በሌብነት የተጠረጠሩት በረከት ስምኦንና ታደሰ ካሣ አርብ በባህር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። በዕለቱ ሁለቱም ግለሰቦች ያሉባቸውን ችግሮች ያስረዱ ሲሆን በተለይ በረከት ስምዖን በእስርቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲል ማማረሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል። ኮምፒውተር ያስፈልገናልም ብለዋል።
በዕለቱ የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ ባለፈው በተሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ማስረጃዎችን ማየቱንና የምስክሮችን ቃል መቀበሉን አሳውቋል። ሆኖም ጉዳዩ ከባድ፣ ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ ከመሆኑም በላይ ምስክሮች እና ሰነዶች በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መገኘታቸውን አስታውሶ ምርመራውን ባለማጠናቀቁ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።
በወቅቱ የቀረበውን ማራዘሚያ ቀን በረከት የተቃወመ ሲሆን ያቀረበው ምክንያትም የሕግ ሥልጣን በሌለው አካል መከሰሰሱን ነው። ይህ ሕጋዊነት የሌለው አካል እንኳም የማራዘሚያ ቀጠሮ ሊጠይቅ መክሰስም አይችልም የሚል ነበር የበረከት ተቃውሞ።
ከበረከት ጋር በሌብነት ተጠርጥሮ የታሠረው ታደሰ ካሣ ደግሞ የዳሽን ቢራ ሁሉም ሰነዶች ተሟልተው ይገኛሉ በማለት ለፍርድ ቤቱ የተናገረ ሲሆን መንግሥት አስረን አናጣራም፤ አጣርተን ነው የምናስረው እስካለ ድረስ የተሟላ መረጃ እያለ እነሱን ማሰሩና የተጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ አነሱን በእስር ለማቆየት ብቻ መሆኑን በመጠቆም ውድቅ አንዲሆን ጠይቋል።
የሌብነት ተከሳሾቹን ቃል ከሰማና የግራ ቀኙን ከተመለከተ በኋላ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን ውስብስብነትና መረጃዎች በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ መገኘታቸውን ከግምት በማስገባት የተከሳሾቹን ቃል ውድቅ በማድረግ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮውን ፈቅዷል።
ከዚህ በተጨማሪ በዕለቱ በነበረው የፍርድ ሒደት ላይ በረከት ስምዖን ስንገባም ስንወጣም አየተሰደብንና ስማችን እየጎደፈ ነው በማለት ማማረሩን ቢቢሲ አማርኛ ጨምሮ ዘግቧል። እንዲሁም ተከሳሾቹ ጠበቃ ማግኘት ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ እንዲያቆምላቸውና ከቤተሰባቸው ጋር የመገናኘት ዕድል እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋል።
ተከሳሾቹ ይደርስብናል ላሉት ዘለፋና ስድብ ፍርድ ቤቱ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ይህንን ለማስቆም እንደሚሠራ አሳውቋቸዋል።
ከዚህ ሌላ ሁለቱ የሌብነት ወንጀል ተከሳሾች በማረሚያ ቤት ለመፃፍ የሚያስችላቸው ኮምፒውተር እንዲገባላቸው ጠይቀዋል። በተለይ በረከት በእስር ቤቱ ውስጥ ኢንተርኔት የለም ሲል መደመጡን ቢቢሲ ዘግቧ።
ባለፈው ፍርድቤት በቀረቡ ጊዜ ተጠርጣሪዎቹ ካለባቸው የጤና ችግር አንጻር በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ እንደሚመገቡ ገልጸው፤ ይሁንና በማረፊያ ቤቱ ምግብ በአግባቡ እና በሰዓቱ እንደማይቀርብላቸው የተናገሩ ሲሆን ለአብነትም ትናንት ምሳ በ10፡00 እንደቀረበላቸው ለችሎቱ ማስረዳታቸው ይታወሳል።
በኢትዮጵያ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ያልፈለገውን ማንኛውንም ሰው አሸባሪ በማለት ሕዝብን ሲገድል፣ ሲያበላሽ፣ ሲያሰቃይ፣ በቃል ሊገለጽ የማይችል ግፍ ሲፈጽም የኖረውን ሥርዓት በታማኝነት ከማገልገል አልፈው መብት ገፋፊ ሕግጋትን በማውጣት ለህወሓት/ኢህአዴግ በትጋት ሲሠሩ የነበሩ ግለሰቦች ይህንን መሰሉ የመብት ጥያቄዎች ሲያነሱ መስማት በእርግጥ በኢትዮጵያ ለውጥ አለ የሚያስብል ነው ተብሎለታል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
gi Haile says
ኮምፒውተር እና እንተርኔት ለከፍተኛ በለስልጣንና በአገርና በአለም አቀፍ ወነጀል የሚፈለግና የኢትዮጵያን ሕዝብ የ42 አመት ሰቆቃዎች ዋና ተዋንያን የሆነው በረከት ስምዖን የሰብዓዊ መብት ምን ማለት እንደሆነ የተረዳውና የተማረው በእስር ቤት በገባበት ጊዜ ነው። ለአንድ ወንጀለኛ ኮምፒውተር እና ኢንተርኔት መጠየቅ ከእስር ቤት ሆኖ ፀረ ሕዝብ ቅስቀሳና መረጃዎችን ለማጥፋት እንዲገናኝ ከመፈለግ የመነጨ መልካም የሚመስል መብት የሚመስል አቀራረብ ሁሉ በረከት ምን አይነት አደገኛ ሌባነቱን በበለጠ ያገነዋል። ባለስልጣናት ያለሆኑ ሚስኪን እስረኞች ጠይቀው ቢሆን ኖሮ ለዚያ ሰው እፈቅድለት ይሆናል። ለወንጀለኞች ባለስልጣናት ኢንተርኔት እንዲጠቀሙ መብት መስጠት የሚቻለው ፍርድ ተጠናቆ ከለቀ በኃላ ቢደረግ ይመረጣል። በአጠቃላይ ደኛ ብሆን የምሰጠው ውሳኔ አይቻልም ነው። ኢንተርኔት ለወንጀለኛ አልፈቅድም። RIP Bereket Semeon.
Tesfa says
ወያኔ አሻፈረኝ ብሎ ጫካ ከገባ በህዋላና የሃገሪቱ የበላይ ገዢ ከሆነ ጀምሮ ተሰፍሮ የማይዘለቅ ሰቆቃ በህዝባችን ላይ አድርሷል። የአፈና ክፍሉ አፍኖ ወስዶ ዛሬ የት እንደገቡ የማይታወቁ ወገኖቻችን ስፍር ቁጥር የላቸውም። ድብቅ እስር ቤት በትግራይ የለንም የሚለው ወያኔ ከገጠር እስከ ከተማ ድብቅ እሰርቤቶች እንደ ነበሩትና እንዳሉት መረጃዎች ያመለክታሉ። በመሰረቱ ወያኔ የተካነው በሸፍጥ በማታለል በመሆኑ ይቅርታን አያውቅም። ሲቀጣም ዘርህን ሁሉ ነው የሚያጠፋው። ገና በገና ከጀግና ዘር ለሃገር ከሚቆረቆር ተፈጥረሃል በማለት በመርዝ/በጥይትና በአፈና የሰወራቸው ስንቶች ናቸው?
ኢትዮጵያዊነትን ከልቡ ይጠላል። በዚህም የተነሳ ነው የበረሃውን የትግል አቀንቃኝ ኢያሱ በርሄን፤ በሃገር ቤት በትግርኛ ዘፈኑ እጅግ የሚወደደውን ኪሮስ ዓለማየሁን፤ የስለላ ክፍሉ ሃላፊ የነበረውን ክንፈ ገ/መድህን፤ የወያኔ ወታደራዊ አዛዥ ሃያሎም አርአያና ሌሎችም ከፍተኛና ዝቅተኛ ወታደራዊ አመራሮች አፈር ያለበሳቸው። አንድ ነን፤ አትከፋፍሉን በማለታቸው ነው። በበረሃም እንደ እነ ዶ/ር ራስ ወርቅ ቀጸላ የመሰሉ የትግራይ ልጆች ተረሽነዋል።
በዚህ አኳያ በበረከት ስምዖን ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ ትዕዛዝ በጎንደርና በጎጃም ብቻ ወደ 6 ሺህ ሰዎች በሰውር እንደተገደሉ ሲገመት በአዲስ አበባና በሌሎች ክፍለሃገራት (ክልል የሚለውን ቃል እጠላለሁ) ነጋዴዎችን፤ ምሁራንን፤ ወታደራዊ መኮንኖችንና ወያኔ ለሰጣቸው አጥፊ ትዕዛዝ በፍራቻም ሆነ ስላላመኑበት እንፈጽምም ያሉ ሁሉ በበረከት ትእዛዝ አፈር ተመልሶባቸዋል። በረከት አረመኔ ነው። አሁን ምግብ አልጣፈጠም፤ ኮምፒውተር ወዘተ ማለቱ ይህ ቀን እንደሚመጣ አምኖና በክፉ ቀን ህዝብ ብቻ መደበቂያ እንደሆነ በመገንዘም መኖር ያኔ ነበር። ፍትህ ያጣው ደም ዛሬም ይጮሃል። እስቲ የኢንተርኔት አገልግሎቱና ኮምፒውተሩ ይቅርና መጽሃፍት፤ መጻፊያ ደብተርና እርሳስ ይግባለት። የሚነግረን ነገር ይኖር? የበረከት ኑዛዜ በሚል ደጎስ ያለ መጽሃፍ… ከበረሃ እስከ እሰርቤት… እውነት ተናግሮ ከመሸበት ማደር ይላል የሃገሬ ህዝብ። እኔ በበኩሌ አቶ በረከት የወያኔን ያለፈና የአሁን ታሪክ ከራሱ ክፋት ጋር በግልጽ ጽፎ ህዝብን ይቅር በሉኝ ካለ ይቅር ለማለት ዝግጅ ነኝ። የሃገራችን ህዝብም እንቱፍ አታድርስ እንዳይደገም በማለት ይቅር እንደሚል አምናለሁ።
በለው ! says
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚ ብዛት 19 ሚሊየን መድረሱን ኢትዮቴሌኮም አስታወቀ።
ኢትዮቴሌኮም ይህንን ያስታወቀው ያለፉትን ስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው።
በዚህም የቴሌኮሙ ተጠቃሚ ብዛት 41 ነጥብ 1 ሚሊየን መድረሱንም ገልጿል።
በሞባይል ድምጽ 39 ነጥብ 54 ሚሊየን፣ መደበኛ ስልክ 1 ነጥብ 14 ሚሊየን፣ በስድስት ወራቱ ዳታና ኢንተርኔት ተጠቃሚ 426 ሺህ ሲሆን፥ አጠቃላይ የዳታና የኢንተርኔት ተጠቃሚ ደግሞ 19 ነጥብ 49 ሚሊየን መድረሱን ይፋ አድርጓል።
በተጨማሪም አጠቃላይ የቴሌኮም ተደራሽነት 43 በመቶ መድረሱንም በስራ አፈጻጸሙ መግለጫ ላይ አንስቷል።
ቴሌኮሙ በመፈንቅ ዓመቱ ካስገባው 16 ነጥብ 71 ቢሊየን ብር ውስጥ ሞባይል 63 ነጥብ 2 በመቶውን ሲሸፍን፥ ዳታና ኢንተርኔት 28 ነጠብ 7 በመቶውን እንዲሁም ከዓለም አቀፍ ድርሻ 5 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻ ማስመዝገቡን ጠቅሷል።
ኢትዮቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት የኢንተርኔት አገልግሎት የማገኘት መጠንም 97 ነጥብ 12 በመቶ እንደነበረም በመግለጫው አንስቷል።
በአብርሃም ፈቀደ
*****************************
ኢትዮጵያ ከ157 አገሮች የጤና እና የትምህርት ሥርዓቶች ( በሰብዓዊ ካፒታል ምዘና ) በ135ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ ካፒታል ምዘና ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ውጤት ከተሰጣቸው አገሮች ተርታ ተመድባለች። ባለፈው ሳምንት የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት በጋራ ባካሔዱት ስብሰባ ላይ ይፋ በተደረገው መመዘኛ ኢትዮጵያ 135ኛ ደረጃ ላይ ብትገኝም ለዘርፉ ትኩረት የሰጠች ተብላለች።
********************************
ጥር 8 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ የሆነው ሪፖርት እንዳመለከተው፣ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ከሚያገኙ 36 ሚሊዮን ሕፃናት መካከል 13 ሚሊዮን የሚሆኑት ከደሃ ቤተሰብ የወጡ ሲሆን፣ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡
94 በመቶ የሚሆኑት በገጠር የሚኖሩ ሕፃናት፣ በከተማ ደግሞ 42 በመቶ ሕፃናት ከላይ ለተጠቀሱት አገልግሎት ተደራሽነት የላቸውም፡፡ በኦሮሚያ ክልል 16.7 ሚሊዮን፣ በደቡብ ክልል 8.8 ሚሊዮን፣ በአማራ ክልል 8.5 ሚሊዮን ሕፃናት ሲሆኑ፣ በሐረር 90,000፣ በድሬዳዋ 156,000፣ በጋምቤላ ደግሞ 170,000 ደሃ ሕፃናት መሠረታዊ ፍላጎታቸው ሳይሟላ እንደሚኖሩ አመልክቷል፡፡በኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ከሆኑ 41 ሚሊዮን ሕፃናት መካከል 36 ሚሊዮን ያህሉ ወይም 18 ዓመት በታች ከሚገኙ ሕፃናት መካከል 88 በመቶዎቹ ለኑሮ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደማይችሉ ተገለጸ፡፡ ሕፃናቱ ካላገኙት መሠረታዊ አገልግሎቶች መካከል የተመጣጠነ ሥርዓተ ምግብ፣ ጤና፣ ውኃ፣ ትምህርት፣ ከጤና ጋር የተያያዘ ዕውቀት፣ መረጃና አሳታፊነት ይገኙበታል፡፡ ሰነዱን ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ከተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ጋር በመተባበር ያወጣው መልቲ ዳይሜንሽናል ቻይልድ ዲፕሪቬሽን ሪፖርት ነው፡፡
*******************
በረከት ስሞኦን ኢህአፓ አልነበረምን? እነሱ ከተገረፉ በኋላ በክራር ነበር የሚዝናኑት፡፡ በኢሃህአዴግ ግዜ ከተገረፉ በኋላ ቤት ተዘግቶባቸው ጭለማ ውስጥ ይዝናናሉ:: አያነቡም፡ አይናገሩም ፡አይጎበኙም፡ በረከትና ጓዱ አንደኛ ዜጋ ናቸውን? እነሱ ጓዶቻቸውን ያሠሩና ያሰቃዩት እዚያው ቦታ አደለምን? አዳሜ እስር ቤት ገብቶ ሲወጣ መጣፍ መሸቀልን እንደ ጥበብ ያዘው ማለት ነው? መፈንቅለ ተሃድሶ ከእሥር ቤት መብርሃቱ በእንተርኔት?
ሰዎቹ ነገር አሳምራለሁ ብለው በቃላቸው ከቀባጠሩት በበለጠ መረጃ ጥፈው ሰጥተል:በአዴፓ ለውጡ ሥር ነቀል ሳይሆን ሥር ተከል ነው!፡፡
Tesfa says
አቶ በለው – የምትለው ትንሽ ያምታታል። በምትኖርበት ሃገር ማርዋና ማጨሽ ይፈቀዳል እንዴ? በመሰረቱ በረከት የኢህአፓ አባል ነበር። ከጎንደር ክፍለ ሃገርም የወጣው በዛ ነው። በቅርብ ውድ ባለቤቱም ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገረቸው የልቡን በመናገርም ይታወቃል። ወያኔ አፈር ያልመለሰበት መለስ ጋር ባለው የጠበቀ ቀረቤታ ነው። በሌላ በኩል አቶ በረከት ያኔ እና አሁን ይህን በደል ፈጽሞአልና እሱም እንደ ሞሶሎኒ ተዘቅዝቆ ይሰቀል በሚለው የብቀላ ሃሳብ ጭራሽ አልስማማም። ሰው በጥፋቱ በህግ ይቀጣል፤ ያለዛም ይቅርታ ጠይቆ በምህረት ይለቀቃል። ይህ አንድ ጊዜ መትቶኛል እና እኔ ሁለት ጊዜ መምታት አለብኝ የሚለው የልጆች የብቀላ ፈሊጥ መገታት አለበት። በማቆያ ቤት ሆኖ ቢጽፍ፤ ቢናገር እሰየው ያሰኛል እንጂ ጨለማ ቤት እንጣለው ሰው አይጠይቀው ማለት በፍጽም ወስላታነት ነው። እንደ ጅሎቹ ወጣቶች በረከት ስሞኦን አለበት የተባለውን ሆቴል ያለምንም መረጃ ማጋየቱ ስሜታዊነት ነው። እንደዛም ሊቀጣ አይገባውም! ዛሬ በሃገራችን ያለው ችግር እናውቃለን የሚሉ መብዛታቸው ነው። አንድ ቀን እንደመር ብሎ ሰልፍ ይወጣል ሌላ ቀን በዘሩና በጎሳው በሃይማኖቱ ተሰልፎ ንብረት ይዘርፋል፤ ቤት ያቃጥላል። የተማታበት ትውልድ።
የበረከት በደል መርገም የሆነው በበረሃ ጎንደር (አርማጭሆ) ቆላማው የትግራይና የወሎ ክፍል፤ እትብቱ የተቀበረበትን ጎንደር በነበረው ከፍተኛ ስልጣን እንዴት ናቹሁ ምን እንርዳ አለማለቱም ነው። ስልጣን ጊዜአዊ ነው። ሃብትም ይበናል። በህዝብ የታቀፈ ወገን ግን ቤተሰቡንም ቢሆን እሱን ጧሪና ቀባሪ አያሳጣውም። ስለሆነም በኢንተርኔት በሚነዛ ያልተጨበጠና የተጨበጠ ወሬ ያንም ይህንም ስቀለው ከማለት ብንቆጠብ ተገቢ ይሆናል። የበረከት ጉዳይ በፍርድ እጅ ያለ በመሆኑ ፍርድን ለፍርድ ቤት መተው መልካም ነው። በረከት ራሱን ለፍጽም ኑዛዜ ካዘጋጀ ህዝባችን ይቅር ባይ ነው።
በለው ! says
ተስፋ ቢሶች ተስፋ አላቸው ለማለት ይከብዳል!
በረከት ኢህአፓ ነበር.”ውድ ባለቤቱም ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገረቸውየልቡን በመናገርም ይታወቃል”
*ድንቄም የልቡን የሚናገር ዘመነኛ (ባለግዜ) እንጂ ህጋዊ ሰው ማለት አደለም፡፡
“ይህ አንድ ጊዜ መትቶኛል እና እኔ ሁለት ጊዜ መምታት አለብኝ የሚለው የልጆች የብቀላ ፈሊጥ መገታት አለበት። በማቆያ ቤት ሆኖ ቢጽፍ፤ ቢናገር እሰየው ያሰኛል እንጂ ጨለማ ቤት እንጣለው ሰው አይጠይቀው ማለት በፍጽም ወስላታነት ነው።?
*ወስላታ ማለት ሌባ ማለት ነው!፡፡ አጭበርባሪ፡ ከአፈር ገፊ ድሃ ህዝብ ጉሮሮ እየነጠቀ ለፖለቲካ ሽርሙጥና የሚጠቀም አድርባይ!፡ኤርትራዊ ሆኖ ጎንደር አደጎ ለወያኔ (ወያናይት ሆኖ) የሚሸቅል ማለት ነው፡፡
“ዛሬ በሃገራችን ያለው ችግር እናውቃለን የሚሉ መብዛታቸው ነው። አንድ ቀን እንደመር ብሎ ሰልፍ ይወጣል ሌላ ቀን በዘሩና በጎሳው በሃይማኖቱ ተሰልፎ ንብረት ይዘርፋል፤ ቤት ያቃጥላል። የተማታበት ትውልድ።”
* ንብረት ማቃጠል፡ መዝረፍ፡ መግደል፡ዘቅዝቆ መስቀል፡ ግንድ ላይ አስሮ ማቃጠል፡ በቁም መቅበር፡ ወንድ መድፈር፡ ሀብት ማሸሽ፡ ዘረኝነትና ጎጠኝነትን ፈጣሪው ከኢህአፓ እስከ ኢህአዴግ የፈጠረው ያስተማረውና ተግባራዊ እንዲሆን ያደረገው እሱ ያለበት ቡድን ለዚህ ትውልድ ያወርሰው በረከት ነው፡፡ አንተም እንዲህ የማታወቀውን ሰው ልትዘልፍ ከእሱ የወረስከው ትምህርት አደለምን!?
” የበረከት ጉዳይ በፍርድ እጅ ያለ በመሆኑ ፍርድን ለፍርድ ቤት መተው መልካም ነው።በረከት ራሱን ለፍጽም ኑዛዜ ካዘጋጀ ህዝባችን ይቅር ባይ ነው።”
***ከተስፋ በረከት ስሞኦን እና ከበለው ለሕግ ቅርብ ማነው? በጥንቃቄ አንብበህ ተረዳ ወይም ጠይቅ አተላ ማይምን
mulugeta Andargie says
መሃላ ደረት ዓያሰፋም
የናንተ ጩሀትም ዓይሰማም
የቁራ ጩሀት ነውም