ነባርና ታዋቂ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ መታየታቸው በወፍ በረር ሲዘከር መሰንበቱ ይታወሳል። ከሶስት ሳምንት በፊት የህወሓት ሰዎች አሜሪካ ቤት ለመግዛትና ኑሯቸውን ለማደላደል እንደመጡ ተደርጎ ስም እየተጠቀሰ ሲነገርም ቆይቷል።
ተቀማጭነታቸው በአሜሪካ የሆነ የጎልጉል የዘወትር ታማኝ ዲፕሎማት መረጃ አቀባይ ግን ጉዳዩ ሌላ እንደሆነ ነው የሚናገሩት። እንደ ዲፕሎማቱ መረጃ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ድረስ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድን ከሥልጣን ለማውረድ በሌላ አነጋገር መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ የአሜሪካንን ይሁንታን ፍለጋ ነው።
ዶ/ር ዓቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑበት ዕለትም ሆነ ከዚያ በፊት በአገሪቱ እየተካሄደ ያለው የለውጥ ማዕበል ያልተመቻቸው የህወሓት ሰዎች ስሜታቸውን በተለያየ መልኩ ሲገልጹ ነበር። ሁሉም አልፎ ኢህአዴግ ካባ ውስጥ ባሉ የለውጥ ኃይሎች የተሸነፈው ህወሓት ሽንፈቱን ሳይወድ በግድ ለመቀበል ተገዷል።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሕዝብ፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በተለይም የአሜሪካን ይሁንታ ማግኘታቸው “በቆሮቆር ላይ …” እንዲሉ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች ሊደብቁት በማይችሉት ደረጃ አሳመማቸው። በዚሁ የህመም ስሜት የተተነፈሰውን ሁሉ ከማኅበራዊ ሚዲያ ጭፍራዎቻቸው ጋር በመሆን በጅምላ የትግራይ ህዝብ ቀለበት ውስጥ እንደገባ አስመስለው ያቀርቡ ጀመር።
“የቀን ጅቦች” በሚል ለሌቦች ሁሉ የተሰጠውን በተለይ ለአንድ የህብረተሰብ ክፍል ነዋሪዎች ሁሉ እንደተሰጠ በማስመሰል ራሳቸውን ህዝብ ጉያ ሥር በመክተት “የትግራይን ህዝብ ከመሪ ድርጅታቸው ህወሓት ነጥለው ሊያጠቁ ተነስተዋል” የሚል መግለጫ ያወጣው ህወሓት ወደ አሜሪካ ያቀናው ከከበበው ፍርሃት በመንሳት መልሶ የፖለቲካ ስልጣኑንን ለመረከብ እንደሆነ ነው የተገለጸው።
በዚሁ መሠረት አሜሪካ ያቀኑት የህወሃት ቁልፍ የተባሉ ሰዎች “ዶ/ር ዓቢይን በሰላማዊ መንገድ እንድናስወግድ ፍቀዱልን” ሲሉ ነው ጥያቄ ያቀረቡት። የመረጃው ምንጭ እንዳሉት “አገሪቱና ቀጣናው አሁን በመበታተን አደጋ ውስጥ ናት” በማለት የህወሓት ሰዎች “የማረጋጋትና ሰላም የማስፈን ልምድና ክህሎት ስላለን ይህንን ሥጋት ማስወግድ እንድንችል ይሁንታ ስጡን” ሲሉ ነው የተማጸኑት።
አንድ የህወሓት የማህበራዊ ገጽ ጭፍራ አገር ባይጠቅስም ይህንኑ ሃሳብ ሲያራግብ እንደነበር፣ የትግራይ ህዝብ አደጋ ላይ መኖሩን ለዓለም ሁሉ በማሳወቅ ራስን የመከላከል ሥራ መስራት አስፈላጊ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲገልጽ የታዘቡና የህወሓት ክንፍ የድረገጽ ደብተራዎች “ማርም ሲበዛ ይመራል” ማለት ደረጃ መድረሳቸው የመፈንቅለ መንግሥት ጥያቄውን ለማጀብ የተወጠነ ስለመሆኑ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
በዶ/ር ዓቢይ ሕይወት ላይ ምንም ሳይደርስ “በሰላማዊ መንገድ ጉዳዩ ይከናወናል” ያሉት የህወሓት ሰዎች፤ የመፈንቅለ መንግሥት ከተካሄደ በኋላ “የአሜሪካንን ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ አዲስ አስተዳደር እናዋቅራለን፤ በቀጠናው የአሜሪካንን ፍላጎት ተግባራዊ እናደርጋለን” ሲሉም ከኩዴታው በኋላ የሚያከናውኑትን በዝርዝር አብራርተዋል።
ጥያቄው የቀረበላቸው የአሜሪካን ወሳኝ የፖሊሲ ሰዎች “አታስቡት” ሲሉ ከከባድ ማስጠንቀቂያ ጋር እንደመለሷቸው፣ አሁን የተጀመረውን የለውጥ ሂደት አጠናክረው እንደሚገፉበት፣ ሕዝብ በለውጡ መደሰቱንና ይህንን የሕዝብ ፍላጎት መከተል ግዴታቸው እንደሆነ አሳስበው በአጭር መልስ አሰናብተዋቸዋል።
መረጃ አቀባይ ዲፕሎማቱ እንዳሉት ከሆነ የህወሓት ሰዎች ዶ/ር አብይ አገሪቱን ወደ ከፋ ቀውስ እያመሯት እንደሆነና ህወሓት በዚህ አካሄድ አገሪቱ ልትበታተን ትችላለች የሚል ስጋት እንደገባው መስሎ ላቀረበው “መንግስት ልገልብጥ” ጥያቄ ከአሜሪካ በኩል የተሰጣቸው መልስ “አርፋችሁ ተቀመጡ” የሚል እንደነበር ይናገራሉ።
ይህ ዶ/ር ዓቢይን ከሥልጣን ለማስወገድ የቀረበ ሃሳብ ተቀባይነት ካጣ በኋላ የቅዳሜው ሰኔ 16 ዓቢይን የመግደል ሙከራ እንደ ሁለተኛ ዕቅድ ተግባራዊ ስለመደረጉ የተጠየቁት መረጃ አቀባያችን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ ንብረት ናቸው። ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን።
Abera Ayana says
The real reason for them to be seen in the USA is the first one the second reason is just to coverup the real fact. I can’t believe Goolgule missed mislead by false information.
www says
የሠራተኛ ቅሬታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
እኛ ሰራተኞች የጠየቅናቸው structure ሳይሆን Grade ሳይሆን የደሞዝ ማሻሻያ ነው.
አሁን የምንጠይቀው
1.የሠራተኞች የጥቅም መብት ይከበር,
የሠራተኛ ቅሬታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በባንክ አለም ውስጥ መሪ ተዋናዮች የሚባሉት መንግስት፣ አሠሪ እና ሠራተኞች ናቸው፡፡
. የሠራተኞች ፍላጎት
ኢኮኖሚያዊ የደመዉዝ፣ የቦነስ እና አበል ወዘተጥቅሞቻቸዉ እንዲሻሻሉፍትሃዊ የደረጃ ዕድገት እና ለሎችማህበራዊ ጥቅሞቻቸዉ እንዲከበሩላቸዉ ይፈልጋሉየሙያ ደህንነት እና ጤንነት ፍትሓዊ የሥራ አመዳደብፍትሃዊ የዝዉዉር ሥርዓት እና ሌሎች
ፍትሃዊ Market-based/campany scales ደሞዛቸው ሊከፈላቸው,ሊያድግላቸው,ይፈልጋሉ፡፡
የሠራተኛ ቅሬታ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በአጠቃላይ ቅሬታ ማለት በአሠሪ እና ሠራተኞች መካከል የሚፈጠር/ የሚኖር ማንኛዉም የጥቅም ፡ የስራ ጫና፡የዝዉዉር፡የሀሳብ፣ የአመለካከትና የፍላጎት ልዩነቶች አለመጣጣም ምክንያት የሚፈጠረው አለመግባባትና ትግል ነዉ፡፡
ዝርዝር ቅሬታዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ
የአሠሪና ሠራተኛ ፍላጎቶች የሚያስተናግድ ሁሉን አስማሚ ቀ ሥርዓት አለመዘርጋት
በባንኩ ዉስጥ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት አለመኖር
በአሰሪና ሰራተኛ መካከል ጤናማ የሆነ ግንኙነት አለመኖር፤
ዲሞክራሲያዊ እና ግልፅነት የሌለበት PMS
ዲሞክራሲያዊ ያልሆነ ጨቋኝና አፋኝ ሕጎች እና ስምምነቶች፡የባነኩን እና የአሠሪና ሠራተኛ ሕጎችን በፍታዊ መንገድ አለመቶርጎም፡፡
ያለሰራተኛው ስምምነት ሠራተኛን ማዛወር እና ሠራተኛው የሚያቀርበውን የዝውውር ጥያቄ አለመቀበል እና አፋኝ በሆነ ሆግ መረጃ ከዛ ከዚ ካላመጣህ በማለት እንዲሁም የመሳሰሉት የእያንዳንዱን የባንኩን ሠራተኛ ጥቅም የጥቂቶች ቡድን መጠቀሚያ እና የዘመድ ማፍሪያ አድሮገዉታል፡፡
ባንኩ ኢ-ሚዛናዊ የሆነ የትርፍ ማጋበስ ስነልቦናዊ ፍላጎት/ጉጉት ምክኒያት ሰራተኞችን መንከባከብ ቀርቶ መብቶቻቸውን መንፈግ ፡፡
ሠራተኞች በሕግ የተሰጣቸዉ መብቶች እና ጥቅሞች ነገ ዛሬ ሲሉ ሳያገኙ አሁን ደርሰዋል ::
አሰሪው ለህብረት ስምምነት ድርድርና አፈፃፀም እምቢተኛ ሆኑዋ::
ተገቢ የሆነ የደመወዝ ጭማሪ ለሠራተኛው ነፍጓል፡፡
የሠራተኛው ቤተሰብ የህክምና አገልግሎት ተነፍገዋል::
ለሥራ የምያስፈልጉት የሥራ መሳሪያዎችን አለማሟላት::
ባንኩ የስራ strategyውን እና policyውን ብቻ ማቀንቀን ::
ድርጅቱን የሰራተኛውን የልብ ትርታ ቦታ ሳይሰጥ ቆይታል::
ድርጅቱ የሰራተኛውን የእድገት ,የደረጃ ,የደሞዝ ጥያቄ ለማስተናገድ አለመፈለግ እና ማርፈድን መርጧል ፡፡
አሰሪ እና ሰራተኛን የሚመለከቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉትን ሕጎች እና ስምምነቶች ወደ ሀገሩ ወስዶ አለማፅደቅ::
ያፀደቃቸዉንም ሆነ ያወጣቸዉን ሕጎች ያለማክበር እና ያለማስከበር ድክመት::
እንደተዋዋይ ወገኖች ፍላጎት መሰረት አለመግባባቶችን ወይም ቅሬታዎችን ለመፍታት የሚያገለግሉ ሥርዓቶች ማፈን እና ማቀጨጭ ወዘተ፡፡
የጉልበት ብዝበዛ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ላይ ይቁም ፍትህ ለአገራችን ፡፡
በአጠቃላይም ዝቅተኛ ደሞዝ,ዝቅተኛ የአመት ረፍት, ዝቅተኛ የብድር አሰጣጥ —-
የኢትዮጵያ ለውጥ ፈላጊ አባላት በሙሉ ይድረስ ሰላምታችን በያላችሁበት ፡፡
በመቀጠልም ከላይ በዝርዝር የቀረብነውን ቅሬታዎች የሚመለከታቸውን የመንግስት አካላት እና የባንኩን አመራሮችና የቦርድ አባላትን አነጋግራችሁ መብትኤ እንድናገኝ አስፈላጊውን ጥረት እንድታደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
Abera Ayana says
I did speak my mind but you guys were cowards to approve it. Shame on you for pretending as a freedom fighters while abridging freedom of speech.
Ezira says
ለባርነቱና ለአገልጋይነቱ ከእኛ ወዲያ ላሣር ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ለአረቡም ሆነ ለቢጫው፤ ለነጩም ሆነ ለጥቁሩ ባሪያ ሆኖ ለማገልገል ከልጅነት ጀምሮ ዕድገታችንም ሆነ ተሞክሯችን በገሃድ የታዬና የሚታይ ታማኝ ባሪዎች ነን ለማለት ከረባት አስረው አሜሪካ ገቡ..? መጥኔ ለአሜሪካ ! ግን ፡ ግን ውሻም እኮ ታምኝነቱ ብቻ አይደለም የሚያስመርጠው። ታማኙ ውሻ ከታማኝነቱ በላይ ትልቁ መለጊያ ሚዛኑ ተልከሰካሽ (ልክስክስ)ነው ወይስ አይደለም የሚለው ምዘና ሚዛን ይደፋል። ባለ 2 እግር እንስሶች የትግሬው ወያኔ ግን ይሄን ግምት ውስጥ አይሰገቡም። ጥሩ ነው ከቀናቸው ! ውሻን አትልከስከስ ማለት ግ አይቻልም።