የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 100 ቀናት የሥልጣን ጊዜ አስመልክቶ ጽህፈት ቤታቸው በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑትን ጉዳዮች በሚከተለው መልኩ ማብራሪያ ሰጥቶበታል። ውስጣዊ መረጋጋትን ከመፍጠር አኳያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡበት ወቅት በሁሉም ረገድ እጅግ ፈታኝ የሆኑ ጉዳዮች ባረበቡበት ወቅት ነው። መንግስት ውስጣዊ መረጋጋት ማስፈን ተስኖት ሁለት ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የተገደደበት፣ እዚህም እዚያም ግጭቶችና ትርምሶች የሚፈሉበት፣ በማንኛውም ቅፅበት አዲስ አበባ በኹከት ልትናጥ እንደምትችል የምታስፈራበት፣ ተረጋግቶ መስራትና መኖር አዳጋች የሆነበት፣ ኢኮኖሚው ተንገጫግጮ የነበረውን ፍጥነት ለማስቀጠል የተቸገረበት፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ ጫፍ የደረሰበት፣ ኢህአዴግ በየጊዜው መግለጫ ቢያወጣም ተሰሚነቱ/ተዓማኒነቱ እጅግ የቀነሰበት፣ … … [Read more...] about ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ100 ቀናት
ahmed
“(ዓብይ) ብዙ ቃል የገባቸውን ጉዳዮች ፈጽሟል”
ማክሰኞ መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓ.ም. ምሽት እኩለ ሌሊት እየተቃረበ እያለ የተሰማው ሰበር ዜና በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ያነጋገረ ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከኢሕአዴግ ሊቀመንበርነታቸውና ከጠቅላይ ሚኒስትርነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን ይፋ ካደረጉ በኋላ፣ ተተኪያቸው ማን ይሆን የሚለው በመላ አገሪቱ ዋነኛ መነጋገሪያ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በተለይ ማክሰኞ መጋቢት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ተተኪውን የግንባሩን ሊቀመንበር ለመምረጥ ስብሰባ የተቀመጠው የኢሕአዴግ ምክር ቤት ለአንድ ሳምንት በመቆየቱ፣ በርካቶች በመላ ምቶችና በሴራ ንድፈ ሐሳቦች እንዲጨናነቁ አድርጓቸዋል፡፡ የአገሪቱ ፖለቲካ ለትንተና እስከሚያስቸግር ድረስ የተለያዩ መረጃዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች በመሰማታቸው፣ የተተኪው ማንነት ብዙዎችን ቢያሳስብ አይገርምም … [Read more...] about “(ዓብይ) ብዙ ቃል የገባቸውን ጉዳዮች ፈጽሟል”
የዶ/ር አብይ አህመድ ፈተናዎች
እርግጥ እንደ መለስ ዜናዊ ባለ ሙሉ ስልጣን ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል? ከልክ በላይ ለጥጠው፤ እንደ ልብ አንጠልጥል ፊልም ያቆዩትን ፍትግያ ትናንት በዜና ሲሰብሩት ደስታቸውን ይገልጹ የነበሩት ዜጎች ጥቂት አልነበሩም። ወትሮውን በስብሻለው ከሚለን ስራዓት አዲስ ነገር የሚጠብቅ ተስፈኛ ቢደሰት ብዙም አይደንቅም። የጠቅላይ ሚንስትር እንጂ የስራዓት ለውጥ መች ተመለከትን? ዶ/ር አብይ አህመድ በዚህ ቀውጢ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ መመረጡ ግን ከክብሩና ከስልጣኑ ይልቅ ፈተናው ያመዝናል። ለሶስት ቀናት ተብሎ የተጀመረው ግብግብ ይሉት ክርክር በተነገረለት ቀን መቋጨት ያለመቻሉ በራሱ የሚነግረን ነገር ነበር። አወዛጋቢው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ፣ ፓርላማ ላይ በጸደቀበት ወቅት ዶ/ር አብይ በስፍራው ባለመገኘታቸው የህወሃት ሰዎች ክፉኛ እንደተበሳጩ አይተናል። ይህንን ቅሬታ በብሎገሮቻቸውም … [Read more...] about የዶ/ር አብይ አህመድ ፈተናዎች