኦሮሞ ጎሳዎች የሚከናወን ሲሆን የጎሳው መሪ አባ ገዳ (ሉባ)፣ አዋጊው የጦሩ መሪ አባ ዱላ፣ የመሬት ባላባቱ ደግሞ አባ ላፋ ይባላሉ። ወንዶችን በዕድሜ እርከን ከፋፍሎ በማደራጀት በየ8 ዓመቱ የደከመውን በአዲስ ተዋጊ ሃይል በመተካት ጥቃቱን አጠናክሮ መቀጠሉ ባህላዊ የውጊያ አደረጃጀቱን ያሳይ ይሆናል እንጂ ሰላማዊ የጉርብትና ፖሊሲ እንዳለው ወይም ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መሆኑን አያመላክትም። ይሁንና ይህ የማህበረሰቡ ባህላዊ የውጊያ አደረጃጃት ተጨማሪ የግጦሽ መሬት ለማግኘትና ያለማቋረጥ ለመስፋፋት እንዲሁም የማህበረሰባቸውን ባህልና ቋንቋን ለማሰራጨት ጠቅሟል።
~
3. የጎሳው መሪ በሚመራው ማኅበረሰብ ክብርና ዝና የሚያገኘው ኦሮሞ ያልሆነን ህዝብ በመውረር ለጎሳው ባስገኘው ተጨማሪ የመሬት ስፋት፣ በነዳው የከብት ብዛት እና በማረከው (ባወረመው) የሰው መጠን በመሆኑ ለራሳቸውና ለጎሳቸው (ለቤተሰባቸው) ክብር ሲሉ አባ ገዳዎች (ሉባዎች) አንዱ ከሌላው የበለጠ ሰፊ መሬት ለመውረርና በርካታ ህዝብ ለመማረክ (ገርባ ለማድረግ) እርስ በርስ ይፎካከሩ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በማህበረሰቡ ባህል መሰረት ወጣቶች ከነገዳቸው ውጭ ያለ ሰው በመስለብ ብልቱን ቆርጠው ለሽማግሌ ካላሳዩ ወይም ትልቅ የዱር እንስሳ አድነው ካልገደሉ በስተቀር ሚስት ማግባት፣ ፀጉራቸውንም መላጨት አይፈቀድላቸውም። በዚህ የተነሳ የሰውን ልጅ እንደ አውሬ በማደን ብልቱን መስለብ፣ መግደልም ሆነ ጎጆውን አቃጥሎ፣ በሽብር ጥቃት ቀዬውን ጥሎ እንዲሰደድ በማድረግ መሬቱን፣ ሚስቱን እና ከብቱን መንጠቅ፣ ልጆቹን በጉዲፈቻ በማወረም ለዘረፋቸው ከብቶች ጠባቂ እረኛ ማድረግ በጥንቱ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ የተለመደና የሚያስከብር ባህል ነበር። በመሆኑም በወቅቱ የድርጊቱ ፈፃሚዎችን ጀግና የሚያስብላቸው፣ በጎሳቸው የሚያስከብራቸው እንጂ የሚያስወቅሳቸው ሃራም ወይም ሃጢያት አልነበረም። ባጠቃላይ የገዳ ሥርዓት በወታደራዊ የበላይነትና በባህል ተፅዕኖ ሌሎች ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰቦችን በሃይል ጨፍልቆ መሬትና የተፈጥሮ ሃብታቸውን በመቀማት የኦሮሞን የበላይነት (Hegemony) ለማምጣት የሚተጋ ሥርዓት ነው።
~
4. በገዳ ሥርዓት ማህበረሰቡን በዋርካ ዛፍ ጥላ ስር ወይም ውሃ (ወንዝ) ዳር ሰብስቦ አምልኮት የመፈፀምና ተዋጊዎችን በአባ ገዳዎችና በቃሉ (ቃልቻ) ለወረራ መርቆ የመሸኘት ልማድ ነበር። ይሁን እንጂ በማህበረሰቡ የስነ ፅሁፍ ባህል (ፊደል) ስላልነበረ የየገዢ መደቡም ሆነ አጠቃላይ የማህበረሰቡ ታሪክ የሚተላለፈው በቃል ከሰው ወደ ሰው በቅብብሎሽ ስለነበረ ተረት እና እውነቱን፣ የተጨመረና የተቀነሰውን ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ ነው። በጽሁፍ፣ በሃውልት፣ በቅርጻ ቅርፅና በመሳሰሉት የተደገፈ የታሪክ መረጃዎች ባለመኖራቸው የማህበረሰቡን ታሪክ በአፈ ታሪክ (Oral Tradition) ላይ የሚያተኩር በመሆኑ ለመዛባት የተጋለጠ ሆነ። ይህ ክፍተት እንደ ኦነግ ዓይነት ህዝብን በማነሳሳት በንጹሃን ደም ላይ ተረማምደው ባቋራጭ የፖለቲካ ድልና ስልጣን ለመያዝ ለሚፈልጉ ጽንፈኛ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ካድሬዎቻቸው የቆርጦ ቀጥል ትርክት (ፕሮፓጋንዳ) ለመፈብረክ ተመቻቸው። ለምሳሌ የኦሮሞ ብሔርተኛ የሆነው ዶ/ር ህዝቅኤል ገቢሳ የመጀመሪያው ኦሮሞ ከውሃ ውስጥ ነው የወጣው ተብሎ በማህበረሰቡ አፈ ታሪክ እንደሚታመን ከአንድ ሚዲያ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ላይ ገልጿል። ሌሎች የብሔረሰቡ ልሂቃን ደግሞ ኦሮሞ ከውሃ ውስጥ ሳይሆን ከደቡባዊ ግብጽ (ከኑቢያ) ፈልሶ እንደመጣ ያስረዳሉ፣ ጥንታዊ የኦሮሞ ጎሳዎች የቀድሞ መኖሪያቸው አፍሪካ ቀንድ ሶማሊያ ውስጥ (Somalia Peninsula) ነው የሚሉም አሉ፣ የኦነግ የትርክት ማሽነሪ የሆኑት እነ ፕ/ር አሰፋ ጃለታና የትግል ጓዶቹ ደግሞ “በቃል ሲነገር ከመጣው ከኦሮሞ ህዝብ አፈ ታሪክ (Oral Tradition)” መረዳት እንደሚቻለው የሚል አንገት ማስገቢያ ከጻፉ በኋላ፡ እንደሌሎች የኩሽ ቋንቋ ተናጋሪዎች የኦሮሞ ህዝብም ጥንታዊ መኖሪያ (Home Land) በመካከለኛው ኢትዮጵያ ደጋማ አካባቢዎች መሆኑን በጥናት ተርጋግጧል በማለት ስለጉዳዩ በቀጥታ ምንም ያላሉትን የአንድ ሁለት ፈረንጆች ስም በመጥቀስ የቃላት ቁማር ከተጫወቱ በኋላ፣ አንድ ኦነጋዊ የጻፈውን ትርክት እንደ ድጋፍ (supporting material) በማቅረብ ያጠቃልላሉ።
~
የማንን አባት ማመን እንዳለብን እርግጠኛ ባልሆንም እንደ ፕ/ር ህዝቅኤል ገቢሳና የፕ/ር አሰፋ ጃለታ ቡድን ከአባቶቼ በአፈ ታሪክ (Oral Tradition) በቃል ሰማሁ የሚሉ አንድ ተጨማሪ የኦሮሞ ተወላጅ ሰው ላስተዋውቃችሁ። እኚህ ሰው ይልማ ደሬሳ ይባላሉ። ክቡር ይልማ ደሬሳ በቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ ዘመን የገንዘብ እና ንግድ ሚኒስቴር የነበሩ፣ በ5ቱ ዓመት የአርበኞች ትግል በጥቁር አንበሶች የፀረ ፋሺስት ትግል ወቅት ለሃገራቸው ነጻነት ዋጋ የከፈሉ ታላቅ አርበኛ ናቸው። ክቡር ይልማ ደሬሳ ወለጋ የተወለዱ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ሲሆኑ ከአባቶቼ በቃል ሲወርድ የሰማሁትና ከታማኝ ምንጮች ያነበብኩት ነው በማለት “የኢትዮጵያ ታሪክ በአስራ ስድስተኛ ክፍለ ዘመን” በተባለ መጽሐፋቸው “ኦሮሞዎች ወደ ደጋ ኢትዮጵያ መውጣት” በሚል ምዕራፍ ስር ስለ ጥንታዊ የኦሮሞ ከብት አርቢ ጎሳዎች ወደ መሃል አገር አመጣጥ በተመለከተ ሲገልፁ፡ መጀመሪያ በባሊ ቆላማ አካባቢዎች በመቀጠልም ቀስ በቀስ ወደ ደጋማው የባሊ ተራራማ አካባቢዎች ለከብቶች በቂ ውሃና የግጦሽ መሬት ወደሚያገኙበት ለምለም አካባቢ በመፍለስ ሰፈሩ። የሰፈሩበትንም አካባቢ በኦሮምኛ ቋንቋ “መደ ወላቦ” ብለው ጠሩት። ትርጉሙም የወላቦ ምንጭ ማለት ነው። ወላቦ በወቅቱ የነበረ የጎሳቸው መሪ ሰው ስም ነው፣ በማለት ክቡር ይልማ ደሬሳ ታሪኩን ይቀጥላሉ። ሌሎች ደግሞ የኦሮሞና የሶማሌ አርብቶ አደር ጎሳዎች ደቡብ ሶማሌ ውስጥ እስከ ኪሲማዮ የባህር ጠረፍ ድረስ እየተመላለሱ በጉርብትና ይኖሩ እንደነበረ፣ ነገር ግን የሱማሌ ጎሳዎች እስልምናን እምነት ከተቀበሉ በኋላ ቀድም በግጦሽ መሬት ያደርጉት ከነበረው ግጭት በተጨማሪ በእምነት ምክንያት ልዩነታቸው እየሰፋና እየተካረረ በመምጣቱ በተደጋጋሚ ይዋጉ ነበር፣ በመጨረሻ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች ጦርነትን በመሸሽ ከሱማሌ አውራጃ ተሰደው በባሊ አካባቢ በመምጣት እንደሰፈሩ በሶማሌ አፈ ታሪክ (Oral Tradition) ይነገራል። በምሳሌነትም “Gaal Madow Wars” ወይም “Galkayo” የተባለውን በሶማሌ ውስጥ በኦሮሞና ሶማሌ አርብቶ አደሮች መካከል የተደረገውን ጦርነት ይጠቅሳሉ። ባጠቃላይ የኦሮሞ ምሁራን የታሪክ ትርክታቸው የሚለያየው ከላይ እንደተገለጸው በማህበረሳባቸው ጥንታዊ መኖሪያ (Home Land) ላይ ብቻ ሳይሆን እነሱ ከሚሉት አካባቢ እንኳን ተነስቶ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንዴት አሁን ባሉበት ደረጃ ማለትም በኬንያ፣ በሱማሌና በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደተሰራጩ የሚሰጡት ትንታኔ በዛው መጠን የተለያየ ነው።
~
5. የኦሮሞ የገዢ መደብ እና የነገድ ስርጭት፣ እንደሚታወቀው በርካታ የሃገር ውስጥ እና የውጭ የታሪክ ፀሀፊዎችና ተመራማሪዎች ስለ ጥንታዊት ኢትዮጵያ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ በተመለከተ ከአባይ (ግዮን) ወንዝ፣ ከቀይ ባህር እና ከህንድ ውቅያኖስ ጋር በማዛመድ ፅፈዋል። ከክርስቶስ ልደት በፊት ሆሜር እና ሄሮዱተስ የተባሉ የግሪክ የታሪክ ፀሃፍት እና ጂኦግራፈር በወቅቱ ኢትዮጵያ ከግብፅ በስተደቡብ የምትገኝ፣ በምስራቅ ቀይ ባህርና በደቡብ ህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ድረስ እንደምታካልል ገልጸዋል። ከላይ ስለ ጥንታዊ የኦሮሞ ጎሳዎች Home Land በተመለከተ በተለያዩ የኦሮሞ ልሂቃን የተገለጹ አስተያየቶችን ጠቅለል አድርገን ስንመለከት ከሞላ ጎደል ምስራቅ አፍሪካ (አፍሪካ ቀንድ) ወደሚል ድምዳሜ ያመራናል። በሌላ በኩል ደግሞ ሆሜር እና ሄሮዱተስ የኢትዮጵያ የወሰን ክልል ብለው በጠሩት ውስጥ ከሚገኘው ከሶማሌ አውራጃ ይኖሩ የነበሩ ጥንታዊ የኦሮሞ አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ተፈናቅለው ባሊ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ሌላኛው የኢትዮጵያ ክፍል በመምጣት መስፈራቸውን እንረዳለን። እነዚህ የኦሮሞ ማህበረሰቦች ከጊዜ በኋላ “ቦረና እና ባሬንቱ” ተብለው ለሁለት አብይ ነገዶች (clans) ተከፈሉ። ከነዚህ ቦረና እና ባሬንቱ ከሚባሉ አብይ (አውራ) ነገዶች በጊዜ ሂደት ሌሎች ንዑሳን ነገዶች (sub clans) ከውስጣቸው ወጡ። የመጀመሪያዎቹ ንዑሳን ነገዶች ውስጥ መጫ፣ ቱለማ፣ ከረዮ፣ ኢቱ፣ አርሲና የመሳሰሉት ይገኙበታል። እንደገና እነዚህ ንዑሳን ነገዶች በራሳቸውም እየተዋለዱና ኦሮሞ ወዳልሆኑ ጎረቤት ህዝቦች ባደረጉት ወረራና መስፋፋት ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን ኦሮሞ ስላደረጉ ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ በፈጣን ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ በእነሱ ውስጥም ሌሎች ደቂቃን ነገዶችና ጎሳዎች በየአካባቢው እየተበራከቱ ሄዱ። ለምሳሌ ሆሮ፣ ጉድሩ፣ ሊበን፣ ገላን፣ በቾ፣ ጀሌ፣ ጉጂና የመሳሰሉትን መጥቀስ ይቻላል።
~
ከኦሮሞ ማኅበረሰብ የሚወለዱ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በ July 24, 2017 ከአድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በመካከለኛው ኢትዮጵያ በርካታ የራሳቸው ማንነት ያላቸው ህዝቦች እንደነበሩና እነዚህ ህዝቦች ዛሬ የት ገቡ? ለተባሉት ጥያቄ ሲመልሱ: “ከ16ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ ከግራኝ አህመድ ወረራ በኋላ ባለው 50 ዓመት ጊዜ ውስጥ የኦሮሞዎች መስፋፋት ነበር። ይሄን ነገር ብዙ ኦሮሞዎች *ይክዳሉ*፤ በኔ በኩል ግን ተቀባይነት የለውም” በማለት የኦሮሞ ጥንታዊ ጎሳዎች ስለፈፀሙት መስፋፋትና ወረራ በግልጽ ተናግረዋል። ከዚህም ቃለመጠይቅ በተጨማሪ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ “የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ” ብለው በፃፉት መፅሐፍ በገፅ 296 ላይ በወለጋ ገላን በሚባል አካባቢ ምንጫቸው ቦረና የሆኑ የመጫና የቱለማ ኦሮሞዎች ወደ አካባቢው መጥተው ከመስፈራቸው በፊት ኦሮሞ ያልሆኑ ጋንቃ፣ ማኦ፣ ክዋማና ክዌጎ የሚባሉ ነባር የኢትዮጵያ ህዝቦች መኖሪያ እንደነበርና አሁን እነዚህ በስም ተለይተው ይታወቁ የነበሩ ህዝቦች በኦሮሞ የአባ ገዳ ወራሪዎች የጠፉና የተደመሰሱ መሆናቸውን ገልፀዋል። ዶ/ር ነጋሶ በዚሁ “የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ” ብለው በጻፉት መፅሐፍ የሰዮ (ቄለም) ወለጋ አካባቢ የነበሩ ብዛታቸው ከአስር በላይ የሆኑ የተለያዩ የአካባቢው ነባር (Native) ማህበረሰቦች ሞጋሳ በሚባል የኦሮሞ ባህል ተገደው ኦሮሞ እንደሆኑ እስከ ስማቸው ዘርዝረው ገልፀዋል። የእሳቸውም ቤተሰቦች በኦሮሞ ጎሳዎች ወረራ ከጠፋ “ዳሞት” ከሚባል ማኅበረሰብ የተገኙ መሆኑን ከአድማስ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ገልፀዋል። ህመሙን ያልተናገረ መድሃኒት እንደማያገኝለት ሁሉ ኢትዮጵያም የምትድነው ሃቅን ተቀብሎ ወደፊት በመጓዝ እንጂ እውነትን በመሸፋፈን ወይም በኦነግ ተረት ተረት አይደለም።
~
ላለፉት አምስት መቶ አመታት አካባቢ የኦሮሞ ገዢዎች ተብለው የሚታወቁት አባ ገዳዎች፣ አባ ዱላዎች፣ አባ ላፋዎች፣ ሞቲዎችና የመሳሰሉት ኦሮምኛ የማይናገሩ ጎረቤት ማህበረሰቦችን ሲያስጨንቁ የኖሩ ሲሆን አሁን በዘመናችን በተለይ ኦነግ እና ወያኔ ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ ሃገሪቷን በቋንቋ ላይ የተመሰረተ የጎሳ ፌዴራሊዝም ካዋቀሩ በኋላ የዚህን የኦሮሞ የገዢ መደብ የጭካኔ መንፈስ የወረሱ ከፌዴራል እስከ ኦሮሚያ ክልል በሃላፊነት ላይ የተቀመጡ፣ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ወታደራዊ ክንፎቻቸው፣ በሲቪል ማህበራትና በእምነት ተቋሞች ውስጥ ተሰግስገው ይገኛሉ። በየአደባባዩ የአባቶቻችን ልጆች ነን እያሉ የሚፎክሩ የዘመናችን የኦሮሞ የገዢ መደቦች ዛሬም እንደ ጥንቶቹ የኦሮሞ ገዢዎች ለሴትና ለህጻናት የማያዝኑ፣ ደም አፍሰው የማይጠግቡ መሆናቸውን በተለይ ላለፉት አራት አመታት በተግባር አሳይተዋል። ህዝብን አስገድዶ የማወረም የሞጋሳ ሥርዓት በቅርቡ የኦሮሞ ዜግነት በሚል በአዲስ መልክና ሽፋን ቃሉን ቀይረው ይዘውት ብቅ ብለዋል። በዚህ መሰረት በክልሉ የሚኖር ኦሮሞ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ የኦሮሞ ዜግት በሚባለው አዲሱ የሞጋሳ ወይም የጉድፈቻ ሥርዓት መሰረት ይወርማል ማለት ነው። ስለዚህ የገዳ ባህል ዛሬም እንደጥንቱ ብዛሃነትን የማይቀበል፣ ሁሉን ወደራሱ የሚጠቀልል፣ ሰልቃጭና ጨፍላቂ መሆኑን ዛሬም ስራቸው ይመሰክርባቸዋል። የጥንቶቹን እና የዘመናችንን የኦሮሞ ገዢዎች ከሚያመሳስላቸው በርካታ ነገሮች ቢኖርም በዋናነት መጥቀስ የምፈልገው ኢትዮጵያ በውስጥም ሆነ በውጭ ጠላቶች ሰላሟ ደፍርሶ አለመረጋጋት ውስጥ ስትገባና ህዝቡ ግራ ተጋብቶ አሻጋሪ ሙሴ በሚፈልግበት ጊዜ በንጹሃን ደም ላይ ተረማምደው የራሳቸውን ፍላጎት (advantage) ለማስከበር አጀንዳ ቀርጸው የሚመጡ፣ በኢትዮጵያ ውድቀትና ኪሳራ እርካብና መንበራቸውን የሚያደላድሉ ልዩ ጥቅም ፈላጊ ስግብግብ Opportunist መሆናቸው ነው። ይህንን ማንነታቸውን በተጨባጭ ምሳሌ ማየት እንችላለን:-
(1) በ16ኛው ክፍለ ዘመን በአረቦች እና በኦቶማን ቱርክ እየታገዘ ከሃረር ተነስቶ መላ ኢትዮጵያን ለ14 ዓመት ባሸበረው የግራኝ አህመድ ጦርነት ምክንያት የማዕከላዊው መንግሥትም ሆነ የአዳል ሱልጣኔቶች ሃይል በተዳከሙ ጊዜ የኦሮሞ የገዥ መደብ የሆኑት አባ ገዳዎች (ሉባዎች) ሁኔታው ለወረራ እንደሚያመች በመረዳት ከጥቃት የሚከላከልለት መንግሥት ያልነበረውን ያን መከረኛ ህዝብ በመንጋ በመውረር ከብቱን ይነዱ፣ ህዝቡን እያፈናቀሉና እየገደሉ በመሬቱ ላይ ይሰፍሩ ነበር፣ ከእልቂት የተረፈውን ህዝብ ደግሞ በሞጋሳና በጉድፈቻ እያወረሙ በሃገሩ ላይ ገዢ ሆነው ተቀመጡ።
(2). በመካከለኛው ዘመን በሃገራችን ተከስቶ ለነበረው ለዘመነ መሳፍንት መፈጠር “የቅርብ” ምክንያት (immediate cause) የትግራዩ ራስ ሚካኤል ስሁል ቢሆኑም የግራኝ ጦርነት ተከትሎ በየአቅጣጫው ያለማቋረጥ ይጎርፍ የነበረው የኦሮሞ ጎሳዎች ወረራ፣ ፍልሰትና ሰፈራ ከፍተኛ ድርሻ የነበረው ሲሆን የመንጋ ጥቃቱን እና ሰፈራውን መግታት ባለመቻሉም የተነሳ የክርስቲያኑ የንጉሳዊ መንግሥት መቀመጫውን ከሸዋ ወደ ጎንደር ለማዛወር ተገደደ። የሃረሩን የአዳል ሱልጣኔት ደግሞ የኦሮሞ ጎሳዎችን ወረራና መስፋፋትን ለመከላከል የሃረር ጀጎል ግንብን በ1550 ዎቹ መጀመሪያ ላይ ገነቡ። ይሁንና በግንብ ሃረር ከተማን በማጠር ችግሩን መግታት ስላልተቻለ የአዳል ሱልጣኔት መንግሥት መቀመጫውን ከሃረር ነቅሎ ወደ አውሳ (አፋር) አዛወረ። በሌላ በኩል የኦሮሞ ጎሳዎች ወደ ሰሜን የሃገራችን ክፍል የሚያደርጉትን መስፋፋትና ሰፈራ በመቀጠል በደረሱበትና በተመቻቸው ቦታ በመስፈር በሃገሩ ላይ እንደባለቤት ተንሰራፍተው ተቀመጡ። የነባሩን ህዝብም ስብጥር፣ ቋንቋ፣ ባህል፣ እንዲሁም የህዝቡን የቆየ ልማድ፣ ወግ እና የመሳሰሉትን እሴቶች አዛቡት። ከሰሜኑ የአማራ ማኅበረሰብ ጋር አብሮ በመኖራቸው አንዳንድ የኦሮሞ ባላባቶች (ገዢዎች) ከመሳፍንቱና ከንጉሳዊ ቤተሰቦች ጋር ጋብቻና ወዳጅነት በመፍጠር እስከ ራስ ማዕረግ ድረስ የሃገሪቱን ከፍተኛ ስልጣን መቆጣጠር ቻሉ (ለምሳሌ የየጁ ኦሮሞዎች)። ይሁንና ከቀድሞ ጀምሮ ሲወርድ የመጣውን የዘውዳዊውን መንግሥት ህግና ሥርዓትን በመጣስ የመንግሥቱን ስልጣን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለመቆጣጠር ባደረጉት ህገ ወጥ እንቅስቃሴ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በየአካባቢው የሚገኘው ባላባትና ሹመኛ አልገብርም አልታዘዝም በማለት ሥርዓት አልበኝነት በመስፋፋቱ የንጉሳዊው መንግሥት በመፍረሱ ዘመነ መሳፍንት ሊከሰት ቻለ።
~
በመሆኑም የግራኝ አህመድ የሽብር ጦርነት ከጀመረበት እስከ አፄ ቴዎድሮስ መነሳት ድረስ በሚገኙ ሶስት መቶ ሃምሳ ዓመታት አካባቢ ጦርነት፣ ዘረፋ፣ ውድመትና ስደት በሃገራችን የተበራከተበት፣ ግራኝን ተከትለው በመጡ አረቦችና ተከታዮቻቸው በሃገራችን የባሪያ ንግድ የተስፋፋበት፣ እምነቴን አልቀይርም ያለው ክርስቲያኑና ሌላው ኢትዮጵያዊ እየታነቀ በባርነት ወደ አረብ ምድር የተሸጠበት፣ ገዳማት፣ የክርስቲያን መኖሪያ መንደሮችና ስልጣኔዎች የወደሙበት ነው። (ከግራኝ አህመድ እግር ስር የማይጠፋው የግል ታሪክ ፀሃፊው የነበረው የመናዊው አረብ ፈቂህ፣ መጽሃፍ ላይ የግራኝ አህመድ ተዋጊዎች ባለፉባቸው አካባቢዎች ሁሉ የሚያገኙትን ቤተክርስቲያን እና የክርስቲያን መኖርያ መንደሮችን ሳይዘርፉና በእሣት ሳያቃጥሉ አያልፉም ነበር ይላል። The Conquest of Abyssinia P. 60)። በነዚህ ዘመናት ጥንታዊ የኦሮሞ ጎሳዎች በየአቅጣጫው የተሰራጩበትና በነባሩ ህዝብ ርስት ላይ በገዢነት ተንሰራፍተው የተቀመጡበት፣ የህዝቡ ቋንቋ፣ ባህል ማንነና ስብጥርን የለወጡበት፣ በተለይ በጅማ በጊቤ አካባቢው የሚገኙ በሊሙ፣ ጉማ፣ ጎማ፣ የም እና በመሳሰሉት የሚኖሩ ነባር ህዝቦችን በሞጋሳ ወረው በማወረም ገርባ ካደረጓቸው በኋላ በቅንጅት ከአረብ የባሪያ ነጋዴዎች ጋር ወደ አረብ ምድር በባርነት ይሸጧቸው ነበር። ባጠቃላይ የግራኝ አህመድ የሽብር ጦርነት ከጀመረበት እስከ አፄ ቴዎድሮስ መነሳት ድረስ ሃገራችን ቀድሞ ከነበራት ከስልጣኔ ማማ የወደቀችበት የኢትዮጵያ የጭለማ ዘመን (Ethiopian Dark Age) ነው።
~
(3). የኦሮሞ የገዢ መደቦች በደርግ ጊዜ አብዮተኛ፣ በወያኔ ዘመን ደግሞ ብሔርተኛ በመሆን ጥቅማቸውን ለማስከበር መቼም የማይቦዝኑ፣ ሃፍረትና ይሉኝታ ያልፈጠረባቸው፣ ሴረኛ ቁማርተኞች ናቸው። በ1960 ዎቹ በነበረው የተማሪው እንቅስቃሴና አመጽ የመንግሥት ለውጥ በተከሰተ ጊዜ ለቀ/ኃ/ሥላሴ ከስልጣን መውረዳቸውን በጽሁፍ ካነበበው ከደበላ ዲንሳ፣ ከደርግ ዋና ፀሃፊ ከመንግሥቱ ኃ/ማርያምና ከደርግ ሊቀ መንበር ከጀነራል ተፈሪ ባንቲ ጀምሮ ኢትዮጵያን አስጎንብሰው የገዟት አብዛኛዎቹ የደርግ ባለስልጣናት ኦሮሞዎች ሆነው ሳለ ልክ ደርግ እንደወደቀ ያለ እፍረት የኦሮሞ ህዝብ “በደርግ የአማራ መንግሥት” ተበድሏል የሚል አጀንዳ ይዘው መጡ። ወደ ኋላ ሄደን ታሪካችንን ብናይ ተመሳሳይ ታሪኮችን እናገኛለን፡- የአጼ ምኒሊክ አብዛኛዎቹ ራሶችና ተዋጊ ወታደሮች፣ የቀ/ኃ/ስላሴ መኳንንትና የበላይ አዋጊ ጀነራሎች፣ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የሃገሪቱ የጦር መኮንኖች አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ነበሩ። ነገር ግን መንግሥት በተቀየረ ቁጥር ያጎረሳቸውን እጅ ነክሰው ተበዳይ ሆነው የሚቀርቡት ደግሞ መልሰው እነሱ ናቸው።
(4). እንደሚታወሰው በ1983 ዓ.ም የደርግ መንግሥት እንደፈረሰ ህወሃትና ኦነግ በመሰረቱት የሽግግር መንግሥት የኢትዮጵያን ህዝብ ውክልና (mandate) ሳይኖራቸው ከጠመንጃ አፈሙዝ ያገኙትን የፖለቲካ ስልጣን በመጠቀም ከዛ በፊት በኢትዮጵያ ታሪክ ያልነበሩ በቋንቋ ላይ የተመሰረቱ 14 የጎሳ ክልሎችን እና የከተማ መስተዳድሮችን አዋቀሩ። ሁሌም በኢትዮጵያ ውድቀትና ኪሳራ ማትረፍ የሚፈልጉት ኦነጋውያን (የኦሮሞ የገዢ መደቦች) ከወያኔ ጋር በመሆን በርካታ መሬቶችንና ህዝቦችን “ትግራይ” እና “ኦሮሚያ” ብለው ወደሰየሙት ክልሎች ህዝቡን ሳይጠይቁ በሃይል አካለሉ። ሰውን ሳይሆን መሬቱን ስለፈለጉ ብቻ በበርካታ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ያለፍቃዳቸው ማንነታቸውን በመጨፍለቅ ወደሰየሙት ክልል በማካለል ሃገሩን አስፋፍተው ያዙ። የነጠቁትን መሬት በህገ መንግሥታቸው የእነሱ ብቻ እንደሆነ ደነገጉ። ያለፍቃዳቸው ማካለላቸው ሳያንስ መልሰው እኛን አትመስሉም፣ የኛን ቋንቋ አትናገሩም በማለት የሃገሩን ባለቤቶች ከክልላችን ውጡ እያሉ ማፈናቀል ጀመሩ። ከወያኔና ከኦነግ በፊት ኢትዮጵያ ያልነበረች ይመስል ፊተኛዋን ኋላኛ አድርገው እናቷን ምጥ ላስተምርሽ እንዳለቸው እንስሣ ዓይነት ኢትዮጵያ የክልሎች ድምር ውጤት እንደሆነች ሰበኩ። ይህንንም በህገ መንግሥታቸው አሰፈሩ።
~
በመቀጠልም ኦሮሚያና ትግራይ በማለት በሰየሙት ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ ነባር ህዝቦችን በተለይም ጠላት ያደረጉትን የአማራን ብሔር ተወላጆችን ከክልላችን ውጡ በማለት ሃብት ንብረታቸውን እየቀሙ አፈናቀሉ፣ በግፍ ገደሉ፣ የዘር ማጥፋትና የዘር ማፅዳት ወንጀሎችን ፈፀሙ፣ ንጹሃንን ገድለው በዶዘርና በኤስካቫተር የሰውን አስከሬን እንደ ድንጋይ እያፈሱ በጅምላ ቀበሩ። የቀረውንም ለጅብ እራት አደረጉት። የዘመናችን የኦሮሞ የገዢ መደቦች የህዝቡን መሬት (የተፈጥሮ ሃብቱን) ለመቀማት ሲሉ በሚሊዮን የሚቆጠር የጌዴዎን ህዝብን አፈናቀሉ፣ በቡራዮ የጋሞን ህዝብ ጨፈጨፉ፣ የአማራን፣ የሶማሌን፣ የደቡብ ህዝብን እና የሲዳማን ህዝብ ደም አፈሰሱ፣ “ፊንፊኔ” (አዲስ አበባ) የኦሮሞ ናት፣ ሌላው ኢትዮጵያዊ በእኛ ፍቃድ የሚኖር ሰፋሪ ነው በማለት በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አውሮፓ ቅኝ ገዢዎች የአፓርታይድ የዘር መድሎ ሥርዓት ዓይነት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ዜግነትን አወጁ።
~
(5). አሸባሪው ህወሃት በህዝብ ማዕበል ተገፍቶ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ እንደፈረጠጠ፣ ወያኔ ያሳደጋቸው የኦህዴድ አመራሮች በህዝብ ትግል የመጣውን ለውጥ በመንጠቅ የሃገሪቷን ዋና ዋና የመንግሥት ስልጣን ተቆጣጠሩ። በመቀጠልም በለውጥ ስም በ2010 ዓ/ም የኦህዴድ የበላይ አመራር የሆኑት ኦቶ ለማ መገርሳና ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አስመራ ድረስ በመሄድ ያለ አንዳች ህጋዊ ውል ኦነግን እስከመሳሪያው ወደሃገር ውስጥ ማስገባታቸው ይታወሳል። አልጋ ባልጋ የሆነለት ኦነግ የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ካሉት ደጋፊና ተባባሪዎቹ ጋር በመቀናጀት 18 ባንክ ሲዘርፍ፣ የፖሊስ የመሳሪያ መጋዘን ሰብሮ ሲታጠቅ፣ ንጹሃንን ሲገድል፣ በመጨረሻም ወታደራዊና የፖለቲካ ክፍሉ ተለያይቷል እያለ በኢትዮጵያ ህዝብ ሲያላግጥ ወደ ሃገር ውስጥ ያስገቡት የኦህዴድ ባለስልጣናት የወሰዱት እርምጃ አልነበረም፣ የለም።
~
(6) የአዲስ አበባ ህዝብ ቆጥቦ የሰራውን የጋራ መኖሪያ ኮንዶሚኒየም ላይ የፈጸሙት ውንብድና ሳያንስ ህዝቡን በጅምላ የሸ**ጣ ልጅ ብሎ የሰደበ የኦሮሞ ጽንፈኛን ለምርጫ ተወዳዳሪ አድርገው ማቅረባቸውና ምርጫውንም አሸነፈ ብለው የህዝቡ ተወካይና የከተማው የካቢኔ አባል ማድረጋቸው ምንያህል የአዲስ አበባን ህዝብ እንደናቁት የሚያሳይ ሲሆን ከዛም በላይ ሰዎቹ ይሉኝታ የማያውቁ፣ ህግና ሞራል የማይዳኛቸው፣ ፈራሂ እግዚአብሔርን የሌላቸው፣ እነሱን እስከጠቀማቸው ድረስ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ እንደሆኑ ያሳያል።
(7) በ2009 ዓ/ም ጽንፈኛ የኦሮሞ ፓለቲከኞችና ልሂቃን ኢትዮጵያ ያበቃላት፣ የወደቀች መስሏቸው፣ ኢትዮጵያ ደክማለች አትተርፍም ብለው እንደለመዱት ሊቦጫጭቋት ለንደን ላይ ተሰባስበው በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ኦሮሚያን እንመሰረታለን እያሉ ሲደነፉ፣ በወቅቱ በኢትዮጵያ የመንግሥት መዋቅር የወያኔ አገልጋይ የነበረው የኦህዴድ ካድሬዎች ደግሞ ጨፌ ኦሮሚያ ተሰባስበው በአዲስ አበባ ላይ ኦሮሞ “ልዩ ጥቅም” ይገባዋል የሚል ረቂቅ ሰነድ አዘጋጅተው ለፌዴራል መንግሥቱ ፓርላማ ማቅረባቸው ይታወሳል። የኦሮሞ የገዢ መደቦች የሃብት ሽሚያና የጥቅም ጥያቄ ለማቅረብ የሚተጉትን ያህል በኦሮሚያ ክልል በገጀራ ስለሚታረደው፣ በጥይት ስለሚረሸነው፣ ተወልዶ ካደገበት ከሃገሩ ላይ ንብረቱን ተዘርፎ ሜዳላይ ስለተጣለው፣ ለትምህርት ወጥተው ታፍነው ስለቀሩት ወጣቶች እንደሰው ሰብዓዊነት ተሰምቷቸው ለአንድ ደቂቃ ሲናገሩ ተሰምተው አይታወቅም።
~
ሃገራችን ኢትዮጵያ አመሠራረቷ እና ያለፈችባቸው የተፈጥሮና የታሪክ ጉዞዎች ከሌሎች ሃገራት የተለየ፣ የራሷ የሆነ አሻራና ማንነት ያላት ጥንታዊትና ቀዳሚት ሃገር ናት። ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ፣ የግዮን መፍለቂያ፣ በቅዱሳን መፃህፍት የተገለፀች፣ የዳአ’ማት፣ የአክሱም፣ የላሊበላ እና የመሳሰሉት ስልጣኔዎች መገኛ ናት፣ የይሁዲ፣ የክርስትና፣ የእስልምና (የአብርሃም እምነቶች) እንዲሁም ባህላዊ አምልኮቶች ያሉባት ሃገር ናት። በዓለማችን ላይ ትላልቅ የሚባሉት መንግሥታት ከመፈጠራቸው በፊት ኢትዮጵያ ከህዝቧ ጋር ነበረች። ኢትዮጵያ በአንድ በኩል የሰው ልጅ መገኛ በሌላ በኩል ደግሞ የውህደት ሃገር ናት። በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከመሃል እስከ ጠረፍ የሚገኘው ህዝብ ባለበት ቦታ እንደዛፍ በቅሎ ወይም እንደ ግንድ ቆሞ የተገኘ ሳይሆን በተለያዩ ዘመናት በተከሰቱ በተፈጥሮና ሰውሰራሽ ምክንያቶች ማለትም በጦርነት፣ በድርቅ፣ በእምነት ልዩነትና በመሳሰሉት ከአንዱ አካባቢ ወደ ሌላ አካባቢ ሲሰደድ፣ ሲስፋፋ፣ ሲሰፍር፣ በሂደቱም አንዱ ህዝብ ከሌላው ጋር ሲቀየጥና ሲዋሃድ እዚህ የደረሰ ህዝብ ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ ህዝብ ከላይ የሸፈነውን የብሔር፣ የሃይማኖትና የፖለቲካ ካባውን ብናወልቀው በደምና በአጥንት የተዛመደ፣ በታሪክ የተሳሰረ ወንድማማች ህዝብ ሆኖ እናገኘዋለን። በመሆኑም ኢትዮጵያዊ ማንነት የብዙ ነገር ድምር ውጤት እንጂ በቋንቋ፣ በብሔር፣ በክልል፣ በእምነት፣ ወይም በሌላ በአንድ ነጠላ ነገር ብቻ ተመዞ ሊገለጽ የሚችል አይደለም። ይህንን እውነታ ገዚዎቻችን ተገንዝበው ለትውልድ የሚያስቡ ከሆነ ከገቡበት የጥላቻ፣ የበቀልና የጎሳ ፖለቲካ (Tribalism) መላቀቅ መቻል አለባቸው።
ምንጭ፣
1. “የኢትዮጵያ ታሪክ፤ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን” በአቶ ይልማ ደሬሳ፣ 1959 ዓ/ም
2. “የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ” (ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ)”–2008 ዓ/ም
3. THE JOURNAL OF OROMO STUDIES VOLUME 5, NUMBERS 1 & 2, JULY 1998
4. “The conquest of Abyssinia” Futuh al-Habasa (Arab Faqih) 2003
5. “በረራ – ቀዳሚት አዲስ አበባ (1400 – 1887) እድገት ውድመት እና ዳግም ልደት” 2020 ፕ/ር ሀብታሙ መንግሥቴ፣
6. አቶ አቻሜለህ ታምሩ፡ “ይድረስ ለሞጋሳ አሞጋሾች”
7. የህይወት ተሞክሮ፣ የግል ግዛቤና ምልከታ፣
ደረጀ ተፈራ
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
Leave a Reply