የተከበራችሁ የጎልጉል አንባቢያን፤ ለወራት ጠፍተን በመቆየታችን ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን። አንዱና ዋንኛው ምክንያት ድረገጻችን በማደስና የምናትማቸውን ጽሁፎች ባዲስ መልክ ለማድረስ እየሠራን ስለነበር ነው። ሥራው በፈቃደኝነት የሚሠራ በመሆኑ ካሰብነው ጊዜ በላይ ቢወስድብንም ባሁኑ ጊዜ በመጠናቀቅ ይገኛል። በቅርቡ አዲሱን ድረገጻችንን እናስተዋውቃለን። እስከዚያው ግን እዚሁ ላይ እንደተለመደው መረጃዎችን ማተማችንን እንቀጥላለን። በተደጋጋሚ ለጠየቃችሁንና መልዕክቶች ለላካችሁልን ምስጋናችን የላቀ ነው። ከልብ እናመሰግናለን። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ። በኢትዮጵያ ከፖለቲካው ቀውስ በማያንስ መጠን የኢኮኖሚው መላሸቅ፣ የሥራአጥነትና ድህነት የሚያስከትሉት አደጋ አሳሳቢና አደገኛ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ። የለውጡ ኃይሎች ለውጡን በሚያደናቅፉ ላይ ፈጥነው እርምጃ አለመውሰዳቸው … [Read more...] about ህወሓት ወደ ስልጣን ለመመለስ የሎቢ ሥራውን ዳግም ጀምሯል
abiy
አማራና ትግራይ ክልሎች ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ?
ሰሞኑን በአማራና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረው የመግለጫ እሰጥ አገባ ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ እንዳይቀየር ፍርሃቻ አለ። የኤርትራው መሪ ኢሳያስ አፈወርቅ ወደ አማራ ክልል ለጉብኝት መምጣታቸው በህወሓት አቀንቃኞች ዘንድ በፍርሃቻ እየታየ ነው፤ ሌሎች የዘር ፖለቲካ አራማጆች ደግሞ ጉብኝቱን ስህተት ነው ብለውታል። የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቅና የሱማሌው ፕሬዚዳንት ሙሐመድ አብዱላሂ ፎርማጆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግብዣ ዛሬ በአማራ ክልል ጉብኝት ለማድረግ ጎንደር ገብተዋል። ይህ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው ጉብኝት የጎንደርና አካባቢውን ታሪካዊ ቦታዎች ለመመልከትና በባህር ዳር ውበት ለለመሰጥ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በተለይ ኢሳያስ በተደጋጋሚ በትግራይ አመራር ላይ ካሉት የህወሓት ሰዎች የቀረበላቸውን የወዳጅነት ጥያቄ ችላ በማለት ከህወሓት ጋር … [Read more...] about አማራና ትግራይ ክልሎች ከቃላት ጦርነት ወደ መሣሪያ መማዘዝ?
ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!
አፍቃሪ ህወሓት የሚዲያ ተቋማት የማኅበራዊ ድረገጽ ተዋናዮቹን ጨምሮ “ቀለበት ውስጥ ገብተናል” በማለት የተጀመረውን ለውጥና ከኤርትራ ጋር የተያዘውን አስደማሚ የሰላም ሂደት ሲቃወሙ ሰንበተዋል። አሁንም ምክንያት በመለጣጠፍ እየተቃወሙ ነው። ድርጅታቸው ህወሓት የአልጀርሱን ስምምነት ያለ ቅድመ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን በሙሉ ድምጽ አራት ኪሎ ላይ ከወሰነ በኋላ ትግራይ ገብቶ ውሳኔውን የማያውቀው እስኪመስል ድረስ እየሸራረፈ ሲቃወም ሰንብቷል። በመጨረሻ ባወጣው መግለጫ የሰላም ድርድሩ ግልጽነት የጎደለውን መሆኑንን ለምክንያትነት ካወሳ በኋላ በዋናነት በድንበር ላይ ያለው የመከላከያ ኃይል እንደማይነሳ አቋሙን አስታውቋል። መከላከያ ሠራዊት የአገር ሃብትና ተጠሪነቱ ለፌደራል መንግሥት ነው። ታማኝነቱ ደግሞ ለሕዝብና ለሕገመንግሥቱ ሲሆን ዋና አዛዡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው። በዚህ እውነትና … [Read more...] about ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ100 ቀናት
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 100 ቀናት የሥልጣን ጊዜ አስመልክቶ ጽህፈት ቤታቸው በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑትን ጉዳዮች በሚከተለው መልኩ ማብራሪያ ሰጥቶበታል። ውስጣዊ መረጋጋትን ከመፍጠር አኳያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት በሁሉም ረገድ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮች ባረበቡበት ወቅት ነው። መንግስት ውስጣዊ መረጋጋት ማስፈን ተስኖት ሁለት ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የተገደደበት፣ እዚህም እዚያም ግጭቶችና ትርምሶች የሚፈሉበት፣ በማንኛውም ቅፅበት አዲስ አበባ በኹከት ልትናጥ እንደምትችል የምታስፈራበት፣ ተረጋግቶ መስራትና መኖር አዳጋች የሆነበት፣ ኢኮኖሚው ተንገጫግጮ የነበረውን ፍጥነት ለማስቀጠል የተቸገረበት፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ጫፍ የደረሰበት፣ ኢህአዴግ በየጊዜው መግለጫ ቢያወጣም ተሰሚነቱ/ተዓማኒነቱ እጅግ የቀነሰበት፣ … … [Read more...] about ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ100 ቀናት
“ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ድንበር የለም” – ህወሓት የትግራይን ሕዝብ የሚያስትበት ቅስት ሲሰበር
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና አብረዋቸው የተጓዙ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑካን በኤርትራ የ27 ዓመታት ታሪክ የመጀመሪያ የተባለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ይህ ዓለም ከዳር እስከዳር ያዳረሰ ታላቅ ግንኙነት በሰዓታት ልዩነት ውስጥ የህወሓትን ውስን አመራሮች ዕቅድና የትግራይን ህዝብ የሚያስቱበትን ቀስት ሰብሯል። መሪዎቹ የሃገራቱን ሕዝብ የጋራ ፍላጎት፣ እኩልነትና ሉዓላዊነትን ከግምት ውስጥ ያስገባ ውይይት እያደረጉ መሆኑንን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገጻቸው የገለጹት ንግግሩ በተጀመረ በቅጽበት ውስጥ ነው። አቶ የማነ እንዳሉት ሁለቱ መሪዎች ፈጣንና አዎንታዊ ውጤት የሚያስመዘግብ ስምምነት ይፋ እንደሚያደርጉ ነበር ፍንጭ የሰጡት። ይህንኑ ተከትሎ የጸብ፣ የጥላቻ ግንብ መናዱንና የ“ፍቅር ድልድይ” መዘርጋቱን ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር … [Read more...] about “ኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ድንበር የለም” – ህወሓት የትግራይን ሕዝብ የሚያስትበት ቅስት ሲሰበር
የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ሄደው ጠ/ሚ/ር ዓቢይን ለማውረድ ያቀረቡት ጥያቄ ድራማ
ነባርና ታዋቂ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ መታየታቸው በወፍ በረር ሲዘከር መሰንበቱ ይታወሳል። ከሶስት ሳምንት በፊት የህወሓት ሰዎች አሜሪካ ቤት ለመግዛትና ኑሯቸውን ለማደላደል እንደመጡ ተደርጎ ስም እየተጠቀሰ ሲነገርም ቆይቷል። ተቀማጭነታቸው በአሜሪካ የሆነ የጎልጉል የዘወትር ታማኝ ዲፕሎማት መረጃ አቀባይ ግን ጉዳዩ ሌላ እንደሆነ ነው የሚናገሩት። እንደ ዲፕሎማቱ መረጃ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ድረስ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድን ከሥልጣን ለማውረድ በሌላ አነጋገር መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ የአሜሪካንን ይሁንታን ፍለጋ ነው። ዶ/ር ዓቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑበት ዕለትም ሆነ ከዚያ በፊት በአገሪቱ እየተካሄደ ያለው የለውጥ ማዕበል ያልተመቻቸው የህወሓት ሰዎች ስሜታቸውን በተለያየ መልኩ ሲገልጹ ነበር። ሁሉም አልፎ ኢህአዴግ ካባ ውስጥ ባሉ የለውጥ … [Read more...] about የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ሄደው ጠ/ሚ/ር ዓቢይን ለማውረድ ያቀረቡት ጥያቄ ድራማ
በደቡብ የህወሓት ኅልውና እያከተመ ነው
ለኢህአዴግ ሊቀመንበርነትና ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የህወሓት እጩ በመሆን የቀረበውና በህወሓት ሙሉ ድምጽ የተሰጠው ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ሕዝብ ሊቀመንበርነቱ ለቀቀ። ሽፈራው ሽጉጤ ራሱ እንደተናገረው ከሆነ “ከሥልጣኔ ለቅቄአለሁ” ቢልም አፍቃሪ ህወሓት የሆኑና እርሱ በኢህአዴግ ሊቀመንበርነት እንዲመረጥ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ሲሠሩ የነበሩ ሰውየው “ተገፍቶ ነው” የወጣው በማለት አቅጣጫ የማስቀየር ሙከራ ሲያደርጉ ተስተውለዋል። በቅርቡ በሃዋሳ በደረሰው ግጭት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የሚመለከታቸው አመራሮች በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ ቢሆኑም ባይሆኑም ይህ ዓይነቱ ግጭት እየተፈጠረ በኃላፊነት መቀጠል እንደሌለባቸውና ከሥልጣናቸው በፈቃዳቸው መልቀቅ እንዳለባቸው ሃሳብ ሰጥተው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ከወላይታ ዞን አራት አመራሮች በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን … [Read more...] about በደቡብ የህወሓት ኅልውና እያከተመ ነው
የአዲስ ኢትዮጵያ ብስራት!
ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) የተመሠረተባቸው አዕማዶች ሁለት ናቸው። እነዚህም ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ! እና ሁላችንም አብረን ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ ሊሆን አይችልም! የሚሉት ናቸው። እነዚህን ግዙፍ መርሆዎች ተግባራዊ ለማድረግ የሚጠቀምባቸው ስልቶች ደግሞ ዓመጽ፣ ጥላቻ፣ ክፋት፣ ምቀኝነት፣ ዘረኝነት፣ ወገንተኝነት፣ ወዘተ ሳይሆን ሰብዓዊ ዘርን ከልዩነት በጸዳ ጽኑ ፍቅር በማክበር፣ በመውደድና ለሌላው ሰው ከልብ በመነጨ ቅንነት በሚያስብ አመለካከት ላይ በመመሥረት ነው። የእነዚህ ተግባራት መዳረሻ ደግሞ በአገራችን ላይ ፍቅር፣ ሰላም፣ ኅብረት፣ ዕርቅና ፍትሕ ማስፈን ነው። ከላይ የጠቀስናቸው መርሆዎች በተባለው አካሄድ ተፈጻሚ ይሆኑ ዘንድ የጋራ ንቅናቄያችን ለበርካታ ዓመታት ያለመታከት ሲሠራ ቆይቷል። ለዚህም ነው ኢትዮጵያውያን በቡድንም ይሁን … [Read more...] about የአዲስ ኢትዮጵያ ብስራት!
የጌታቸው አሰፋ ሌጋሲ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች!
የህወሓት ነባር ታጋይ የሆነው ጌታቸው አሰፋ የመረጃና ደህንነት ዳይሬክተር ሆኖ የተሾመው 1993 ዓ.ም ላይ ነበር። ክንፈ ገ/መድህንን የተካው ጌታቸው አሰፋ ከቀደመው የመረጃና የደኅንነት ሰው ፍጹም የተለየ ባህሪ እንዳለው የመረጃ ምንጮቻችን ይጠቁማሉ። ከሸራተን ሆቴል ውጭ እምብዛም የማይዝናናው ጥንቁቁ የመረጃ ሰው ሲበዛ ተጠራጣሪና ደመቀዝቃዛ እንደሆነ ይነገርለታል። በኤምባሲዎች ራት ግብዣ ላይ እንኳን ለመገኘት ከኤምባሲ ኤምባሲ፣ ከአምባሳደርም አምባሳደር የሚያማርጠው የደህንነቱ ቁንጮ፣ በህይወት እያለ ምሽት ላይ ከቦሌ ወሎ ሰፈር ግሮሰሪዎች በአንዱ ከማይታጣው ክንፈ ገ/መድህን አኳያ የተለየ ባህርይ ብቻ ሳይሆን የረቀቀ የአፈና መዋቅር በአገር ውስጥም ሆነ በቀጠናው ላይ መዘርጋት የሚችል ሰው መሆኑ ከቀደመው የመረጃ ሰው እንደሚለየው ይነገርለታል። ሰውየው ራሱን እንደመንፈስ … [Read more...] about የጌታቸው አሰፋ ሌጋሲ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች!
“የጥላቻና የምቀኝነት አስተሳሰብ መገረዝ አለበት፤ አደገኛ በሽታ ነው”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የአስፈጻሚውን አካል የሥራ ክንውን በተመለከተ ያቀረቡት ሪፖርትና ለጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ። ሙሉውን ለመመልከት የቪዲዮው ምስል ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about “የጥላቻና የምቀኝነት አስተሳሰብ መገረዝ አለበት፤ አደገኛ በሽታ ነው”