ከቅርብ ወራት ወዲህ ከአማራ ክልል በደጀን መስመር ወደ አዲስ አባባ የሚሄዱና የሚመለሱ ከባድ የደረቅ የጭነት ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች በተለይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከጎሐጽዮን ደብረጉራቻ ባለው መስመር ማለፍ ፈተና ሆኖባቸዋል። አስተያየታቸውን ከሰጡት አሽከርካሪዎች መካከል አንዱ ”ከፍቼ ከተማ የቅርብ ርቀት ከምትገኝ ‘አሊ ዶሮ’ ከተባለች ቦታ ላይ መስከረም 30/2013 ዓ. ም የክልሉን የፀጥታ ኃይሎች የደንብ ልብስ የለበሱ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው የቆሰሉና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው አሽከርካሪዎችና ከ10 በላይ የተሰባበሩና የተቃጠሉ መኪናዎች አሉ” ብሏል።እየደረሰ ያለውን ጉዳት በዝርዝር ያስረዳው ይኸው አስተያት ሰጪ፣ በአሽከርካሪዎችና በንብረት ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ሰሞኑን እስከ 70ና 80 የሚሆኑ አሽከርካሪዎች ከነተሸከርካሪዎቻቸው ለአማራ ክልል የተለያዩ … [Read more...] about ኦሮሚያን አቋርጠው የሚያልፉ የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ፈተና
oromiyaa
የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥርስ ውስጥ ገብቷል
የኦሮሚያን ክልል በውክልና የሚያስተዳድረው ኦህዴድ አቶ መለስ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ ውስጥ ውስጡን ሲንተከተክ የቆየው የድርጅቱ “የመስመር” ችግር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በተፈጠረ ስጋት የኦሮሚያ ልዩ የፖሊስ ተወርዋሪ ሃይል እንደ ቀድሞው እንደማይታመን ተጠቆመ። ሲቪል ሆነው በብርጋዴር ጀኔራልነት ስውር ማዕረግ የኦሮሚያን ፖሊስ ሲመሩ የነበሩት አቶ ደምመላሽ ገብረሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ የማዕከላዊ መረጃና የወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነርነት ቢዛወሩም አሻራቸው ኦሮሚያ ፖሊስ ውስጥ እንዳለ የሚጠቁሙት የጎልጉል ምንጮች፤ ክልሉ በፌዴራል ፖሊስ ደረጃ ያዋቀረው ተወርዋሪ ሃይል እየተደረገበት ያለው ክትትል ጥርጣሬው ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል ብለዋል። አቶ ደምመላሽ አሁን በፌዴራል ደረጃ ያላቸው ኃላፊነት ቀድሞ በኦሮሚያ ከነበራቸው ሥልጣን ጋር ተዳምሮ የተወርዋሪው ልዩ … [Read more...] about የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥርስ ውስጥ ገብቷል