የህወሓት ነባር ታጋይ የሆነው ጌታቸው አሰፋ የመረጃና ደህንነት ዳይሬክተር ሆኖ የተሾመው 1993 ዓ.ም ላይ ነበር። ክንፈ ገ/መድህንን የተካው ጌታቸው አሰፋ ከቀደመው የመረጃና የደኅንነት ሰው ፍጹም የተለየ ባህሪ እንዳለው የመረጃ ምንጮቻችን ይጠቁማሉ። ከሸራተን ሆቴል ውጭ እምብዛም የማይዝናናው ጥንቁቁ የመረጃ ሰው ሲበዛ ተጠራጣሪና ደመቀዝቃዛ እንደሆነ ይነገርለታል። በኤምባሲዎች ራት ግብዣ ላይ እንኳን ለመገኘት ከኤምባሲ ኤምባሲ፣ ከአምባሳደርም አምባሳደር የሚያማርጠው የደህንነቱ ቁንጮ፣ በህይወት እያለ ምሽት ላይ ከቦሌ ወሎ ሰፈር ግሮሰሪዎች በአንዱ ከማይታጣው ክንፈ ገ/መድህን አኳያ የተለየ ባህርይ ብቻ ሳይሆን የረቀቀ የአፈና መዋቅር በአገር ውስጥም ሆነ በቀጠናው ላይ መዘርጋት የሚችል ሰው መሆኑ ከቀደመው የመረጃ ሰው እንደሚለየው ይነገርለታል። ሰውየው ራሱን እንደመንፈስ … [Read more...] about የጌታቸው አሰፋ ሌጋሲ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች!