ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ ተጠርጥሮ በእስር ላይ የሚገኘው ጃዋር ሲራጅ መሃመድ የተከሰሰበት ጉዳይ “ፖለቲካዊ ነው፤ ይህ ችግር የሚፈታው ቁጭ ብሎ በመወያየት ነው” በማለት ለፍርድ ቤቱ ተናገረ። የወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል። ከጃዋር ጋር አብሮ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎችም ተጠርጣሪዎች ሐሙስ ዕለት ነው ልደታ ምድብ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እና አራዳ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት። ይህንንም ተከትሎ የጃዋር ጠበቃ ደንበኛቸው በዋስ ከእስር ቤት ውጪ ሆኖ ጉዳዩን መከታተል እንዲችል እንዲፈቀድለት ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ተቀብሎታል። በዚህ … [Read more...] about በወንጀል ተጠርጣሪው ጃዋር ለፍርድ ቤቱ፤ “ጉዳዩ ፖለቲካዊ ነው፤ የሚበጀው ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው” አለ
court
“በማረፊያ ቤት ሰብዓዊ መብታች ተጥሷል”፤ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ በአግባቡና በሰዓቱ አይቀርብልንም – በረከትና ታደሰ
በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉት በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሣ “በማረፊያ ቤት ቆይታችን ሰብዓዊ መብታችንን እና ክብራችንን የሚነካ ድርጊት ተፈጽሞብናል” በማለት ለፍርድቤት ቅሬታ አቀረቡ። ጉዳያቸው በአዲስ አበባ እንዲታይ ለፍርድቤቱ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ የአስራ አራት ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል። በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም. በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ ካለባቸው የጤና ችግር አንጻር በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ እንደሚመገቡ ገልጸው፤ ይሁንና በማረፊያ ቤቱ ምግብ በአግባቡ እና በሰዓቱ እንደማይቀርብላቸው ተናግረዋል። ለአብነትም ትናንት ምሳ በ10፡00 እንደቀረበላቸው ለችሎቱ አስረድተዋል። የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባቸው እና ጡረታ በአግባቡ … [Read more...] about “በማረፊያ ቤት ሰብዓዊ መብታች ተጥሷል”፤ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ በአግባቡና በሰዓቱ አይቀርብልንም – በረከትና ታደሰ