• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በማረፊያ ቤት ሰብዓዊ መብታች ተጥሷል”፤ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ በአግባቡና በሰዓቱ አይቀርብልንም – በረከትና ታደሰ

January 25, 2019 12:54 pm by Editor 3 Comments

በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉት በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሣ “በማረፊያ ቤት ቆይታችን ሰብዓዊ መብታችንን እና ክብራችንን የሚነካ ድርጊት ተፈጽሞብናል” በማለት ለፍርድቤት ቅሬታ አቀረቡ። ጉዳያቸው በአዲስ አበባ እንዲታይ ለፍርድቤቱ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ የአስራ አራት ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል።

በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም. በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ካለባቸው የጤና ችግር አንጻር በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ እንደሚመገቡ ገልጸው፤ ይሁንና በማረፊያ ቤቱ ምግብ በአግባቡ እና በሰዓቱ እንደማይቀርብላቸው ተናግረዋል። ለአብነትም ትናንት ምሳ በ10፡00 እንደቀረበላቸው ለችሎቱ አስረድተዋል።

የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባቸው እና ጡረታ በአግባቡ እንደማይወስዱም ነው ተጠርጣሪዎቹ የገለጹት። በባሕር ዳር ቤት እና ዘመድ ስለሌለን ቤተሰቦቻችን ከአዲስ አበባ ተመላልሰው ምግብ ለማብሰልም ሆነ ለማገዘ አይመቻቸውም ነው ያሉት።

በተጨማሪ በማረፊያ ጣቢያው ዙሪያ የተሰበሰቡ ወጣቶች “ወንጀለኛ፣ ሌባ እና ነብሰ ገዳይ በማለት ክብራችንን እና ህገ መንግስታዊ መብታችንን የሚነካ ድርጊት ፈጽመውብናል:: በከተማዋ ያለው ድባብ ለደህንነታችን እና ጉዳያችንን በደንብ ተከታትሎ ለመከራከር እክል ይፈጥራል፤ ስለሆነም የክርክሩ ጉዳይ አዲስ አበባ ይታይልን” ሲሉ ለችሎቱ አቅርበዋል። ችሎቱም የተጠርጣሪዎቹን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ ጉዳያቸውን በባሕር ዳር ሆነው እንዲከራከሩ ወስኗል።

“የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና አመራሮች ወንጀለኛነታችን ሳይረጋገጥ ጉዳዩን በማራገብ የደቦ ፍርድ እንዲደርስብን አድርገዋል” ብለዋል። ለአብነትም አቶ በረከት በደብረ ማርቆስ ከተማ በወጣቱ የደረሰውን ሁከት እና ግርግር አንስተዋል።

ጉዳዩን ያየው የባሕር ዳር እና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስፈላጊው ጥበቃ እና ክትትል ለተጠርጣሪዎቹ እየተደረገላቸው በባሕር ዳር ማረፊያ ቤት ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ወስኗል።

በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩና ጉዳዩ አዲስ አበባ እንዲታይላቸውም ጠይቀዋል። በምክንያትነት ደግሞ የጤና ችግርና የቤተሰብን ድጋፍ በቅርበት ለማግኘት በሚል አቅርበዋል።

ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ “ተመዘበረ” ካለው የሀብት መጠን ከፍተኛነት አንጻር ዋስትና እንዳይሰጣቸውና እንዲሁም የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በአማራ ክልል በመሆኑ ጉዳያቸው በባሕር ዳር እንዲታይ ለፍርድ ቤቱ ጠይቋል። ምሥክሮችን በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ስለሚያቀርብም የጉዳዩን በባሕር ዳር መታዬት ተገቢነት ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ የዋስትና መብታቸውን ከልክሎ በጥብቅ ጥበቃ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ወስኗል። የተጠረጠሩበት ወንጀል ከፍተኛ መሆኑን በመጥቀስ ዋስትና የከለከለው ፍርድ ቤቱ የተመዘበረው ሀብት በአማራ ክልል ስለሆነ ጉዳዩ መታዬት ያለበት በባሕር ዳር እንደሆነም ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

በጥብቅ ጥበቃ እንዲቆዩ ፍርድ ቤቱ የወሰነው ከነበራቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት አንጻር መሆኑንም ችሎቱ አስታውቋል።

የተጠረጠሩበትን ጉዳይ ዐቃቤ ሕግ አጠናክሮ እንዲያቀርብ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ የዛሬ ውሎውን ችሎቱ አጠናቅቋል። (ይህ የአብመድ ዜና የተዘገበው በቢኒያም መስፍን ሲሆን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ከራሱ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ አንጻር እንደሚፈልገው አቅርቦታል)

በሌላ ዜና ሰኞ ጥር 20 ቀን 2011ዓም ታትሞ የሚወጣው በኩር ጋዜጣ በወንጀል ተጠርጥረው ስለተያዙ የነ በረከት የክስ ጭብጥ በሌላ ወንጀል ለመጠየቅ ሂደቱ ዝግ አይደለም በማለት በፊት ገጹ ላይ ዘግቧል።

በሌብነት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት ሁለቱ ተጠርጣሪዎችን በተጨማሪ ወንጀሎች ለመጠየቅ ማስረጃ እስከቀረበ ድረስ ዝግ አለመሆኑን የጠቆሙት ጋዜጣው ያነጋገራቸው የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ኃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ ናቸው።

ግለሰቦቹ የተያዙት በሙስና ወንጀል እንጂ በፖለቲካዊ ጉዳይ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ምግባሩ ተጠርጣሪዎቹን እንደ አንድ ግለሰብ ለመክሰስ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በቂ ማስረጃ እስካቀረበ ድረስ ክስ መመሥረት እንደሚችል ገልጸዋል።

በርካታ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት በረከት ስምዖን ለሦስት ዐሥርተ ዓመታት ያህል ይዞ ከቆየው የተለያዩ ሥልጣኖች አንጻር በሙስና ብቻ ሳይሆን ከዚያ በተጨማሪ ለዓለምአቀፍ እና ለአገር ውስጥ የሚቀርቡ ሪፖርቶችን እጅግ በማዛባት፣ አፋኝ ሕግጋትን እንዲወጡ ከማርቀቅ ጀምሮ ተጽዕኖ በማድረግ፣ ለውጡን ለመቀልበስ በመሞከር፣ በዘር ማጥፋት፣ በሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ በጋዜጠኞች አፈናና ግድያ፣ ወዘተ ሊጠየቅ ይገባዋል ይላሉ።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: bereket, court, Full Width Top, kassa, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. gi Haile says

    January 25, 2019 06:58 pm at 6:58 pm

    መብታችን ተጣሰ? መቶ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን መብትና ነፃነት ረግጠው ሲገዙት የነበረው ምንም ሳይል እነሱ መብታችን ተነካ ብለው ሲጮሁ መስማት ያሳፍራል። ሲያስገርፍና ሲያስገድል የብዙዎችን ቤትና ቤተሰብ ሲያወድሙና ደም ሲያስለቅስ ሕዝብ ምን ኣለ? እንባውን አፍስሶ ለፈጣሪ አቤቱታቸውን አቀረቡ። በረከትና ሌሎች ወንጀለኞች የሰራችሁት በደል ቀአለም ታሪክና በኢትዮጵያውያን ወንድምና እህት የፈፀማችሁት ግፍ ጣሊያን እንኳን አላደረገውም። የሰላም ኣምላክ እናንተን ይፋረድ እንጂ ምድራዊ ፍትህ እንደማይመጣ እናውቀዋለን። የዘረፋችሁት ገንዘብ ለጠበቃ ሰለኣላችሁ ከኣምላክ ፍርድ ኣታመልጡም። ለናንተ ያለኝ ምክር ብሩን መልሱ አጥኣታችሁን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተናዘዙ ያን ብታደርጉ በምድርም በኣምላክ ዘንድም ምህረት ታገኛላችሁ። ያ ከልሆነ ደግሞ ሲዖል አፍዋን ከፍታ ልትውጣችሁ ትጠባበቃለች። ሰላም ለኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለአለም ሁሉ ይሁን።

    Reply
  2. Tena Lehulu says

    January 27, 2019 03:00 pm at 3:00 pm

    ዶ/ር አሚር የጤና ጥበቃው በረከት
    ባህር ዳር ተወልዶ ያደገ ከልጅነቱ በያዘው በባክቴሪያ በሚመጣ የልብ በሽታ ሲስቃይ የነበረና ፈለገ ህይወት ሆሰፒታል ለዘመናት ክትትል የነበረው
    ህክምና ትምህርቱን በጥቁር አምበሳ ሆስፒታል የተከታተለ ሲሆን በዘመኑ የበረከት ደቀ መዝሙርና በወያኔ ካድሬኔቱ እንዲታዎቅ የሚፈልግና በወያኔነቱ መምህሮችን ጭምር የሚያስፈራራ

    በልታይ ልታይ ባይነቱና በሰልጣን ወዳድነቱ በቴድሮሰ አድሃኖም ለጸረ ሀኪም ዘመቻው የተመለመለ። ለዚህም ከሰራውና ከውጤቱ የገዘፈ ከፍተኛ የሚዲያ ሸፋን የተስጠው (የሊሙ ገነት ህዝብና ጤና ባለሞያ ሰለ ድራማው ይመስክራል)
    ከጀማሪ ሃኪምነት ወደ የጤና ጥበቃ የስው ሃብት ዳይሬክተርነት ያደገ። ይህም ክፍል ልምድ ያላቸው ባለሞያዎችን ሞራል በመንካትና በማባረር ፈላጭ ቆራጭነቱን አሳይቶዋል። ከዚያን ወቅት ጀምሮ ለተፈጠረው የጤና ባለሞያ ትምህርት ጥራት መውደቅ፡ የምደባና ጥቅማ ጥቅም ኢ ፍትሃዊነት ግለስቡና በግል ጥቅም የስበስባቸው ጋሻ ጃግሬዎቹ ተጠያቂ ናቸው
    የጤና ጥበቃ የስው ሃብት ዳይሬክተር እያለ በሚያሽከረክረው የመንግሰት መኪና ስው ገጭቶ ቢገድልም በቴድሮስ አድሃኖም ድጋፍ በ ቱሌን ፕሮጀክት ወጪው ተሸፍኖ አሜሪካ ለአንድ አመት የሚሆን ተደብቆ ቆይቶ ተመልሶዋል። ለልብ በሽታውም በዚሁ ፕሮጀክት ወጪው ተሽፍኖ የተሻለ ህክምና አግኝቶዋል። (የቱሌን ፕሮጀክትና የአሚር የቡዙ ሚሊየን ዶላር ጨዋታ በሌላ ፖሰት እመለሰበታለሁ)
    ቴድሮስ አድሃኖም ወደ ውጭ ጉዳይ ሚንሰትርነት ሲዛዎር አሚር ወደ ሚንስትር ዲኤታነት በማደግ የኦፕሬሸን ዘርፉን (ፋይናንሰ፡ ግዥ፡ ሰው ሀብት፡ መስረተ ልማት፡ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ጠቅላላ አገልግሎት ከፍሎችን) የመራ ሲሆን እነዚህን ከፍሎች ከሲቪል ስርቪስ መመሪያ ውጭ የሱን ፍላጎት የሚያሙዋሉ ኣቅም የሌላቸው ኣቃጣሪዎች የስገስገ ሲሆን ቡድኑ በከፍተኛ ሰርቆት የተዘፈቀ ሲሆን ለአሚር ከፍተኛ ጥበቃ ያደርጋል። አሚር እነዚህን ሆድ አድሮች በመጠቀም የራሱን የሃስት ሰበእና የገነባ ሲሆን የተንኮል መረቡን በመዘርጋትም የሚንሰትሮችን ውድቀት በማፋጠን ሚንሰትርነቱን ሊቆናጠጥ ችልዎል።
    ከዚህ በተጨማሪም የሚንሰትር መሰሪያ ቤቱ የኢህአዴግ ድርጅት ጉዳይ ሃላፊ በመሆን የበረከት አስተምሮት የሆኑትን የትምክህት፡ ጠባብነት ሊቅና አስተማሪ የነበረ ሲሆን በመስሪያ ቤቱ ጸረ ኢህአዴግ በማለት ቡዙ ባለሞያዎችን ያሳስረ ሲሆን (ክርሲቲያን ታደለን 6 ወር እንዲታስር ያዘዘ) ሲሆን በተለይም መድሃኒት ፈንድ መሰሪያ ቤት በሱ ኔትዎርክ ቡዙ ብክነትና ዝርፊያ ተከናውኑዋል
    የጤና ጥበቃን በእርዳታ የተገኘ ገንዘብ ለሱ ጥቅም ለሚፈልጋቸውና ለሰልጣን ጥሙ መስላል ለሚሆኑ ድርጅቶችና ከፍተኛ ሓላፊዎች ለማስደስት ፍትሃዊ ያልሆነ ክፍፍል በማድረግ በስልጣን መቆየት የቻለ ሲሆን( ምሳሌ፡ በልጅነቱ ታሞ ህክምና ያገኘበት ፈለገ ህይወት ሆሰፒታል መጠነ ስፊ ችግሮች እንዳሉበት እያዎቀ ምንም አይነት ድጋፍ አላደረገም በአንጻሩ ለአይደር ሆሲፒታል 500 ሚሊዮን ብር ለጳውሎስ ሆስፒታል 2 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲስጥ አድርጎዋል። የአሚርን ጸረ አማራነት መቀሌና ድሬዳዋ ለምን መሄድ እንደሚዎድ በሌላ ጽሁፍ እመለስበታለሁ)
    አሚር ሚንሰትር ከሆነ ጀምሮ ከፍተኛ ልምድ ያላቸውና የመርህ ስው የሆኑ ከ16 በላይ ዳይሬክቶሮችና ከፍተኛ ሃላፊዎች ያለምንም ጥፋት የአይናችሁ ቀለም አላማረኝም በማለት ብቻ ከሲቪል ስርቪስ መመሪያ ውጭ በግፍ ያስናበተ ሲሆን በነዚህ ስዎች ምትክም ልምድና እውቀቱ የሌላቸው የሱ አምላኪ የሆኑ ሆድ አደሮችን ስግሰጎበታል።
    በአሚርና የሙሰና ቡድኑ ሰኬቶች
    ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበትና በተገቢው ሰራ ላይ ያልዋል የሊፍት፡ አወቶቢስና የፍተሻ መሳሪያ ግዥ
    እሰካሁን ድረስ በየ መጋዘኑ የተደበቀና ጥቅም ላይ ያልዋለው 30000 በላይ የጤና ኤክሰቴንሽን የብሰክሌት ግዥ
    በየ ጤና ተቁዋሙ የተበተነና ጥቅም የማይስጥ ሶላርና UPS (ከ 10000 በላይ)
    በጣም በውድ ዋጋ ከመንግሰት ካዝና ብር ወጪ በማድረግ በቱሌን ዩንቨርሲቲ አማካኝንት ተገዝቶ ለዩኒቨርሲቲዎች የተከፋፈለው 20000 ታብሌት
    በመስሪያ ቤቱ ለድግሰ በጥቅም የተስጠ ውልና ከተገቢው በላይ የተከፈለ የአገልግሎት ክፈያ

    የአሚር ስብዕና፥
    እይታውና አመልካከቱ የልጅ፡
    ሴስኛና ለዚህ ፍላጎቱ እሰከ ከፍተኛ ሹመት ለአልጋ ተጋሪዎቹ የስጠ
    ቂመኛና ለሱ የማይገዙትን ከማጥፋት የማይመለሰ
    እዮኝ እዮኝ የሚያበዛና የሱን ስብዕና ለመገንባት ታዋቂ የሚዲያ ስዎችን የገዛ

    አሚር እንደ በረከት የሰራወን የሚያገኝው መቼ ነው?

    Reply
    • አለም says

      January 30, 2019 10:28 pm at 10:28 pm

      ውድ ጤና ለሁሉ፣
      አሚር 30 ዓመት እድሜ፣
      ተመርቆ አንድ አመት ተኩል ብቻ በጤና ጣቢያ የሠራ፣
      ስድስት ወር በጤና ጥበቃ ሚንስቴር የበጀትና ፖሊሲ ኃላፊ፣
      ለአንድ ዓመት ያህል ምክትል፣
      ከዚያ ሚንስትር። አይገርምም?
      ዶ/ር አቢይ ላይ በተደረገው የግድያ ሙከራ የመጀሪያዋንና ብቸኛ
      ቲዊት ያደረገ።
      ቴዎድሮስ ሚንስትር በነበረ ወቅት የቢል ጌትስ ተላላኪ ነበር፤
      ቢል ጌትስ ዋና ዓላማው የወሊድ ቁጥጥር ነው፤
      አገራችን ከአፍሪቃ ሁለተኛዋ ነች በህዝብ ብዛት፣
      ጥቁር ህዝቦች እንደ ጥንቸል ተዋልደው አውሮጳንና ባህሉን እንዳይበክሉ ይል ነበር፤
      ቴዎድሮስ በጌትስ ሰበብ የህወኃትን ሥራ ሲሰራ ነበር፤
      ቢል ጌትስ ለዓለም ጤና ጥበቃ አበቃው፣ ቴዎድሮስ ብቃት ያለው ስለሆነ ሳይሆን
      ጥሩ ተላላኪ ስለሆነ ነው፤ የኢትዮጵያን ለአማን አሚር ሐጎስ በውርስ አስተላለፈ።
      ስለዚህ ቢል ጌትስ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ገደለ።
      ዶ/ር አቢይ ያለ ችሎታ የተሰየመውን አማንን ዞር ቢያደርግ እርግጠኛ ነኝ
      ቴዎድሮስ የጭቃ ጅራፉን ይዞ ብቅ ይላል።
      ጤና ለሁሉ፣
      ከስሜታዊነት የራቀ መረጃ አቅርብልንና አስተምረና!

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule