ገዱ አንዳርጋቸው በምሁራን መድረክ ያድረጉት የመክፈቻ ንግግር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበራችሁ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች! እንኳን ወደ አማራ ክልል መዲና ውቢቷ ባህርዳር ከተማ በሠላም መጣችሁ! ከነገሬ ሁሉ በማስቀደም የአማራ ክልል መንግስት እና ህዝብ የጐደለውን ትሞሉለት ዘንድ ምክራችሁን እና የሙያ ድጋፋችሁን በመሻት ለልጆቹ ያደረገውን ይህን ታሪካዊ ጥሪ ያለምንም ማቅማማት ተቀብላችሁ እዚህ በመካከላችን በመገኘታችሁ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ። በረጅሙ የሃገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የአማራ ህዝብ በስልጣኔ፣ በተለይም በመንግስት አስተዳደር፣ በታሪክ፣ በኪነ-ጥበብ፣ በስነ-ፅሁፍ፣ በአርበኝነት ተጋድሎ እንዲሁም በኢኮኖሚ ዕድገት ለሃገር ያበረከተው ድርሻ ትልቅና አይረሴ ቢሆንም ያለፈው ግማሽ ምዕተ-ዓመት … [Read more...] about “በመንግስት አመራር ውስጥ ‘እኔ አውቅላችኋለሁ’ የሚል ደዌ ተጠናውቶን ቆይቷል” አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
gedu
ጠባብነት እና ትምክህት
ከ2 አመት በፊት፦ ጠባብነት እና ትምክህት ኢህአዴግ እንደ ፓርቲና መንግስት የችግሮች ሁሉ መንስዔ አድርጎ የሚወስደው የጥገኝነት አስተሳሰብና ተግባራትን ነው። ለህዝቡ ሰላም እና ለፌደራል ሥርዓቱ አደጋ ናቸው ከሚላቸው ውስጥ፡- ጠባብነት እና ትምክህተኝነት የሚሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ። እነዚህ ቃላት በመንግስት ድክመት ምክንያት ለተፈጠሩ ችግሮች ሌሎችን ተጠያቂ (externalize) ለማድረግ ነው። በመሠረቱ “ትምክህተኛ” የሚለው እሳቤ የአማራ ብሔር ተወላጆችን በባህላቸውና በታሪካቸው ላይ ያላቸውን የራስ መተማመን ስሜት የሚሸረሽር ነው። በዚህ መልኩ የሚደረገው ተፅዕኖ በአማራ ልሂቃን ላይ የማንነት ቀውስ (identity crisis) ይፈጥራል። በዚህ መሰረት፣ አንድ ሰው በአማራነቱ ብቻ “ትምክህተኛ” እየተባለ ታሪኩና ማንነቱ እንደ ጥፋት ሲቆጠር በውስጡ የብሔርተኝነት ስሜት … [Read more...] about ጠባብነት እና ትምክህት
የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!
በእርግጥ ፖለቲካ ማለት ልክ "Bicycle" ነው። ሁልግዜም በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል መሽከርከር አለበት። ለውጥና መሻሻል ከቆመ ልክ እንደ "Bicycle" ፖለቲካዊ ስርዓቱም ተንጋሎ ይወድቃል። ህወሓት የማይለወጥ የፖለቲካ ቡድን ከመሆኑም በላይ ሌሎች እንዳይለወጡ የሚያደርግ ፀረ-ለውጥ ቡድን ነው። ስለዚህ ይህ ቆሞ-ቀር ቡድን የሌሎችን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያለመታከት ጥረት ያደርጋል። በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥና መሻሻል ጠፍቶ መንግስታዊ ስርዓቱ ለመውደቅ እየተንገዳገደ ባለበት ወቅት እንኳን ህወሓት በኦህዴድ መሪነት የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ላይ-ታች ሲል ነበር። አዲሱ የኦህዴድ አመራር ወደ ስልጣን እንደመጣ የወሰደው የለውጥ እርምጃ ፀረ-ለውጥ አቋም ከሚያራምደው የህወሓት ቡድን ራሱን ማላቀቅ ነው። በዚህ ረገድ የክልሉ ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ … [Read more...] about የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!
ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!
ህወሓት የሚዘውረው ኢህአዴግ ከሁለት ሳምንታት በላይ ስብሰባ አድርጎ “መግለጫ” ያለውን “ቀጭን ትዕዛዝ” በማውጣት ተጠናቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በለውጥ አራማጅነት ሲጠቀሱ የነበሩት እነለማ መገርሳ “መግለጫውን” አብረው አጽድቀው ወጥተዋል። “የጨለንቆን ፍጅት የፈጸመው ማነው?” የሚለውም ደፋር አጀንዳ አብሮ የሞተ ጉዳይ ሆኗል። “ምን ይዤ (ወደ ሕዝቤ) ልመለስ?” በማለት ወደስብሰባው የገቡት ኦህዴድና ብአዴን “የተቀናጁ ተጨማሪ እርምጃዎች” እወስዳለሁ (መግደሌን እቀጥላለሁ) ለሚለው የህወሓት “መግለጫ” ይሁንታቸውን ሰጥተው ወጥተዋል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከወር በላይ ስብሰባ በማድረግ የደቆሰውና የፈጨውን በተስፈኞቹ ብአዴንና ኦህዴድ ላይ በመድፋት በድንፋታ ኢህአዴግ የሚለውን የድርጅቱን ሥራ አስፈጻሚ መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁ ከራሱ ከአገዛዙ የሚዲያ ተቋማት … [Read more...] about ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!
የገዱ አንዳርጋቸው ፈተና
በህወሓት ተመልምለውና ለሥልጣን በቅተው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ “የለውጥ ኃይል” እየተባሉ ከሚወደሱት መካከል አንዱ የሆነው ገዱ አንዳርጋቸው ለምስክርነት መጥሪያ ተቆርጦለታል። ገዱና ሌሎች ህወሓት እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ የሠራው ብአዴን አባላት የተጠሩት በነ ንግሥት ይርጋ ክስ በመከላከያ ምስክርነት ነው። ህዝባዊ ዓመጹ የተነሳው “በመልካም አስተዳደር ችግር” ምክንያት እንደነበር እነ ገዱ በተደጋጋሚ በየሚዲያው ሲናገሩ ቆይተዋል። ዓቃቤሕግ ደግሞ ክሱን የመሠረተው ሕዝባዊ ዓመጹን ከ“ሽብር” ጋር በማገናኘት ነው። በ“ለውጥ ኃይልነት” ሲወደስ የነበረው ገዱ አንዳርጋቸው ታማኝነቱ ለማን እንደሆነ በይፋ የሚያሳይበት ፈታኝ ወቅት ላይ የሚገኝ ሲሆን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች “አንገቱ ላይ ያለውን ገመድ ለማጥበቅ በህወሓት የታቀደ ሤራ ነው” ብለውታል። በተለይ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ደመቀ መኮንን … [Read more...] about የገዱ አንዳርጋቸው ፈተና
በ’ርግጥ በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል ጥላቻ፣ በደልና ቂም በቀል አለ?
የትላንቱ እንቅፋት፣ ዛሬም ይመታናል የትላንቱ ገመድ፣ ዛሬም ይጠልፈናል ፤ ሰምተንም - አልሰማን፣ ሳሰማም ሰምተናል አይተንም - አላየን፣ ሳናይም አይተናል ላለመማር - መማር እኛ ተምረናል። አሁን… አሁን ''ከልሂቃኑ እስከ ኢ-ልሂቃኑ'' ድረስ፤ ቀድም ብሎ ሙሰላዊያንና ሂተለራዊያን፤ ካለፉት ሃምሳ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ሻአቢያዊያንና ወያኔያዊያን እንዲሁም ኦነጋዊያን ከባንዳ አያቶቻቸውና አባቶቻቸው የተቀበሉትን የፈጠራና የጥላቻ ታሪክ ስላወሩትና የስልጣን ኮርቻውን ስለተፈናጠጡት፤ የሚንናገሩትና የሚጽፉት ሁሉ እንድ ዕውነት ተቆጥሮ ፤ “በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል ጥላቻ፣ በደልና ቂም-በቀል አለ!" መባሉ ነው። ሌላውን ሁሉ ትተን ባለፉት 26 ዓመታት ብቻ ሻአቢያዊያን፣ ወያኔያዊያንና ኦነጋዊያን የሰሩትን ግፍና በደል፣ የዘሩትን ጥላቻና በቀል ብናስብ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ 'ርስ-በርሱ … [Read more...] about በ’ርግጥ በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል ጥላቻ፣ በደልና ቂም በቀል አለ?