• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!

May 2, 2018 08:38 pm by Editor 5 Comments

በእርግጥ ፖለቲካ ማለት ልክ “Bicycle” ነው። ሁልግዜም በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል መሽከርከር አለበት። ለውጥና መሻሻል ከቆመ ልክ እንደ “Bicycle” ፖለቲካዊ ስርዓቱም ተንጋሎ ይወድቃል። ህወሓት የማይለወጥ የፖለቲካ ቡድን ከመሆኑም በላይ ሌሎች እንዳይለወጡ የሚያደርግ ፀረ-ለውጥ ቡድን ነው። ስለዚህ ይህ ቆሞ-ቀር ቡድን የሌሎችን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያለመታከት ጥረት ያደርጋል። በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥና መሻሻል ጠፍቶ መንግስታዊ ስርዓቱ ለመውደቅ እየተንገዳገደ ባለበት ወቅት እንኳን ህወሓት በኦህዴድ መሪነት የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ላይ-ታች ሲል ነበር።

አዲሱ የኦህዴድ አመራር ወደ ስልጣን እንደመጣ የወሰደው የለውጥ እርምጃ ፀረ-ለውጥ አቋም ከሚያራምደው የህወሓት ቡድን ራሱን ማላቀቅ ነው። በዚህ ረገድ የክልሉ ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ የወሰዱት እርምጃ እንደ ማሳያ ሊጠቀስ ይችላል። ቅርበት ካላቸው ሰዎች በተደጋጋሚ ጠይቄ እንደተረዳሁት፣ የአቦ ለማ የስልክ ግንኙት ሲያደርግ የነበረው በቀጥታ ከቀድሞ ጠ/ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ እና በጎንዮሽ (horizontally) ደግሞ ከቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ኣይተ አባይ ወልዱ ጋር ብቻ ነበር። ከዚያ ውጪ እንደ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋና ሳሞራ ዬኑስ የመሳሰሉ የህወሓት ፈላጭ-ቆራጭ አመራሮችን ስልክ አያነሳም። በአካል ወደ ለማ ቢሮ ሲሄዱም እንደ ማንኛውም ሰው ተፈትሸውና ትጥቃቸውን ፈትተው ነው። በአጠቃላይ ከኦቦ ለማ ጋር የሚነጋገሩት በድርጅቱ ኢህአዴግ ወይም በጠ/ሚኒስትሩ አማካኝነት በተጠራ ስብሰባ ላይ ብቻ ነው።

የፈለጉትን ሰው በፈለጉት ቦታና ግዜ ጠርተው ቀጭን ትዕዛዝ በመስጠት የሚታወቁት የህወሓት መሪዎች እንደ ለማ መገርሳ ያለ ትንታግን  በይፋዊ ስብሰባ ላይ ማሳመን ሆነ ማስፈራራት አይችሉም። የለማ ቡድን (TeamLemma) በሚል ከድርጅቱ ኦህዴድና ከኦሮሞ ልሂቃን ለለውጡ አስፈላጊው ብቃትና ቁርጠኝነት ያላቸውን ሰዎች መርጦ በዙሪያው አሰባሰበ። በዚህ መልኩ አዲሱ የኦህዴድ አመራር ከህወሓቶች ቁጥጥርና ጫና ራሱን ነፃ በማውጣት የለውጡን ንቅናቄ በራሱ መንገድ መምራት ጀመረ። በጥቅሉ የለማ ቡድን ልክ ቄሮዎች፣ መሪው ኦቦ ለማ መገርሳ ደግሞ ልክ እንደ የቄሮዎቹ መሪ አቦ ጀዋር መሃመድ ከህወሓቶች ክትትልና ቁጥጥር ውጪ ሆነው እንደነበር መገንዘብ ይቻላል።

የለማ ቡድን ወደ 20ሺህ የሚጠጉ እስረኞችን በምህረት መልቀቁ ይታወሳል። በመቀጠል የክልሉ አድማ በታኝ ፖሊስ ሙሉ በሙሉ ከክልሉ ህዝብ ጎን እንዲቆም አደረገ። በዚህ መልኩ የክልሉ አመራርና የፀጥታ መዋቅር እንደ ቀድሞ የህወሓት መገልገያ መሆኑ አበቃ። ከዚህ በተጨማሪ ኦቦ ለማ ወደ ባህር ዳር በመሄድ ከአማራ ክልል እና ህዝብ ጋር ያለውን አንድነትና ትብብር ለማጠናከር መንቀሳቀስ ጀመረ።በብአዴንና እህደዴ የተጀመረው ትብብር ወደ ምሁራንና የህዝብ-ለህዝብ ትብብር እያደገ መጣ። በዚህ ምክንያት በፍርሃትና በመለያየት ላይ የተመሠረተው የህወሓት የበላይነት ተፍረከረከ። የህወሃት አመራሮችና ልሂቃን “መርህ አልባ ጉድኝት” በማለት ያጣጣሉት ትብብር የህወሓትን የበላይነት ለመገርደስ የሚያስችል ጥርስ አወጣ።

ህወሓቶች የኦህዴድና ብአዴን አመራሮችን እንደ ቀድሞ መለያየትና ማስፈራራት ሲሳናቸው ያላቸውን የመጨረሻ አማራጭ ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ አወጡ። ቅርበት ካላቸው የኢህአዴግ ባለስልጣናት ባገኘሁት መረጃ መሠረት የዕቅዱ ዋና አዘጋጅ አስር (10) ሺህ ዶላር አበል ተከፍሎት ከአሜሪካን ሀገር የመጣ ነባር የህወሓት አባል ነው። ጥቅምት 21/2010 ዓ.ም “አይጋፎረም” በተሰኘው ድረገፅ ላይ “የኢህአዴግ የመፍረስ አደጋና የኢትዮጵያ ቀጣይ እጣ ፋንታ” በሚል ርዕስ ባወጡት ፅሁፍ የህወሓት/ኢህአዴግን ዕቅድ እንደሚከተለው ገልፆታል፡-

 “… ኢህአዴግ ለህዝቡና ለዓላማው የሚቆረቆር ከሆነ ለግለ–ሰዎች ዝና መበገር የለበትም። ህዝበኞች እንደሆነ የአንድ ሳምንት አጀንዳ ከመሆን አያልፉም። ስለሆነም በተጨባጭ መረጃ የተገኘባቸው በቀጥታ ወደ ቃሊቲ እንዲወርዱ ማድረግ የተለያየ የፖለቲካ ሴራ የፈፀሙ ግን ደግሞ ተጨባጭ መረጃ ከሌለ መረጃ እስከሚመጣ መጠበቅ ሳይሆን ፖለቲካዊ እርምጃ መውሰድ። … ይሄ ተጠናክሮ በሚሄድበት ይህን ስርዓት ማስቀጠል የሚፈልግ ህዝብና አገር ወዳድ በርካታ ስለሆነ ከነዚህ ሆዳሞችና ከሃዲዎች በኋላ የሚፈጠር ስጋት አይኖርም።” 

ከላይ በተገለፀው መሠረት “በኢህአዴግ” ስም የህወሓትን የበላይነት ለማስቀጠል ያለው ብቸኛ አማራጭ በድርጅቱ ውስጥ የለውጥ ንቅናቄ የጀመሩትን የእህዴድና ብአዴን አመራሮች በማሰር ወደ ቃሊቲ መላክ ነው። ለዚህ ደግሞ ህወሓቶች አንድ ቅድመ-ሁኔታ አስቀምጠዋል። ይኸውም የተነሳውን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በድጋሚ ማወጅና ሀገሪቱን በወታደራዊ ሃይሉ ቁጥጥር ስር ማዋል ነው።

በዚህ መሠረት በመጀመሪያ በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል ላይ ብቻ ተግባራዊ የሚሆን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለማወጅ ሞከሩ። አልተሳካም! ቀጠሉና “ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት” በማለት በእጅ አዙር የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ለማወጅ ሞከሩ። እሱም ተግባራዊ ሳይሆን ቀረ። ከዚያ በኋላ ስልታዊ ማፈግፈግ አደረጉና 17 ቀናት የፈጀውን የኢህአዴግ ስብሰባ አደረጉ። በዚህ ስብሰባ ላይ የህወሓቶች ዓላማ አንድና አንድ ብቻ ነበር። እሱም የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጅና “ህዝበኞች” ያሏቸውን የኦህዴድና ብአዴን አመራሮች ለቃቅሞ ማሰር ነው።

በተጠቀሰው ስብሰባ ላይ በኦህዴድና ብአዴን አመራሮች ከተነሱት ጥያቄዎች ውስጥ “የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ” የሚለው ይገኝበታል። በወቅቱ ኦቦ ለማ መገርሳና ዶ/ር አብይ አህመድን በጉያቸው አቅፈው ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ኦቦ በቀለ ገረባን ማሰር ለህወሓቶች ፋይዳ የለውም። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና አቶ ንጉሱ ጥላሁንን ከጎናቸው አስቀምጠው እስክንድር ነጋ እና አንዷለም አራጌን ማሠር ለእነሱ ፋይዳ-ቢስ ነው። በአንፃሩ እነዚህን የፖለቲካ እስረኞች መፍታት በሀገር ውስጥ ሆነ በውጪ በሚገኘው ማህብረሰብ ዘንድ ትልቅ ፋይዳ አለው። ህወሓት ግን ተቃዋሚ ፖለቲከኞችን የሚፈታው “ህዝበኞች፥ Populist” ያላቸውን የኦህዴድና ብአዴን አመራሮች ለማሰር ነው። በዚህ መሠረት ህወሓቶች “እሺ … የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ። ነገር ግን፣ አመፅና ሁከት ከተነሳ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ይታወጃል” የሚል የድርድር ሃሳብ አቀረቡ። እስረኞችን በማስፈታት የህዝቡን ጥያቄ የመለሱ የመሰላቸው የኦህዴድና ብአዴን አመራሮች በሃሳቡ ተስማምተው ስብሰባው ተጠናቀቀ።

በዚህ ስምምነት ተቀናቃኞቹ ህወሓትና ኦህዴድ ሁለቱም የተሳሳተ እሳቤ ነበራቸው። ኦህዴዶች “ምንም አይነት አመፅና ሁከት በሌለበት ህወሓቶች የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አያውጁም” የሚል የተሳሳተ እሳቤ ነበራቸው። ህወሓቶች ደግሞ “ዋና መጠቀሚያቸው የሆኑት ጠ/ሚኒስትር ያለ እነሱ ፍቃድ ከስልጣን አይወርዱም” የሚል እሳቤ ነበራቸው። ነገር ግን፣ ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ከህወሓቶች የሚደርስባቸውን ዛቻና ማስፈራራት ተቋቁመው መልቀቂያ አስገቡ። ህወሓቶች “እንገድልሃለን” ብለው እስከማስፈራራት ደርሰው የነበረ ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩ ደግሞ ለሁለት ቀናት ያህል ፀሎት እንዲደረግላቸው እስከመጠየቅ ደርሰዋል።

የጠ/ሚ ሃይለማሪያም መውረድ ህወሓቶችን በፍርሃትና ጭንቀት ያራዳቸው በሁለት ምክንያት ነው።

አንደኛ፦ ሃይለማሪያም ሲወርድ ህወሓቶች መተኪያ የሌለውን መጠቀሚያቸውን ያጣሉ፣
ሁለተኛ፦ ኦህዴዶች በጥብቅ የሚሹት ቦታ ለውድድር ክፍት ይሆናል።

በመሆኑም በሁለቱም መልኩ ሚዛኑ ወደ ኦህዴድ ያዘነብላል። ስለዚህ ህወሓቶች ያላቸው ብቸኛ አማራጭ በ17ቱ ቀን ስብሰባ ያገኟትን ካርድ በመምዘዝ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጅ ነው። እንደሚታወሰው ምንም አይነት አመፅና ሁከት በሌለበት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አወጁ። አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውድቅ ቢደረግም አይናቸውን በጨው አጥበው ሀገሪቱን በወታደራዊ ዕዝ ለመምራት መንቀሳቀስ ጀመሩ።

የአዋጁ ዓላማ፤ እንደ ቱቦ የሚያገለግላቸውን አዲስ ጠ/ሚኒስትር መምረጥ እና “ህዝበኞች” ያሏቸውን የኦህዴድና ብአዴን አመራሮች ወደ “ቃሊቲ” መላክ ነው። ለዚህም አዲሱ ጠ/ሚኒስትር ከመመረጡ ቀደም ብለው ዋና ዋና ላሏቸው የኦህዴድ አመራሮች የእስር ማዘዣ ቆርጠው ይጠባበቁ ጀመር። ምን ያደርጋል ታዲያ! ብአዴን ጆከሩን ለኦህዴድ አሳልፎ በመስጠት ህወሓትን ጨው አደረገው። እነሆ አብይም ጠ/ሚኒስትር ሆኖ ተመረጠ። ህወሓቶች ለእነ አብይ ያወጡት የእስር ማዘዣ በብአዴን የጆከር ጨዋታ ከንቱ ሆኖ ቀረ።

ስዩም ተሾመ

ምንጭ፤ Ethiopian Think Thank Group by Seyoum Teshome

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: abiy, andm, Full Width Top, gedu, hailemariam, lemma, Middle Column, opdo, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Ayu says

    May 4, 2018 05:54 am at 5:54 am

    It is true Ato Team Lemma is a radical person. We need his radical actions ASAP

    Reply
  2. Tesfa says

    May 4, 2018 01:31 pm at 1:31 pm

    በሃገራችን ታሪክ ውስጥ ሶስት አጥፊ ሃይሎች ምድራችን አተራምሰዋል፡፡ ከዚህ ቀዳሚው ሃይል ሻቢያ ነው፡፡ ቀጣዮ የሻቢያ ተቀጥላ የሆነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሲሆን የመጨረሻው ደርግ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በሃገሪቱ የረጅም ታሪክ እንደ ወያኔ ያለ አጥፊ ሃይል ተፈጥሮ አያውቅም፡፡ ወያኔ ከድርቡሽና ከጣሊያን ወራሪ ሃይል የከፋ ነው፡፡ ህዝባችን በጎሳ/በቋንቋ/በሃይማኖትና በጎጥ ከፋፍሎ ሁሉም ነገር ወደ ትግራይና ለትግራይ በማለት ለመቁጠር የበዙ የሃገሪቱ የቁርጥ ቀን ልጆችን ከምድሪቱ በተለያየ ሴራ አስወግዷል፡፡ በማስወገድም ላይ ይገኛል፡፡
    ቀን ነገሮችን ይለውጣል፡፡ በኦሮሞና በሌሎች የሃገሪቱ ክፍል የተቀጣጠለው ተቃውሞ አልገታ ሲለው ወያኔ በሃሳብ የላላ ከክፋት የራቀ መስሎ የሚታያቸው ልበ ቢስ ፓለቲከኞች ባይታለሉ ይሻላል፡፡ አቶ ለማ ላይ ምናምንቴ ነገር በስብሰባ መካከል የወረወረው አባይ ፀሃዪ ከእኔ በላይ ላሣር የሚለው ሳሞራ እና አንድ እግሩ መቃብር በር ላይ ያለው በእርጅና ዘመኑ እንኳን የልብ ርህራሄ የሌለው የሻቢያ አቀንቃኝ አቶ ስብሃት ነጋና ሌሎችም ከበረሃ እስከ ከተማ ክፋትና ማፍረስን የተቃመሱ የወያኔ ጥምር ሃይሎች ዛሬም አልተኙም።
    አቶ ለማና አጋሮቹ የኢትዮጵያ ሃብት ናቸው። እንዲህ ዓይነት አርቆ አሳቢ ሰው ከኦሮሞ ህዝብ መካከል ዘልቆ መውጣቱም አያስደንቅም። ድሮም ነበሩ፤ ዛሬም አሉ። ወደፊትም ይኖራሉ። የሻቢያን የመገንጠል ጽዋ የተቃመሱ አንዳንድ ጠባብ የኦሮሞ ብሄርተኞች እንደሚያናፍሱት ወሬ ሳይሆን የኦሮሞ ህዝብ ራሱ ተከብሮ የሌላውን አክብሮ የኖረ በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደር ህዝብ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ለሃገሪቱ አንድነትና ህብረት የሚታገሉትን ሁሉ ዘር ጎሳና ሃይማኖት ሳይለህ ድጋፍና ጥበቃ ሊያደርግላቸው ይገባል። ወያኔ በአመድ የተዳፈነ እሳት ነው። ቀን ጠብቆ ጥቃት ማድረሱ አይቀሬ ነው። ህዝባችን ለሃገር አንድነት የቆሙ ወገኖቻችን ሁሉ ከሰውርና ከይፋ ጥቃት የመከላከል ሃላፊነት አለበት።

    Reply
  3. tesfalem says

    May 4, 2018 03:40 pm at 3:40 pm

    ትጃጃለለህ አቶ ስዩም ስንት አመት የሰማነው የናንተ አዛማሪነት

    Reply
  4. Eyerus says

    May 6, 2018 08:21 pm at 8:21 pm

    ለማከብርህ ለትግራይ ወገኔ በሙሉ!!!

    ጆሮ ያለው ይስማ!!!

    (ለህወሓት አቃጆች)

    ግራም ነፈሰ ቀኝ፣
    ሕወአት ዎች አትሁኑ ሞኝ፣
    ምክሬን ስሙ ወዳጃቹህ ነኝ፣
    ብትሆኑም እንኳ የቀለዳችሁብኝ፣
    እኔን ኦሮሞውን ከአማራው ጋር ያጣላችሁኝ፣
    ለእኔ ለሌንጮው ንግግራችሁ እውነት መስሎኝ፣
    በአብሮ አደጌ አማራው ላይ ሰይፍ ያስመዘዛችሁኝ፣
    አትችሉምና ከእንግዲህ ልታሞኙኝ፣
    ሴራውን ሁሉ ላፈርስ ከተበደለው ጋር በመሆን ተነሳሁኝ፣
    ከተጸጸታችሁና የተለመደ ሴራችሁን ካቆማችሁልኝ
    እኔም ለሐገር አንድነት ስል እርግፍ አድርጌ ልተው የበደላችሁኝን!
    ቃል ልግባ በእግዚአብሄር ፊት የምትተውት ከሆነ አጭበርባሪነታችሁን!
    ለእናንተም እንዲሆነላችሁ ከራበው አንበሳ በእውነት መዳን!
    እባካችሁ ስሙኝ የሚበጀው ይህ ነውና ለሁላችን!
    ይቅርባችሁ እድሜ ለማርዘም የምትውጡት የማዘናጊያ ክኒን!!!!
    እስቲ ቆም ብላችሁ አስቡ በስሙ ለምትነግዱበት የትግሬ ወገን???
    አያሳዝናችሁም በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠልቶ ሲባዝን???
    ይዤያችኋለሁ ከእግዚአብሔር በላይ በምትወዱት አቡነ አረጋይ!
    አስተውሉ!ተመከሩ!ተመለሱ!ለልጆቻችሁ አስቡ!ሳይጫናችሁ አፈርና ድንጋይ!!!

    እህታችሁ
    እየሩስ ነኝ!!!

    Reply
  5. zianziad says

    May 29, 2018 07:38 am at 7:38 am

    መጪዉ ግንቦት 20 ከእግሬ በታች(ተግሬ) በኢትዮጵያ ታርክ የተናቀዉ ከዳተኛዉ ቡድን የበታተናቲን ሀገርን ሊሰበስቡ የተወዳጁ ሀገር ወዳድ ትዉልድ ለ ዶ/ር አብይ፤ ለለማ መገርሳ እና ለጌዱ የሚንሮጥበት ሀገር አድን የሩጫ ቀን ወይም የአብይ፤ ለማ እና የጌዱ ቀን ቢንሌ ደስተኛ ነኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule