በሌብነት የተጠረጠሩት በረከት ስምኦንና ታደሰ ካሣ አርብ በባህር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በዕለቱ ሁለቱም ግለሰቦች ያሉባቸውን ችግሮች ያስረዱ ሲሆን በተለይ በረከት ስምዖን በእስርቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲል ማማረሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ኮምፒውተር ያስፈልገናልም ብለዋል። በዕለቱ የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ባለፈው በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ማስረጃዎችን ማየቱንና የምስክሮችን ቃል መቀበሉን አሳውቋል። ሆኖም ጉዳዩ ከባድ፣ ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ምስክሮች እና ሰነዶች በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መገኘታቸውን አስታውሶ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። በወቅቱ የቀረበውን ማራዘሚያ ቀን በረከት የተቃወመ ሲሆን ያቀረበው ምክንያትም የሕግ ሥልጣን በሌለው አካል መከሰሰሱን ነው። ይህ ሕጋዊነት … [Read more...] about በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም፤ ኮምፒውተር እንፈልጋለን – በረከት ስምዖን
bereket
“በማረፊያ ቤት ሰብዓዊ መብታች ተጥሷል”፤ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ በአግባቡና በሰዓቱ አይቀርብልንም – በረከትና ታደሰ
በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉት በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሣ “በማረፊያ ቤት ቆይታችን ሰብዓዊ መብታችንን እና ክብራችንን የሚነካ ድርጊት ተፈጽሞብናል” በማለት ለፍርድቤት ቅሬታ አቀረቡ። ጉዳያቸው በአዲስ አበባ እንዲታይ ለፍርድቤቱ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ የአስራ አራት ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል። በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም. በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ ካለባቸው የጤና ችግር አንጻር በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ እንደሚመገቡ ገልጸው፤ ይሁንና በማረፊያ ቤቱ ምግብ በአግባቡ እና በሰዓቱ እንደማይቀርብላቸው ተናግረዋል። ለአብነትም ትናንት ምሳ በ10፡00 እንደቀረበላቸው ለችሎቱ አስረድተዋል። የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባቸው እና ጡረታ በአግባቡ … [Read more...] about “በማረፊያ ቤት ሰብዓዊ መብታች ተጥሷል”፤ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ በአግባቡና በሰዓቱ አይቀርብልንም – በረከትና ታደሰ
ሃቀኛው መላኩ ፈንታ
መልከ ቀና ነው፤ ፀጉሩ እንደ መኸር ጤፍ ተኝቷል። ሲራመድ ይፈጥናል። ወደ ምኒሊክ ቤተመንግሥት እየገባ ነው። ገባ። “አቶ መለስ ሦስት ምርጫዎች አሉኝ!” ቀጠለ። አንድ ህግ ተክትዬ መሥራት፣ ሁለት እያስመሰልኩ መኖር፣ ሶስተኛ ሳልሰራ በሪፖርት መኖር! አቶ መለስ በምርጫው ተደንቀው “በህግ ስራ፤ ማንም ከህግ በታች ነው” አሉት። የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ንግግር ከራሱ እሳቤ ጋር ተጣጣመ። የሚኒስቴር የቤተሰብ መኪና አልቀበልም ብሎ ቤተሰቡ በአዲስ አበባ የታክሲ ሰልፍ መያዝ ለመዱ። ቁርስ እና ምሳውን ከመስሪያ ቤቱ ካፍቴሪያ በ15 ብር እየተመገበ ሥራውን አጧጧፈ። አንድ የክልል ቢሮ ኃላፊ ቢያንስ ሁለት መኪና እና መኖሪያ ቤት ይሰጠዋል። ለዚህ ሰው ግን የለውም ።በጭቃ ቤት ይኖራል። ሰውየው የገቢዎች እና ጉምሩክ ኃላፊ ነው። ሚኒስትር ነው። የሃገሪቱ ገንዘብ በመዳፉ ቢያልፍም ወደ … [Read more...] about ሃቀኛው መላኩ ፈንታ
የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥርስ ውስጥ ገብቷል
የኦሮሚያን ክልል በውክልና የሚያስተዳድረው ኦህዴድ አቶ መለስ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ ውስጥ ውስጡን ሲንተከተክ የቆየው የድርጅቱ “የመስመር” ችግር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በተፈጠረ ስጋት የኦሮሚያ ልዩ የፖሊስ ተወርዋሪ ሃይል እንደ ቀድሞው እንደማይታመን ተጠቆመ። ሲቪል ሆነው በብርጋዴር ጀኔራልነት ስውር ማዕረግ የኦሮሚያን ፖሊስ ሲመሩ የነበሩት አቶ ደምመላሽ ገብረሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ የማዕከላዊ መረጃና የወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነርነት ቢዛወሩም አሻራቸው ኦሮሚያ ፖሊስ ውስጥ እንዳለ የሚጠቁሙት የጎልጉል ምንጮች፤ ክልሉ በፌዴራል ፖሊስ ደረጃ ያዋቀረው ተወርዋሪ ሃይል እየተደረገበት ያለው ክትትል ጥርጣሬው ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል ብለዋል። አቶ ደምመላሽ አሁን በፌዴራል ደረጃ ያላቸው ኃላፊነት ቀድሞ በኦሮሚያ ከነበራቸው ሥልጣን ጋር ተዳምሮ የተወርዋሪው ልዩ … [Read more...] about የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥርስ ውስጥ ገብቷል