• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሃቀኛው መላኩ ፈንታ

May 28, 2018 10:53 am by Editor 8 Comments

መልከ ቀና ነው፤ ፀጉሩ እንደ መኸር ጤፍ ተኝቷል። ሲራመድ ይፈጥናል። ወደ ምኒሊክ ቤተመንግሥት እየገባ ነው። ገባ።

“አቶ መለስ ሦስት ምርጫዎች አሉኝ!” ቀጠለ።

አንድ ህግ ተክትዬ መሥራት፣ ሁለት እያስመሰልኩ መኖር፣ ሶስተኛ ሳልሰራ በሪፖርት መኖር!

አቶ መለስ በምርጫው ተደንቀው “በህግ ስራ፤ ማንም ከህግ በታች ነው” አሉት።

የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ንግግር ከራሱ እሳቤ ጋር ተጣጣመ።

የሚኒስቴር የቤተሰብ መኪና አልቀበልም ብሎ ቤተሰቡ በአዲስ አበባ የታክሲ ሰልፍ መያዝ ለመዱ። ቁርስ እና ምሳውን ከመስሪያ ቤቱ ካፍቴሪያ በ15 ብር እየተመገበ ሥራውን አጧጧፈ።

አንድ የክልል ቢሮ ኃላፊ ቢያንስ ሁለት መኪና እና መኖሪያ ቤት ይሰጠዋል። ለዚህ ሰው ግን የለውም ።በጭቃ ቤት ይኖራል። ሰውየው የገቢዎች እና ጉምሩክ ኃላፊ ነው። ሚኒስትር ነው። የሃገሪቱ ገንዘብ በመዳፉ ቢያልፍም ወደ ኪሱ አያስገባም። ሰውየው መላኩ ፈንታ ነው።

አንድ ቀን የአቶ በረከት ስምኦን ዘመድ በ3 ሚሊየን ብር ያለቀረጥ ካሜራ አስገባ። መላኩ ሆዬ አስወረሰው። አቶ በረከት ቢደውልም ወይ ፍንክች መላኩ ሆዬ።

መላኩ ሒልተን እና ሸራተን ሆቴልን አያውቋቸውም። አላሙዲ ስለ መላኩ ኩሩነት ሁሌም ይደነቃሉ። ለአላሙዲ ሚኒስትሮች ይሄዱላቸዋል እንጂ ራሳቸው ወደ ሚኒስትር ቢሮ አይሄዱም። አላሙዲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ብቻ ይገባሉ። ሌላ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት በገንዘባቸው እና በወኪላቸው ያስፈፅማሉ።ኩሩው አቶ መላኩ ግን ከአላሙዲ ጋር ሸራተን አልተገናኙም። ይልቁንም አቶ አላሙዲ በአቶ መላኩ ተደንቀው ወደ ቢሮአቸው አመሩ። አቶ መላኩ እና አላሙዲ እንደማንኛውም ደንበኛ ቢሮ ተገናኙ።ሲገናኙም መላኩ የተለየ መቅበጥበጥ አላሳየም። አቶ አላሙዲ በአቶ መላኩ ተደነቁ።

አቶ መላኩ ሲታሰር ከሚኖርበት የመንግሥት ቤት ቤተሰቦቹ እንዲወጡ መንግስት ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፈ። የአቶ መላኩ ቤተሰቦች ወደ ጎዳና ሊወድቁ ሲል በክብሩ የማይደራደር በመሆኑ ቀድሞም አድንቀውት ነበርና አቶ አላሙዲ ለአቶ መላኩ ቤተሰቦች ቤት ሰጧቸው። እስከዛሬም የሚኖሩት አቶ አላሙዲ በፈቀዱት ቤት ነው። አቶ አላሙዲ ጉዳይ ለማስፈፀም በብቸኝነት ሂደው የነበሩት ወደ አቶ መላኩ ቢሮ እንደሆነ ይነገራል።

2005 ዓም ከ3 ሺ በላይ አማራዎች ከቤሻንጉል ተፈናቅለው ፍኖተሰላም ላይ ከተሙ።

አቶ መላኩ “አማራው ሁነኛ ተወካይ የለውም። ሀገሪቱም አግላዋለች” ሲል በኢህአዴግ ጉባዔ ተናገረ። በብአዴን ውስጥ ትምክህት ቤቷን ገነባች ተብሎ ተወገዘ።

አቶ መላኩ በ 2000ዎቹ አካባቢ የአማራ ልማት ማኅበር ቴሌቶንን አቀናጅተው በቀን ከ 2 ቢሊየን ብር በላይ አሰብስበዋል። አማራው በኢኮኖሚ እንዲራመድ አማራ ባንክ እንዲከፈት አድርጓል። ይህ ባንክ በወቅቱ አማራው አማራ ሲሉት ብዙ ላይሞቀው ይችላል ተብሎ አባይ ባንክ ተብሏል። የደጀን ሲሚንቶ ፋብሪካ እና በደብረብርሃን ያሉ ውስን ፋብሪካዎች የአቶ መላኩ የጥረት ውጤቶች ናቸው።

ጎንደር ፒያሳ የዳግማዊ ቴዎድሮስን ሃውልት እንዲቆሞ አድርጓል። አቶ በረከት እና አቶ መላኩ ጎንደር ቀበሌ አንድ አብረው አድገዋል። የዳግማዊ ቴዎድሮስ ሃውልት ሲገነባ አቶ በረከት አሻራ ብዙ ባይኖራቸውም የኔ ስም ከአሰሪ ኮሚቴው ካልገባ ብለው ስማቸውን አሰፍረዋል።

የወገኑ ወደኋላ መቅረት የሚያንገበግበው አቶ መላኩ በ 2005 ዓም የብሄሮች በዓል በባህርዳር ሲከበር ከተማሪዎች ካፌ ሻይ በ50 ሳንቲም አብረን ተቋድሰናል። አቶ መላኩ ክብራቸው እውነት እንጂ ስልጣናቸው አልነበረም።

ግንቦት 5 ቀን 2005 ዓም ሙሰኛ ተብሎ ወደ ቃሊቲ ገባ። ከተከሰሰበት ገራሚ ነገር ውስጥ የወይዘሮ መቅደስ ለማ ጉዳይ ነው።

አቶ መላኩ ከወይዘሮ መቅደስ ሁለት ልጆችን ወልዷል። ቴዎድሮስ እና ፋሲል መላኩን። ነገር ግን የሰማንያ ሚስቱን በስልጣኑ ከሌላ ወንድ የነጠቃት ነው ተብሎ ተከሰሰ። የሁለት ልጆቹን እናት ባለቤትህ አይደለችም ተባለ።

ሌላው ሆቴል ሄደህ ሳሙና እና ሻወር ስልጣንህን ተጠቅመህ በነፃ ተጠቅመሃል የሚል ክስ ነበር።

እንዲሁም ባለቤትህን ደብረሊባኖስ ገዳም በመንግስት መኪና ወስደሃል ተብሎም ተከሶ ነበር።

መላኩ 5 ዓመት ሙሉ ያለ ብይን በእስር ቆየ። በአምስት ዓመቱ እስሩ ተቋረጠ። አቶ መላኩ እንደ እስክንድር ነጋ፣ እንደ ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከውጭ ወደ ሃገራቸው ገብተው ለሃገራቸው ሲሉ ዋጋ ከከፈሉ ብሩሃን መካከል ናቸው።

አብዛኛዎቹ መረጃዎች ከአቶ መላኩ አንደበት እና ከባለቤታቸው ከወይዘሮ መቅደስ የተወሰዱ ናቸው።

(ምንጭ፤ የሺሀሳብ አበራ ገጽ)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: bereket, eprdf, Left Column, melaku fenta, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Goche says

    May 29, 2018 08:21 am at 8:21 am

    ይገርማል! መልካም ሰው የማይከበርበት አገር፡፡

    Reply
  2. Aytalnew Newzendro says

    May 29, 2018 12:34 pm at 12:34 pm

    The truth should have been told in time so that we stand with him and shorten the suffering.

    Reply
  3. Whatsinaname says

    May 29, 2018 07:18 pm at 7:18 pm

    I doubt this story – it is just what the author says. First of all what is Melaku doing with EPRDF? How do we know he is not corrupt? Yes, he might felt Amhara people are disadvantage later on but to start with why join eprdf or its government – if there is a differece between the two. Also you said he didn’t get a government assigned house and then you say his family was kicked out of one. So Ala-moudi did that out of the kindness of his heart? I will find that heard to believe. When do we Ethiopians stop this cult status building of individuals? The whole story about Melaku is fishy.

    Reply
  4. Abcdef says

    May 30, 2018 01:49 am at 1:49 am

    This is a fake story. No one works with woyane if the do not have an impaired or opportunistic trait. Melak is no different. Stop covering up the truth. He was a woyane minister at the end of the day imprisoned or not. So what is all this trim a about? Was he as you said an honest man?

    Reply
  5. Ezira says

    May 31, 2018 12:51 am at 12:51 am

    ወይ አጋጣሚ ! ኮ/ል መንግስቱ ኃይለ ማርያም ሌ/ ኮ/ል አጥናፉ አባተን ካስገደሉ በኋላ ከነቤተሰባቼው የሚኖሩበትን የመንግስት ቤት በአስቼኳይ እንዲለቁ አስደርገው 8 ልጆቻቸዉን ሜዳ ላይ እንዲፈሱ ወይም እንዲበተኑ ማደረጋቸውን የያኔው ሕፃን ልጅ ዛሬ ግን የ5 ልጆች አባት የሆነው ሱራፌል አጥናፉ አባት (የሌ/ኮ/ አጥናፉ አባተ ልጅ ) አሳዛኝ ታርካቸዉን በቅርቡ ጽፎ አስነብቦናል። ይሄ ታሪክ የሁሉም ኢትዮጵያዊያኖች የመጥፎ ታሪካችን ጠበሳ ነው። ግን ግን ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አብረው ይበራሉ እንደተባለው ሁሉ በየትኛዉም አፍሪካ ውስጥ ያሉ ዲክታተሮች በህዝባቸው ላይ ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው። አይደንቅም? – የሁሉም አገር የፍሪካ ዲክታተሮች ባህሪ !

    Reply
  6. Tesfa says

    June 4, 2018 02:20 pm at 2:20 pm

    ከቀደመው ታሪካችን የዛሬው የሚለየው ጥላቻውና ሽኩቻው በዘር ላይ ያተኮረ መሆኑ ነው፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያዊነትን ይጠላል፡፡ በቅርቡ የወያኔው ባለሥልጣን ዶ/ር ደ/ጽዮን በመቀሌ በሰጡት መግለጫ ዶ/ር አቢይ እንደዚህ ከቀጠለ የትግራይ ህዝብ አንድ ነገር ያደርጋል። ምን ማለት ነው? ማንን ለማስፈራራት ነው? ወያኔ የቀን ለውጥን የማያይ እውር ድርጅት ነው። ዛሬ የሃገራችን ህዝብ ወያኔን አክ-እንትፍ ብሎታል። መዝባሪና የዘር ሰልፈኛን ጭራሽ ጠልቷል። የአቶ ለማ መገርሳን ድርጅቶ በአራተኛ ደረጃ ላይ ፈርጆ ራሱን አንደኛ ብሎ የሰየመው ወያኔ ህፍረት የማያውቅ ድርጅት ነው።
    በአቶ መላኩ ፈንታ ላይ የደረሰውም ግፍ ከወያኔ የክፋት ኮሮጆ እየተቆነጠረ የሚዘራ መርዝ ነው። ሰው ለእውነት በእውነት የማይኖርባት ሃገር! አቶ በረከት ሻቢያ እንጂ ወያኔም አይደለም። ልቡ አስመራ ቂጡ አዲስ አበባ ነው። ደግሞስ በቃኝ ካለ በህዋላ ዛሬ ተመልሶ በወያኔ ሥር በመሆን ህዝባችንን የሚያምሰው ለምን ይሆን? ወያኔ ሙሉ ታህድሶ በማድረግ ህዝብ ለመረጠው ሥልጣን ያስረክባል ብለው ለሚያምኑ የፓለቲካ ጅሎች የምለው አንድ ነገር ነው። የቅርቡን የጄ/ል ሳሞራንና(ወይን ጋዜጣ) ና በመቀለ የዶ/ር ደ/ጽዮንን ቃለ መጠየቅ መጣጣም በቂ ይሆናል። አፍቃሪ ወያኔ የሆኑ ድህረ ገጾች የሚለፉትን ማየት ተገቢ ነው። በሃገር ውስጥ ታዋቂ የነበረው “በረከት መንግሥተአብ” ስለትግራይ ዘፈን አወጣ ይለናል አንድ ሾተላ የወያኔ ድህረ ገጽ ጡሩምበኛ። ይመስለኛል ወያኔ በጎን ከኤርትራ ጋር ድርድር ጀምሯል። ይመቻቹሁ።

    Reply
  7. sewnet says

    June 5, 2018 09:49 pm at 9:49 pm

    እስክዛሬ በሌሎች ስናይ የነበረው ዘረኝነት በአማራውም ማየት ጀምረናል። አማራ በመሆኑ ብቻ መላኩ እንዲፈታ ከተፈታ በሁዋልም መኪና እንዲሸልም ሁኖዋል። ይገርማል!
    እኔ እንደማየው ይህንን የሚያደርጉት እንዳውም በመላኩ ሙሰኝነት ተጠቃሚ የሆኑ አይቀሩም እላለሁ።

    Reply
  8. Tesfa says

    June 6, 2018 11:37 pm at 11:37 pm

    አቶ ሰውነት – እንደ ሰው በሰው ከሥር መፈታት ደስ ሊልህ/ሽ ይገባ ነበር። ያው ግን ወያኔና የተለጣፊዎች በሽታ ተስቦ ነው፡፡ ዞሮ ተመልሶ ሰውን በዘር ማሰለፍ። በወያኔ ያለ ቅጥ ሃበሳ የቆጠረው ወገን የአማራው ህዝብ መሆኑ ቢታወቅም ሌሎች የሃገራችን ህዝቦችና በየአደባባዮ ወያኔ ቆመንለታል የሚሉትና በስሙ የሚነግዱበትን የትግራይ ህዝብ ሳይቀር ለመከራ ዳርገዋል። እኔ ለሰው መኪና የምሸልምብት ሃብት የለኝም። ግን ቡና ወይም ሻሂ ለማለት እበቃለሁ። ያው እንኳን ተፈታህ ዳግም እንዳይጠልፉህ ተጠንቀቅ ለማለት። በወያኔ ዘመን ከእሥር መፈታት የመኖር ዋስትና አይደለምና። እንዲሁ ግን በቅርበትም ሆነ በርቀት ከእውነት ጋር ባልተገናኘ ነገር ሰውን መወንጅል ተገቢ አይደለም። ሙስና ስጪና ተቀባዮም ያው እኩል ወንጀለኞች ናቸው። ይህ መቆም ያለበት ነገር እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን። ከአቶ መላኩ የመኪና ሽልማት ጋር ግን የሚያገናኘው ነገር ያለ አይመስልም።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule