ነባርና ታዋቂ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ መታየታቸው በወፍ በረር ሲዘከር መሰንበቱ ይታወሳል። ከሶስት ሳምንት በፊት የህወሓት ሰዎች አሜሪካ ቤት ለመግዛትና ኑሯቸውን ለማደላደል እንደመጡ ተደርጎ ስም እየተጠቀሰ ሲነገርም ቆይቷል። ተቀማጭነታቸው በአሜሪካ የሆነ የጎልጉል የዘወትር ታማኝ ዲፕሎማት መረጃ አቀባይ ግን ጉዳዩ ሌላ እንደሆነ ነው የሚናገሩት። እንደ ዲፕሎማቱ መረጃ የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ድረስ የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድን ከሥልጣን ለማውረድ በሌላ አነጋገር መፈንቅለ መንግሥት ለማድረግ የአሜሪካንን ይሁንታን ፍለጋ ነው። ዶ/ር ዓቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑበት ዕለትም ሆነ ከዚያ በፊት በአገሪቱ እየተካሄደ ያለው የለውጥ ማዕበል ያልተመቻቸው የህወሓት ሰዎች ስሜታቸውን በተለያየ መልኩ ሲገልጹ ነበር። ሁሉም አልፎ ኢህአዴግ ካባ ውስጥ ባሉ የለውጥ … [Read more...] about የህወሓት ቁልፍ ሰዎች አሜሪካ ሄደው ጠ/ሚ/ር ዓቢይን ለማውረድ ያቀረቡት ጥያቄ ድራማ