- እርግጥ እንደ መለስ ዜናዊ ባለ ሙሉ ስልጣን ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል?
ከልክ በላይ ለጥጠው፤ እንደ ልብ አንጠልጥል ፊልም ያቆዩትን ፍትግያ ትናንት በዜና ሲሰብሩት ደስታቸውን ይገልጹ የነበሩት ዜጎች ጥቂት አልነበሩም። ወትሮውን በስብሻለው ከሚለን ስራዓት አዲስ ነገር የሚጠብቅ ተስፈኛ ቢደሰት ብዙም አይደንቅም። የጠቅላይ ሚንስትር እንጂ የስራዓት ለውጥ መች ተመለከትን? ዶ/ር አብይ አህመድ በዚህ ቀውጢ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ መመረጡ ግን ከክብሩና ከስልጣኑ ይልቅ ፈተናው ያመዝናል።
ለሶስት ቀናት ተብሎ የተጀመረው ግብግብ ይሉት ክርክር በተነገረለት ቀን መቋጨት ያለመቻሉ በራሱ የሚነግረን ነገር ነበር። አወዛጋቢው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ፣ ፓርላማ ላይ በጸደቀበት ወቅት ዶ/ር አብይ በስፍራው ባለመገኘታቸው የህወሃት ሰዎች ክፉኛ እንደተበሳጩ አይተናል። ይህንን ቅሬታ በብሎገሮቻቸውም ሳይቀር ሲገልጹልን ነበር።
ደስታቸውን ከልክ ባለፈ መንገድ እየገለጹ ያሉት ወገኖች ይህንን አጋጣሚ እንደ ምክንያት ሳይሆን እንደ መዳረሻ ካዩት ግን በህዝብ ትግሉ የተከፈለው መስዋእትነት ሁሉ ከንቱ ነበር ማለት ያስችለናል። የጠቅላይ ሚንስትርነት ስፍራ የለውጥ ማራመጃ ሳይሆን እንደ አንድ ትልቅ ግብ ስናየው ነው ስህተቱ።
ማህደረ ትውስታችን አጭር ካልሆነ በስተቀር ሊያሳስበን የሚገባው አዋጁን ተከትሎ የበታች አመራሮች በሙሉ እስር ቤት መታጎራቸው እንጂ የኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን አልነበረም። ስሜታችንን ሊነካ የሚችለው ስደት፣ አፈና እና ግድያው እንጂ በወታደሩ ክርን ውስጥ ያለች ሃገር ጠቅላይ ሚንስትር መሆን አልነበረም።
ግራም ነፈሰ ቀኝ ዶ/ር አብይ ተመርጠዋል። ይህ ደግሞ ያለ ህወሃት በጎ ፈቃድ ከቶውንም ሊሆን አይችልም። ምርጫ፣ ብልጫ፣ ደብረጽዮን ሁለት ድምጽ፣ አብይ 108 ድምጽ፣ ምናምን የሚሉት ትርክት እኛን ትንሽ ፈገግ ቢያደርገንም ፈረንጆቹን ያሳምን ይሆናል። ምን አይነት ታኮ እንዳሰቡ ባይታወቅም፣ ምርጫቸው ሳይፈልጉት የሚውጡት መድሃኒት አይነት ይመስላል። እንደ ኮሶ እያንገሸገሻቸው ዶ/ር አብይን በስፍራው አስቀምጠውታል። ለዚህም አንዱ እሳቤ የኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን እንቅልፍ እየነሳቸው ያለውን የቄሮ አመጽ ሊያበርደው ይችላል ከሚል ሂሳብ ተነስተው ነው። የሰላማዊው ሽግግር ለውጥ የሚሉት ጨዋታቸው ደግሞ ለምዕራቡ አለም መሸቀያ ይሆናቸዋል። የገቡበት አደገኛ ማጥ ፋታ አልሰጣቸውም። ግዜ መግዛት አለባቸው።
አዲሱ ተመራጭ እርግጥ እንደ መለስ ዜናዊ ባለ ሙሉ ስልጣን ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል? በህገ መንግስቱ ላይ የሰፈፈረውን ስልጣን ተግባራዊ ያሚያደርግ ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ ግዜ የሚፈታው ጉዳይ ቢሆንም በፊቱ ላይ ሁለት ነገሮች ተደቅነዋል። እድል እና ፈተና። ምርጫው የሱ ነው። እንደ አነሳሱ እድሉን ይጠቀምበታል ብለን እናምናለን። ዶ/ር አብይ የህዝብን ጥያቄ መልሶ እርቅ እና ፍትህን የማስፈን እድል አለው። ይህንን ለማድረግ ደግሞ ይህንን ከማይፈልጉ የህወሃት ጡረተኞች ጋር መፋጠጡ ግድ ይላል። የህወሃት መርህ የሆነው የዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት በራሱ እንቅፋት ነው። ተግዳራሮቶቹን እና እንቅፋቶቹን አልፎ ይህንን እድል ከተጠቀመ ታሪክ ሰርቶ ያልፋል። ያ ካልሆነ ግን እንደ ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ አሻንጉሊት ተብሎ የሞራልም ውድቀት ይሆንበታል።
ዶ/ር አብይ የአዲሱ ትውልድ ትግል ውጤት ነው። ስለዚህም ችግሩን ከላይ ሳይሆን ከታች፤ በውስጡ እየኖረ ያውቀዋል። ከሌሎቹ በበለጠም ይረዳዋል። እናም ይፈታዋል የሚል እሳቤ አለ። ይህንን ሲያደርግ ብቻውን አይደለም። ለለውጥ የተነሳው ሃይል ከጀርባው እንዳለ ይገነዘባል።
አንደበተ ርቱዕ ነው። አብሮነትን እና ፍቅርን ይሰብካል። ባገኘው መድረክ ሁሉ ከዘር ጥበት ወጥቶ ኢትዮጵያን ከፍ የማድረግ አዝማሚያ ይታይበታል። ይህን ማድረጉ ደግሞ ከኢትዮጵያዊነትን ከሚያቀነቅኑ ሳይቀር ድጋፍ አግኝቷል። ይህ ሰፊ የህዝብ ድጋፍ ወታደራዊ አገዛዙ የከረቸመውን በር የመስበር ጡንቻ ይሆነዋል።
“መለስ የጀመረውን ልጨርስ ነው የመጣሁት” ብለው ነበር ሃይለማርያም ደሳለኝ በተሾሙ ወቅት። ዶ/ር አብይም ሃይሌ የጀመሩትን አንዳንድ ነገሮች ከዳር እንደሚያሰርስ ተስፋ አለን። ለምሳሌ ማዕከላዊ ሚዚየም ሆኖ ያስጎበኙናል።
አብይ ስፍራውን የያዘው ኢህአድግን ለማዳን ነው ወይንስ ሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ? ግዜ ይጠይቃል። ጥያቄውን እሱ እና የ”ለማ ቲም” የሚመልሱት ይሆናል። … መልካም እድል!
ክንፉ አሰፋ
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
aradaw says
Hello Ato kinfu;
I appreciate your non tiring pen. I read most of your writings and agree with most of them specially those written these days. ግራም ነፈሰ ቀኝ ዶ/ር አብይ ተመርጠዋል። ይህ ደግሞ ያለ ህወሃት በጎ ፈቃድ ከቶውንም ሊሆን አይችልም። I just can not take the expression በጎ ፈቃድ. TPLF is forced between the breakdown of EPRDF and the bigger risk of the country falling in big danger. This choice in any angle you look, it is a suicide to TPLF. There is no በጎ ፈቃድ and will not be after this. People struggle has go far from TPLF, EPRDF and including Dr. Abiy. DR. Abiy can use this big challenge to accommodate peoples demand. He has no other option.
በለው! says
**ኅይለመልስ ደስአለኝ “ሀገሪቱን ላለፉት ፮ ዓመት ችግር ላይ ስለጣልኳት ሥራዬ መቀጠል አልችልም። ልቀቁኝ ግን ተጠቅላይ ሚ/ር ሆኜ ‘የመፍትሔው አካል መሆን እፈልጋለሁ” እንዴት ነው ነገሩ? መጀመሪያውኑ ችግሩን ለምን ፈጠረው? አሁን ሁለተኛ ም/ጠ ሚኒስተር ሊሆን ነው? ወይስ የአብይ መሐመድ የመለስ ራዕይ አስተማሪና
በጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የህወሓት ጉዳይ ፈጻሚ የኢህአዴግ ሊቀመንበር፡ የኢትዮጵያ ሚኒስትሮች ጠቅላይ፡ ምርጫ አቶ ደመቀ ራሱን እንዲያገል ተደርጎ ዶ/ር ዐቢይ፣ ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጡ ለፉክክር በቀረቡበት ምርጫ ተገኘ የተባለውን ብአዴን ፵፭ ቱም ድምፅ፣ ኦሕዴድ ፵፭ቱም ድምፅ፣ ደኢሕዴን ፲፰ ድምፅ ለዶ/ር ዐቢይ አሕመድ፡፡ ሕወሓት ፴፪ ድምፅ፣ ደኢሕዴን ፳፯ ድምፅ ለአቶ ሽፈራው፡፡ ሕወሓት ፪ ድምፅ ለደብረጽዮን፡
ድምፅ -ተዐቅቦ ፰ ድምፅ፡ በምርጫ ያልተገኙ ፫ ተባለ።
**ዶ/ር ደብረፂዮን እንደተናገሩት ትግራይን ለማስተዳደር ከተመረጥኩ አጭር ጊዜ ስለሆነኝ መመረጥ አልፈለኩም ነበር “አትምረጡኝ ብዬ ቅስቀሳ አድርጌያለሁ” ዶ/ር ደብረፂዮን «መመረጥ ካልፈለጉ ለምን አንደ አቶ ደመቀ ራስዎን አላገለሉም»
“የሕወሓት የበላይነት እንደሌለ ግልጽና ፉክክር የነበረበት ለየት ያለ ምርጫ መሆኑን ለሕዝብ ለማሳመን ሲባል”
ህዉሃት በ1983/84 ዓም ኦነግን ይዛ ቀሪዉን የኢትዮጵያ ህዝብ አግልላ ምናምንቴ ህገ መንግስት እና ኢትዮጵያዉያንን የሚያባላ ክልል ያጸደቀች ጊዜ ብዙ ኢትዮጵያዉያንን እና አለም አቀፍ ማህበረሰብን ማታለል ችላ ነበር። በድጋሚም በ1997 ዓም ምርጫ ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ለዉጥ ፈልጎ ቅንጅትን ሲመርጥ ሶስት ጣምራ ስትራቴጂዎችን ተጠቅማ ህዝባዊዉን ሀይል ከጫዋታ ዉጭ እንዲሆን አድርጋዉ ነበር። ይሄዉም የቀኝ ክንፍ አክራሪ ሀይሎች መጡብህ የሚል ማስደንበሪያ፣ የጉልበት ስልት እና ቅንጅቱን እራሱን ገብቶ የመከፋፈል ስትራቴጂዎችን በማጣመር ቅንጅቱን ከጥቅም ዉጭ ማድረግ ችላ ነበር። የአዲሱ ሴራ ሲተነተን… ሸንቁጥ
(ሀ) ኦህዴድ እና ብአዴን ከህዉሃት ጋር ትግል ዉስጥ ገብተዋል የሚል ትርክት ተቀባይነት እንዲያገኝ ተደረገ።የኦሮሞ ብሄረተኞችን እነ ጀዋርን ሳይቀር ወደ ኦህዴድ ደጋፊነት እንዲያዘነብሉ ማድረግ የሚያስችል የድርሰት ሴራዉ እንዲጦፍ ተደረገ::
(ለ)አባይ ጸሃዬ እና አቢይ ተቧቀሱ፣ ደመቀ እና ደብረጺዮን ተደባደቡ፣ ቲም ለማ እና ገዱ ግንባር ፈጠሩ በሚል ትርክት በለዉጥ ጥማት የሚንገበገበዉን ኢትዮጵያዊ ብዙሃን ትኩረት ወደ ህዉሃት ድራማ ትርክት እንዲሳብ አደረጉት።
(ሐ) አቦይ ስብሃት ብአዴኖችን ሰብስቦ ለምን ከኦህዴዶች ጋር መከራችሁ ብሎ አስጠነቀቃቸዉ የሚል ትርክት ከባህርዳር የብአዴን ካድሬዎች እንዲሰራጭ ተደረገ። ድራማዉን በደንብ ለማጦፍም ኢትዮጵያዊነት ሲሰበክ ለመስማት የሚቋምጠዉን ሰዉ የሚያማልል “ኢትዮጵያዊነት ሱሴ” የሚል ትርክት በስፋት እንዲሰማ ተደረገ።
(መ) በሚገርም እና ለማመን በሚያስቸግር ፍጥነት ኢትዮጵያ የሚል ቃል ሲጠራ ጆሮዉን ያሳክከዉ የነበረዉ ጀዋር ሳይቀር ኢትዮጵያዊነት ሱሴ የሚለዉ ትርክት ደጋፊ እንዲሆን የቲም ለማ ሀይል እያሸነፈ ነዉ፣ የህዉሃት ጉልበቱ እየተንቀጠቀጠ ነዉ የሚል አንደምታዎች መሰራጨት ጀመሩ::
(ሠ) ለማ መገርሳ እና አቢይ ቦታ እንዲቀያየሩ እና አቢይ የኦህዴድ ሊቀመንበር እንዲሆን ሲደረግ ወያኔ ከኋላ ሆና ድራማዉን ብትቆምርም ይሄ የአቢይ እና የለማ ቦታ ልዉዉጥ የጀግንነት እና የብልሃት ትርክት እንዲላበስ ወደ ተቃዋሚ ጎራዉ እንዲስፋፋ ተደረገ።ኢሳት የኦህዴድ ድምጽ እንዲሆን እና እነ አቢይን እንዲያጀግን አስተማማኝ ስራ ተሰራ::ኢሳት ኢህአዴግን የከፋፈለ መስሎት በዋናነት የወያኔን ድራማ ማስፈጸሚያ ሚዲያ ሆኖ ቁጭ አለ።
(ረ) በጠቅላይ ሚኒስቴር ሹመቱ ላይ ህዉሃት በአቢይ ደስተኛ እንዳልሆነ ለማስመሰል ደመቀ መኮንንም ለማጀገን እንዲሁም የብአዴንን ክብር ጠብቀዉ ከኦህዴድ ጋር የጠበቀ ፍቅር ናቸዉ፡ ለማስባል ብሎም በብዙሃኑ የአማራ እና የኦሮሞ ተወካዮች የተመረጠ ጠቅላይ ሚኒስቴር ነዉ ለማስባል አቢይ በዋናነት በኦህዴድ እና በብአዴን ድጋፍ እንዳለፈ እንዲመስል ድራማዉ አግባባዊ ትረካዉን አስቀምጧል።
**በየአካባቢዉ የተነሱ የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አንዱም እንኳን አልተፈታም። ሆኖም ወያኔዎች እና አስመሳይ ተቃዋሚዎች የተቃዉሞዉን አቅጣጫ እኛ የመረጥንልህን ጠቅላይ ሚኒስቴር ትግሬ ሳይሆን ከዚህ ብሄር በመሆኑ ተነስተህ አጨብጭብ የሚል አንደምታ እየሰበኩ ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ የኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ የአማራ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ የትግሬ ጠቅላይ ሚኒስቴር የሚል አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ ጥያቄ በዋንኛነት የዲሞክራሲ አስተሳሰብ እና መርህ እዉን የሚሆበት ስርዓት እና በህግ የበላይነት የሚመራ ተቋማት እዉን ሆኖ ማዬት ነዉ። ይሄን ደግሞ ገማሁ፣ በሰበስኩ፣ በወንጀል ተጨማለቅሁ፣ በሙስና ከረፋሁ ብሎ እራሱን ደጋግሞ በህዝብ ፊት ባዋረደዉ ኢህአዴግ ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም። እንቶኔም ሄደ እንቶኔም ተተካ ሁሉም የገማዉ ስርዓት አካል እና አባል ነዉና። “ሲል ሸንቁጧል።
**የብአዴኑ ኦሮአማሮ ያሬድ ጥበቡ ከእፎይታ ምሽትና መኝታ በኋላ ስለአቢይና የመመረጡ ትርጉም ብዙ አውጠነጠንኩ ። በአቢይ ምርጫ አንዱ ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ የተነሳው ቀንበር፣ ኦሮሞ በመሆናችን፣ ሙስሊም በመሆናችን እኩል አንታይም የሚለው ትርክት ነው ። ይህ ትርክት እውነትም ሆነ ምናባዊ፣ ዛሬ በአቢይ ምርጫ የተነሳ መፍትሄ አግኝቷል። ይህ ትልቅ ክንዋኔ ነው። ዴሞክራሲያዊ የሚባሉ ብዙ የምእራብ ሃገሮች እንኳ ሊያደርጉት የማይችሉትን ነው ኢትዮጵያችን ባለፉት ስድት ዓመታት ያደረገቸው። (በምእራብ ሃገሮች ዛሬም ካቶሊክ ወይም ፕሮቴስታንት መሆን እንኳንስ ለከፍተኛው ሥልጣን ለፓርላማ አባልነት እንኳ ጋሬጣ ይሆናል) ። በመጀመሪያ ወላይታና ፔንጤ፣ አሁን ደግሞ ኦሮሞና ሙስሊም ለታላቁ ወንበር በማጨት ትልቅ ክንዋኔ አድርገናል ። ዶክተር አቢይ ፔንጤ መሆኑን ሰምቻለሁ፣ ሆኖም ከአጋሮ ኦሮሞ ሙስሊሞች የተወለደ መሆኑ የኢትዮጵያውያን ሁሉ አለቃ ከመሆን አላስቆመውም። ስለሆነም፣ በኢትዮጵያችን ሙስሊምነትም ሆነ ኦሮሞነት፣ ጴንጤነትም ሆነ ወላይታነት ሳያግደን አንድን ኢትዮጵያዊ በዜግነቱ ማክበር የምንችል የመከባበር ሃገር መሆናችንን ነው ለዓለሙ ያስመሰከርነው። በዚህ ፍፃሜያችን ልንኮራ ይገባናል። ከእንግዲህ ኢትዮጵያችንን በብሄርና ሃይማኖት አግላይነት ስሟን የሚያነሳ የተረገመ ይሁን። ያን ሩጫ ጨርሰናል።”
( ብርሃኑ ደሬሳ፡ ተፈሪ በንቲ የኢሃዴግ ክንፍ ኦነግ/ኦህዴድ ካልሆኑ ኦሮሞ አልነበሩም ማለቱ ነው።) አኑዓር መስጊድና ራጉኤል ቤተክርስቲያን ጎን ለጎን የሚመለክበት ሀገር አሜሪካ ይሆን? እስላምና ክርስቲያን ግራና ቀኝ በድንኳን ሠርግና ሐዘን የሚጋሩበት፡ በልተው ጠጥተው ተጋብተው ወልደው የሚከብሩበት በሰላም የሚኖሩበት የት ሀገር ታይቷል?
*በጣም አስገራሚና አስደንጋጩ ነገር ሁሉምና እያንዳንዱ ቦልጥቀኛ ዲያስፐር ተቃዋሚና ተቋቋሚ ሁሉ ለዓብይ መሐመድ አሊ ነገዱን ትምህርቱን፡ማዕረጉን፡ የሥራ ደርሻውን፡ዕድሜውን፡ ቤተሰቡን ጓደኛና ጎረቤቱን እያጣቀሰ መረጃና ማስረጃ አድርጎ የመጀመሪያውን የሕዝብ ንግግር፡የመጀመሪያውን ፻ ቀን የሥራ ዕቅድ፡የመጀመሪያውን ስድስት ወር መርሃ ግብር ነድፈው ለጥፈዋል፡ ይቺ ናት ሀገር! ይህ ሀገር በወሮ በላ መወረሩ ሳያንስ ከዕድርና ዕቁብ ያነሰበት ሕዝብ የተናቀበት ግርም ይላል። ዶ/ር ዓብይ መሐመድ አሊ ሆይ፡ ይቺ ማንቆለጳጰስ ለመለስም አልበጀች ይልቁንም እንደአጀማመርህ ኢትዮጵያዊነትን ስበክ! የክልል የከብት ጋጣ ጎን ድልድይ ሥራ! ብሔርን ከወረቀት መታወቂያ ላይ ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብም አስለውጥ! ለህወሓት ሐሳብን አምኖ፡ ነገርን ማሳመንን፡ በሕዝብ መታመንን አስተምር! አሳታፊ እንጂ አግላይ አትሁን! የታሰረ ሕዝብ፡ቋንቋ፡ሰንደቅና ሀገርን አስምር! በመረጠው የሚኖር፡በፈለገውና ባመነው የሚያስብ ትውልድ እንዲኖር አበረታታ! አፍራሽ ሳይሆን ገንቢ ትውልድ እንዲኖር የወጣት ሥነልቦና ቀረጻ ቅድሚያ ሥጥ! ተምሮ አስተማሪ እንጂ ሳይማር የሚያደነቁርና የሚያባላ ካድሬ፡ ሠርቶ ጥሮ ግሮ እንዲበላ አሰናብት!ሕዝብ የነበረ ያለ የሚኖር እንጂ “ማንነታችሁን የማታወቁ የማትታወቁ በ፩፱፹፫ በእኛ የተፈጠራችሁ፡ ለእኛ የምትኖሩ፡ያለ እኛ የምትበታተኑና የምትጠፉ ብርቅዬ ተናጋሪ እንስሶች” የሚለውን የጫካ ማኒፌስቶ የከተማ ሕገ ጠርንፍ በባለሙያ አስጠና ! አስተምር አንቃ አደራጅ…ከጉልበት(ከመሳሪያ) ወደዕውቀት(ሥራ) ሽግግር እንዲኖር ይሁን መልካም ዕድል!!!