ለኢህአዴግ ሊቀመንበርነትና ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የህወሓት እጩ በመሆን የቀረበውና በህወሓት ሙሉ ድምጽ የተሰጠው ሽፈራው ሽጉጤ ከደቡብ ሕዝብ ሊቀመንበርነቱ ለቀቀ። ሽፈራው ሽጉጤ ራሱ እንደተናገረው ከሆነ “ከሥልጣኔ ለቅቄአለሁ” ቢልም አፍቃሪ ህወሓት የሆኑና እርሱ በኢህአዴግ ሊቀመንበርነት እንዲመረጥ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ሲሠሩ የነበሩ ሰውየው “ተገፍቶ ነው” የወጣው በማለት አቅጣጫ የማስቀየር ሙከራ ሲያደርጉ ተስተውለዋል። በቅርቡ በሃዋሳ በደረሰው ግጭት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የሚመለከታቸው አመራሮች በግጭቱ ውስጥ ተሳታፊ ቢሆኑም ባይሆኑም ይህ ዓይነቱ ግጭት እየተፈጠረ በኃላፊነት መቀጠል እንደሌለባቸውና ከሥልጣናቸው በፈቃዳቸው መልቀቅ እንዳለባቸው ሃሳብ ሰጥተው ነበር። ይህንንም ተከትሎ ከወላይታ ዞን አራት አመራሮች በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን … [Read more...] about በደቡብ የህወሓት ኅልውና እያከተመ ነው