አልሸባብ ጋልሙዱግ በሚባል ክልል ከሶማሌ ጦር ጋር ባደረገው ውጊያ ሶስት የሶማሊያ ጦር ካምፖችን በቁጥጥሩ ስር አድርጓል። አል ሸባብ ከሶማሊያ ጦር ጋር አምስት ሰዓታት ያህል የቆየ ከባድ ጦርነት ካካሄደ በኋላ ከጥቃቱ የተረፉ የሶማሌ ብሄራዊ ጦር የ"ጎርጎር ኮማንዶ" መኮንኖችና ወታደሮች እንደተናገሩት በውጊያው ከ230 በላይ የሶማሊያ ወታደሮች መሞታቸውን እንዳረጋገጡና ስፍር ቁጥር የሌላቸው መቁሰላቸውን ገልፀዋል። የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር በቦታው ያሰፈራቸው ወታደሮቹ 4 ሻለቃ የ"ጎርጎር ኮማንዶዎችን" ሲሆን 15 የአል ሸባብ አሸባሪዎች ጋር ባደረገው ውጊያ ከፍተኛ ሞትና የአካል ጉዳት አስተናግዷል።የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር በአል ሸባብ ከበባ ውስጥ ሆኖ ምንም ዓይነት የሽፋን ኃይል ማሰማራት አልተቻለውም ተብሏል።ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ በአል ሸባብ የሽብር ቡድን ላይ … [Read more...] about አል ሸባብ ሦስት የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ካምፖችን ተቆጣጠረ
al shabab
“ቄሮ አልሸባብ” ነው – ህወሓት!
“ስድስት ሚሊዮን ወጣት በጠላትነት ፈርጀህ ማንን ልታስተዳድር ነው?” ለማ መገርሳ ህወሓት/ኢህአዴግ በኢትዮጵ የተለያዩ ክፍሎች በተለይም በምሥራቅ ሐረርጌ “ቄሮ” በመባል የሚታወቅ ሕገወጥ እንቅስቃሴ እመረምራለሁ፤ ለፍርድ አቀርባለሁ ብሎ ዝቷል። “አመራሩ ብቃት የለውም” በማለት ራሱን የገመገመው ህወሓት/ኢህአዴግ ብቃት አልባነቱን ተገንዝቦ ራሱን ከሥልጣን ማግለል ሲገባው አሁንም የማሰርና የማሰቃየት ግፉን በስፋት ለመቀጠል በዕቅድ ለመቀንቀሳቀስ ማሰቡን ነው በዚህ ዜና የገለጸው። የኢትዮጵያ ወጣቶችን በሥራ በማሰማራት ለአገር እንዲጠቅሙ ከማድረግ ይልቅ “አደገኛ ቦዘኔ” በማለት ሲፈርጅና ሲስር የነበረው ህወሓት አሁን ደግሞ በኦሮሞ ወጣቶች “ቄሮ” ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ለመሰንዘር ጎራዴውን እየሳለ ነው። ግፉ የበዛባቸው ወጣቶች ታላቁ ሩጫ በተካሄደበት ባንድ ወቅት ላይ “አደገኛ ቦዘኔ … [Read more...] about “ቄሮ አልሸባብ” ነው – ህወሓት!