• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

መልስ ለዶ/ር በያን አሶባ ቃለ መጠይቅ

January 5, 2018 09:00 am by Editor 3 Comments

የተከበራችሁ አንባቢያን፤

ይህችን መጣጥፍ ለመከተብ የተነሳሁት የዶ/ር በያን አሶባን (የኦሮሞ ዴሞክራሲ ግንባር ቃል አቀባይ) ቃለ መጠይቅ ካደመጥኩ በኋላ ነው፤ አመለካከታቸው ብዙ መልካም አስተሳሰቦችን በውስጡ ያካትታል፤ መልካም የምላቸው አመለካክቶች የኢትዮጵያ ችግር መፈታት ያለበት እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑ፤ መሰረታዊ ለውጥ ማስፈለጉ፣ በሙሉ እከሌ ከእከሌ ሳይባል የፖለቲካ እስረኞች የመፈታትን ሃሳብ፣ የውጭው ትግል አጋዥነት እንጂ መሪ ቦታ መያዝ እንደማይገባው፤ የሚሉትን ሲሆን ትልቁ ተቃውሞዬ ወያኔን የሽግግሩ አካል ማድረጉ ላይ ነው፤ (በሰላምና እርቅ ሰበብ) ፍራቻቸው ወያኔ አጓጉል አወዳደቅ ከወደቀ አገሪቱ የማትወጣበት ችግር ውስጥ ትገባለች ነው፤ {አገሪቱ የማትወጣበት ችግር ውስጥ ከገባች ሰንብታለች}።

ወደ በያን አሶባ ማንነት ስመለስ ለዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ በመለሱት ደብዳቤ እራሳቸውን ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ ፡ Even pupils used to be coerced by their teachers to dump the names originally given to them by their parents and to assume a new in order to start the process of qualifying as an Ethiopian. It is this practice of demanding that individuals need to first die as Oromos, Sidamas, Walayitas, Kambatas, Hadiyas, etc. in order to be reborn as Ethiopians that sits at the heart of the political contestation in that country. And so long as being an Oromo and an Ethiopian are made incompatible, we have no choice but to either reject your Itophiyawinnet or suffer the imposed self-abnegation…. Beyan H. Asoba 5/29/13

ወደ አማርኛ ስንመነዝረው ተማሪዎች በአስተማሪዎቻቸው በወላጆቻቸው የተሰጣቸውን ስም ትተው ኢትዮጵያዊነትን ሊያሟላ የሚችል ስም እንዲያወጡ ይገደዳሉ፤ የዚህ አይነቱ አሰራር ነው እንደ ኦሮሞ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ከምባታ ሀዲያ ያሉ ማንነቶች ሞተው እንደ ኢትዮጵያዊ እንዲወለዱ የሚያስገድደው፤ ስለዚህ ኦሮሞነትና ኢትዮጵያዊነት አብረው ስለማይሄዱ ወይ ኢትዮጵያዊነትን አሽቀንጥረን እንድንጥል አሊያም እራሳችንን ንቀን እንድንጥል እንሆናለን ይላሉ።

ጣሊያን አሁን ያላትን ቅርጽ ስትይዝ (ስትዋሃድ) በ 1861 መሆኑ ነው ዘመናዊ ጣሊያንኛን የሚናገረው ሕዝብ ቁጥር ከኗሪው 2.5% ነበር፤ ለዚህም ነው ከውህደት ታጋዮቹ አንዱና ዋንኛው ማሲሞ ዳዜሊዮ (Massimo d’Azegglio) ጣሊያንን መሰረተን ጣሊያኖችን ማዘጋጀት አለብን ያሉት።

ይህንን ምሳሌ መጥቀሴ አገር ሲመሰረት አካባቢውን የያዘው ሕዝብ ባህሉን፣ ቋንቋውን አመለካከቱን የያዘው አካባቢ ላይ እንዲሰራጭ ያደርጋል፤ ይህ የአሰራር ልምድ ሁሉም አገሮች ሲመሰረቱ የነበረ ነው፤ በአጼ ምኒሊክ ላይ ኢትዮጵያን ለማዋሃድ ያደረጉትን ጥረት በተጋነነ ሁኔታ ሲኮንኑ ይሰማል ፤ (አቦሳም የምኒሊክ Conquest የምኒሊክን ድል የኦሮሞ መሬት መውሰድ ማለታቸው ነው) ከግራኝ መሐመድ ወረራ በፊት የአማራ ግዛት የነበሩ በርካታ ቦታዎች በኦሮሞ ከተያዙ በኋላ ባሕላቸውም ሆነ ቋንቋቸው ስማቸውም ጭምር የኦሮሞዎች ሆኗል፤ {ፈጠጋር – አሩሲ፣ ደዋሮ– ጨርጨር፣ ወጂ– ሐይቆችና ቡታጅራ፣ ዳሞት – ወለጋ፣ ግራሪያ – ሰላሌ፣ እናሪያ -ኢሊባቡር፣ ቤተ አምሐራ – ወሎ፣ ሽንብራ ኩሬ – ቢሾፍቱ….የተሰመረባቸው የቀድሞ ስማቸው ነው በኦሮሞ ከመወረራቸው በፊት} (ተጨማሪ መረጃዎችን የኢትዮጵያ ታሪክ ከአቶ ከይልማ ዴሬሳ ህዳር 20/1959፤ የአጼ ሓይለስላሴ ታሪክ ከበሪሁን ከበደ መስከረም 21/1993 ሊያገኙ ይችላሉ)።

ይህንን እውነታ ግን ዛሬ አማራ ተነስቶ ከግራኝ በፊት የኔ ነበርና ቦታዬን መልሱ አይልምም ሊልም አይገባም የጨርጨር (የደዋሮ) ተወላጅ የሆኑት ዶ/ር በያን አሶባ የቀድሞው የኦነግ አመራር የነበሩ ናቸው፡{እራሳቸውን ሲገልጹም የኦነግ ውጤቶች ነን ይላሉ} በድርጅቱም ከተራ አባልነት እስከ ማእከላዊ ኮሚቴ ሃላፊነት ደርሰዋል፤ ይህ ድርጅት ከወያኔ ጋር በመመሳጠር በርካታ አሰቃቂ ወንጀሎችን የፈጸመ ድርጅት ነው፤ ኦነግን ከመካብ ባለፈ ስለሰራችው አሰቃቂ ወንጀሎች የጠቀሱት ነገር የለም፤ “በምኒሊክ ኮንከስትም ቢሆን ከ፻ አመት በላይ አብረን ኖረናል” ይላሉ ዶ/ር በያን፣ ካለፈው ድርጅቴ ያሁኑን የሚለየው ኦሮሞን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹንም ያካተተ መሆኑ ነው፤ እኔን የሚደንቀኝ ለምንድን ነው ጎሰኞች የኢትዮጵያን ታሪክ ለነሱ ከሚመች ግዜ የሚጀምሩት፤ በአስራስድስተኛው ምእተ አመት አባ ባሕርይ ስለ ኦሮሞዎች የደረሱትን ዜናሁ ለጋላን ቢያነቡ ታሪኩን ሊረዱት ይችላሉ፤ መጽሐፉ በፐሮፌሰር ጌታቸው ሓይሌ በ 1995 ተተርጉሟል።

ወደ ተነሳሁበት አጀንዳዬ ስመለስ ለሚቀጥለው ለዘላቂው ሰላም ወያኔ መካተት አለበት ላሉት፣ የወንጀሉንም ተካፋይ ኦነግንም (የሚያሞግሱት የቀድሞ ድርጅታቸው) ስለሚጨምር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሕዝብ የሚያውቃቸውን እውነቶች ለማካፈል ነው።

የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ ለማስታወስ ያህል

  • December 2003 ፣ 424 አኙዋኮች (ጋምቤላ) ሲገደሉ 1600 አኙዋኮች ወ ደ ሱዳን ተሰደዋል፤ (This report is based on studies by the International Human Rights Clinic at Harvard’s Law School, UNICEF Ethiopia, Human Rights Watch, the United States Department of State )ይህንን ጭፍጨፋ እንዲካሄድ ያደረጉ የወያኔ ባለስልጣናት ዛሬም የድሎት ሕይወታቸውን እየቀጩ ነው፤
  • በወያኔ መንግስት በራሱ ሪፖርት መሰረት በ 2007 በተደረገው ቆጠራ የአማራው ሕዝብ ቁጥር በ 2.5 ሚሊዮን ከተገመተው ቀንሷል፤ የተቀረው ጎሳ በ2.7% ሲያድግ የአማራው ቁጥር ግን በ1.7% ነው ያደገው፤ ምክንያቱን ግን ለማውቅ ጥረት አልተደረገም፤ ከተለያዩ ጥናቶች እንደምንረዳው ለሕዝቡ የመድሃኒቱ ምንነት ሳይነገረው የወሊድ መቆጣጠሪያ መድሃኒቶች ለወጣት ሴቶች በግዳጅ እየተሰጠ እንዲመክኑ ተደርጓል፤ ይህም የአማራውን ሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ የተደረገ የወያኔ ሻጥር ነው፤
  • በምራብ ሐረርጌ በሁለት አመት ግዜ ውስጥ ከ 40.000 ስዎች በላይ መተከል (ቤንሻንጉል ጉሙዝ) ተጨፍጭፈዋል፤ በተቀረው አካባቢ ከ 10 እስከ 20000 አማሮች ተገድለዋል፤
  • አማሮች ከደረሰባቸው ጭፍጨፋ ሌላ ከተለያዩ አካባቢዎች እትብታቸውን ከቀበሩበት፣ ካደጉበት ቦታ ያለምንም ፍርድ ያፈሩትን ሃብት ጥለው እንዲሰደዱ ተዳርገዋል፤ ቤታቸው ንብረታቸው ተቃጥሏል፤ 1990/91 ከምራብ አሩሲና ምስራቅ ሸዋ 60000 አማራ፤
  • በ 2000 አ.ም . 14000 ሰው ከወለጋ፤
  • በ 2013 ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፤

ይህ ሁሉ ግድያና ጭፍጨፋ ሲካሄድ በሟቹ መለስ ያለው አስተዳደርም ሆነ ያሁኑ ወያኔ ምንም አይነት እርምጃ ካለመውሰዱም ሌላ እንዲያውም በድብቅ ይረዳና ያበረታታም ነበር፤

  • በቅርቡ ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) የኢሬቻን በአል ለማክበር የተሰበሰቡ የኦሮሞ ተወላጆች በተደረግው ጭፍጨፋ ከ 500 በላይ የንጹሕ ኦሮሞዎች ደም በወያኔ ወታደሮች ደመ ከልብ ሆኖ ቀርቷል፤
  • ርዋሳ ከደጋው ወልቃይት ጠገዴ ወረድ ብሎ የሚገኝ መንደር፤ በ 1986 ከ 500 ቤቶች በላይ እንዲቃጠሉ ተደርጎ ኗሪዎቹ ከተባረሩ በኋላ በ 1988 አዲስ ኗሪዎች ከትግራይ መጥተው እንዲሰፍሩ ተደርጓል።
  • ታህሳስ 30/1982 አሶሳ በኦነግ 365 አማራዎች (ሴቶችን፣ሕጻናትን፣ሽማግሌዎችን ጨምሮ) ተገድለዋል፤
  • 1984 ወለጋአንፊሎ ወረዳ 627 አማራዎች ተገድለዋል፤
  • 1984 አርባጉጉ 96 አማራዎች ተገድልዋል፤
  • ከ 1986 ጀምሮ ከዋልድባ ገዳም ድንበር ጀምሮ የተከዜ ወንዝ ኢያካለለው ወደ ምእራብ እስከ ሱዳን ድንበር የተንጣለለው እጅግ ለም በሆነው መሬት በመዝጋ ወልቃዪት ነዋሪ የነበሩትን የወልቃይትና ጠገዴ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ይህን ለም መሬት እንዲለቁ ተደርጎ ዛሬ አካባቢው በ ትግራይ ባለቤትነት ይተዳደራል፤
  • በአዋጅ የህዝብ ፍላጎት ሳይጠየቅ የወልቃይት‹የጠገዴና የጠለምት ወረዳዎች በትግሪኛ ተናጋሪነት ሽፋን የትግራይ ክልል እንዲኦኑ ተደርጓል፤

{አንድን ሕዝብ ሆን ብሎ ከቀየው ማፈናቀልና የሌላ ጎሳ ተወላጆችን በምትኩ ማስፈር በዘር ማጥፋት (Genocide) ደረጃ የሚፈረጅ የዘር ማጽዳት (Ethnic cleansing) ወንጀል መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ይደነግጋል፤Ethnic cleansing is the systematic forced removal of ethnic or religious groups from a given territory by a more powerful ethnic group, often with the intent of making it ethnically homogeneous.[1][page needed] The forces applied may be various forms of forced migration (deportation, population transfer), intimidation, as well as mass murder and genocidal rape.}

  • ሙሰኝነትን አስመልክቶ ስናይ ታላላቅ የወያኔ ጀኔራሎች ያካበቱት ሃብት የአደባባይ ምስጢር ነው ( ለምሳሌ እነ ሌ/ጄ ጻድቃን፣ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ፣ ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ፥ ሌ/ጄ ገዛኢ አበራ፣ እያለ ይቀጥላል፤ የወታደር ቤቱን ስልጣን ስናይ አገሪቱ ውስጥ ሌላ ጎሳ የሌለበት ይመሰላል፤ በ1989 በአቶ መለስ ዜናዊ ትዛዝ በአዲስ አበባ ቦሌ አንደኛ ደረጃ መሬት 500 ካሬ ሜትር እንዲሰጣቸው ከመደረጉ ሌላ ብዝበዛው ያለምንም እንከን እንዲካሄድ አስተካክሎላቸዋል፤ እነዚህም ለሆዳቸው ያደሩ ጀኔራሎች ዋናው ተልኮአቸው ወያኔን ለዘለአለም ስልጣን ላይ ማቆየት ነው፤
  • በውጪው አለም ከድሃዋ ሃገራችን ዘርፈው ለመስማት የሚሰቀጥጥ የብር መጠን ያካባቱ {ሟቹ መለስ ዜናዊ፣ አምባሳደር ብርሃኔ ገ/ክርስቶስ፣ አባዲ ዜሞ፣ ስብሃት ነጋ፣ የተሰደደው ተፈራ ዋልዋ፣ ሽመልስ ክዴ፣ አዲሱ ለገሰ፣ አባይ ጸሃዬ፣ ገነት ዘውዴ…….

እነዚህ ለአብነት ያህል የተጠቀሱ እንጂ ሙሉ መጽሐፍ ሊወጣው የሚችል ግፍ ያካሄደውን ወያኔ የለውጡ አካል ማድረግ በግል እምነቴ ትክክል አይደለም፤ በኦነግ ስር ይህንን ወንጀል የፈጸሙ በአዲሱ ማህበር ስም ስማቸውን ማጽዳትም አይችሉም፤ ዶ/በያን አቦሳም ለዚህ ሁሉ ኦነግ ለፈጸመው ወንጀል፣ ወንጀልነቱን አምነው፣ ይቅረታ ጠይቀው መለወጣቸውን በተግባርም ቢያሳዩን በአዲሱ አመለካከታቸው ላይ ቅሬታ አይኖረኝም፤

በኔ እምነት አብረን መኖር እንድንችል ሊሆን የሚገባው

1. ድርጅቶች በኢትዮጵያውነት ስር መሰባሰብ ይገባቸዋል፤ አማራው የኦሮሞ ደም የኔ ደም ነው፣ ኦሮሞው ጣና ኬኛ እያለ አብሮ ለመኖር ትግሉን ሲያካሄድ ለግል ጥቅማቸው የሚሯሯጡ ፖለቲከኞች የዘር-የጎሰኝነትን ወሬ ማራገብ ሊያቆሙ ይገባል፤ መረሳት የሌለበት ከ 80 በላይ ቋንቋዎች የሚነገርባት ታላቅ አገር መሆኗን ነው፤የተለያየ የፖለቲካ ፕሮግራም ያላቸው ድርጅቶች ሁሉንም ጎሳ ያካተተ ራእይ ሊነድፉ ይገባል፤

2. ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ጎሳዎች ሁሉ በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ የመኖር፣ የመዘዋወር፣ ሃብት የማፍራት፣ የመነገድ ወዘተ እኩል መብት ሊኖራቸው ይገባል፤ የመብት መሰረቱ በግለሰብ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት፤ ሁሉም ሃይማኖቶች የእኩል መብት ሊኖራቸው ይገባል፤ ግለሰቦች የሌላውን መብት እስካልተጻረሩ ድረስ የትኛውንም ሃይማኖትም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት የመቀበል መብት ሊኖራቸው ይገባል፤

3. ኢትዮጵያ ብዙ ብሄሮችን እንዳካተተ ትልቅ አገር አንድ የጋራ ቋንቋ ሊኖራት ይገባል፤ በአሁኑ ሰአት በብዛት የሚነገረው ቋንቋ አማርኛ ነው (ጎንደር፣ ጎጃም፣ ከፊል ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ በመላው አገሪቱ በሚገኙ የከተማ ኗሪዎች፣ በመንግስትና በግል መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ ሰራተኞች)፤ ይህ ቋንቋ በብዛት መነገሩ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን መላ አፍሪካን ሊያኮራ የሚገባ የራሱ የሆነ (ግእዝ) ፊደላትና ቀን መቁጠሪም ስለአለው አመቺነቱ የማያጠራጥር ነው፤

4. ሌሎች በብዛት የሚነገሩ የአገሪቱ ቋንቋዎች በያሉበት አካባቢ እንደሁለተኛ የስራ ቋንቋ የሚያድጉብት መንገድ መፈለግና ስራም ላይ እንዲውሉ ጥረት መደረግ አለበት

ታዛቢው ነኝ ከሆላንድ (kasbeg@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: amhara, eprdf, Ethiopia, Left Column, olf, oromo, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. aradw says

    January 10, 2018 01:51 am at 1:51 am

    This is very interesting note. I am not here in any way to defend Dr. Asoba. Knowing him, he is absolutely capable of defending himself. But I can guarantee you he has no time to read and even if he read it, I do not think he will respond to this unworthy comment. As a person of frequent reader, I observed how people deal with current situation., specially when the country is on a cross road and all of Ethiopians and friends of Ethiopia are struggling to find any applicable solution. ታዛቢው ከሆላንድ (since there is no name) is trying to bring things that has no relation to the topic in hand an old intellectually discussions between Dr. Asoba and Dr. Tolossa and use it here for a hatred he has for the Oromo and the Oromo movement. I can guarantee him if he ask both gentlemen (Asoba and Tolossa) today, they will lough with his comment as an outdated thinking. Today is a different time when the Kerro from Oromia and Fano from Amhara hand in hand are fighting the TPLF dictators. Writing this divisive piece is briging more division than anything else. . We must be careful what we read. Here is a poison spit when things are different and changing. It is time for creating bridge and closing the gap that was wide opened by TPLF between the Oromo and Amhara. I am not an apology of OPDO but the OPDO under the leadership of Mr Lemma Megerssa are trying to bring the two leading nationalities together to fight TPLF and it is early to say but a right direction forward.
    Secondly here the author mentions the crimes of Woyane as hindrance to include them in future negotiation. This is again a divisive mechanism obstacle to unity and stability of the nation. Mr. Asoba never said criminals will be included. The Woyane criminals will get there time in peoples court under the new Ethiopia. Just a reminder to the writer, the situation and reconciliation in South Africa. Peaceful transition is hard until forgiveness is included.

    Reply
    • Berhanemeskle k says

      January 10, 2018 12:33 pm at 12:33 pm

      aradw…if you have a confidence just write your name and defend what is right and logically explain
      what is missing from the writers well written critic. But you are trying to see the future with out learning from the past. unless we come close to see the division and hatred of the past we can’t move forward to a brighter future. if you have time try to spent few hours to see the past speech’s and written documents of OLF members. They don’t have a common agenda for the oromo’s let alone for Ethiopia. They are the one who divided the country in two pieces with the Eritreans liberation front and the woyanies. still they are working with the same group who created the division and hatred in Ethiopia. The old and the new OLF member’s knew that they don’t win the heart and mind’s of the Ethiopian people as OLF. so they changed their name to ODF but in a dirty mind and soul full of hate to the Ethiopian history. As I told you just listen to the Eritrean president and the former OLF members speech to Ethiopia and other ethnic groups. It is full of hate and inferiority complex. They don’t have the will and heart to understand twenty first century political economy. That is why it took them almost fifty years to win the heart and mind of Ethiopian people. I am not writing for woyane or any other political group but I am just saying it is better to learn from our past and design a bright future so our kids can enjoy peace.

      Reply
      • aradw says

        January 10, 2018 10:39 pm at 10:39 pm

        Dear Berhanmeskel:

        You are asking my confidence, but you forgot the person who wrote the article. The article I replied is also the same written with ታዛቢው ነኝ ከሆላንድ (kasbeg@gmail.com) with no name. Secondly, it is not that much important to have name, the most important is the content. Thirdly, let us concentrate on the current situation more than trying yo deal with the past. Please note, I understand the past because I look the past with open mind and also with the the situation at the time in mind (the 1960and 70). At the time the country was in a big revolution from all side, EPRP, MAISON, Derg, OLF, TPLF, EPLF, EDU. Here you are pointing some of the rhetoric of the past. The statement you have here as “It is full of hate and inferiority complex.”.. They don’t have the will and heart to understand twenty first century political economy” This is baseless and one can not expect from a learned man like you. It will be nice to refrain from this type of writing since it is not our culture and it does not help for our unity and integrity. It is a common thing or a common talk “learn from the past” cliche. We all learn from the past but the problem is how we see the past. Here we are absolutely different in looking the past and history will soon judge what happened then in the 1960and 1970.
        There is a lot to say but I will refrain since it is not the time. We are now in a different but an environment of Unity and decisive struggle to throw the dictator TPLF. This is the time to talk, write things that brings us together that spending time to the thing that widens the gap we had. At home in most part of the country people are saying your blood is my blood and hand in hand fighting the dictators, including in Arat Kilo in the hiding place of TPLF. As a mattter of fact I am not a fan of OPDO and ANDM but now I see some positive things are coming out and we have to critically support them instead of bring the past and refrain from support.

        Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule