የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር አሜሪካ ስልክ ደውለው መረጃ አሳልፈው በመስጠታቸው ዋጋ የሚያስከፍል ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተሰማ። አፈጉባዔው እንደተቀጣሪ ሪፖርተር በአሜሪካዊ ዜግነት አማራ ክልል ሆኖ ዜና ሲያሰራጭ የነበረው አቶ ተዋቸው ደርሶ የመታሰሩን ዜና ነው በስልክ ያሳበቁት። አቶ ተዋቸው መታሰሩን ዘሃበሻ “ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ባለሥልጣን ነገሩኝ” ሲል ነው የዘገበው። በዚሁ መነሻ አቶ ተዋቸውን አስመልክቶ መረጃ ለማሰባሰብ የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባደረገው ማጣራት በቀጥታ ለእስር የዳረገው ምክንያት ባይታወቅም፣ የግንኙነት ሰንሰለቱን ተከትሎ በርካታ መረጃ እንደተገኘበት ለማወቅ ተችሏል። ሰላማዊ መንገድን አማራጭ አድርገው ከማይከተሉ ኃይላት አመራሮች ጋር ግንኙነት አለው የሚለው ግን ለመታሰሩ ከተነገሩት ምክንያቶች ገዝፎ የወጣው … [Read more...] about አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ
andm
“በመንግስት አመራር ውስጥ ‘እኔ አውቅላችኋለሁ’ የሚል ደዌ ተጠናውቶን ቆይቷል” አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
ገዱ አንዳርጋቸው በምሁራን መድረክ ያድረጉት የመክፈቻ ንግግር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተከበራችሁ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች! እንኳን ወደ አማራ ክልል መዲና ውቢቷ ባህርዳር ከተማ በሠላም መጣችሁ! ከነገሬ ሁሉ በማስቀደም የአማራ ክልል መንግስት እና ህዝብ የጐደለውን ትሞሉለት ዘንድ ምክራችሁን እና የሙያ ድጋፋችሁን በመሻት ለልጆቹ ያደረገውን ይህን ታሪካዊ ጥሪ ያለምንም ማቅማማት ተቀብላችሁ እዚህ በመካከላችን በመገኘታችሁ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ። በረጅሙ የሃገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የአማራ ህዝብ በስልጣኔ፣ በተለይም በመንግስት አስተዳደር፣ በታሪክ፣ በኪነ-ጥበብ፣ በስነ-ፅሁፍ፣ በአርበኝነት ተጋድሎ እንዲሁም በኢኮኖሚ ዕድገት ለሃገር ያበረከተው ድርሻ ትልቅና አይረሴ ቢሆንም ያለፈው ግማሽ ምዕተ-ዓመት … [Read more...] about “በመንግስት አመራር ውስጥ ‘እኔ አውቅላችኋለሁ’ የሚል ደዌ ተጠናውቶን ቆይቷል” አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
ጠ/ሚ/ር ዓቢይ እና ህወሓቶች፡ ለይቶ ማሰር ወይስ አብሮ መሥራት?
ኢህአዴግ ውስጥ ስለተደረገው አመራር ለውጥና ለውጡ የተካሄደበትን ሁኔታ አስመልክቶ የተለያዩ ሃሳቦችና አስተያየቶች ይሰጣሉ፡፡ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ኢህአዴግ የአመራር ለውጥ ያደረገው በሀገሪቱ እየታየ ያለውን ህዝባዊ አመፅና ተቃውሞ ለመግታት እንደሆነ ሲገልፁ ይሰማል፡፡ በሌላ በከል አንዳንድ የህወሓት/ኢህአዴግ ደጋፊዎች የአመራር ለውጡ የተካሄደው በተለመደው የፓርቲው ደንብና ስርዓት እንደሆነና የአዲሱ ሊቀመንበር ምርጫ በአባል ድርጅቶች የጋራ መግባባት የተመሠረተ እንደሆነ ሲገልፁ ይሰማል፡፡ ነገር ግን፣ ሁለቱም አመለካከቶች በተሳሳተ ግንዛቤ ላይ የተመሠረቱ ናቸው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ ያሉ አስተያየቶች፤ አንደኛ፦ የለውጡን መነሻ ምክንያት በጥልቀት ካለመረዳት፣ ሁለተኛ፦ የአመራር ለውጡ የተካሄደበትን ሁኔታ በግልፅ ካለመገንዘብ የመነጩ ናቸው፡፡ ኢህአዴግ የአመራር ለውጥ እንዲያደርግ … [Read more...] about ጠ/ሚ/ር ዓቢይ እና ህወሓቶች፡ ለይቶ ማሰር ወይስ አብሮ መሥራት?
አማራ የሚፈናቀለው ሆነ የሚገደለው በመንግስት ፍቃድ ነው!
ትላንት (May 15) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አበጥር ወርቁ በተባለ የአማራ ብሔር ተወላጅ ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ግፍ ተመልክተናል፡፡ ይህ ከመሆኑ ከአንድ በፊት ደግሞ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ527 በላይ አባወራዎች በድምሩ 2000 ከሚሆኑ ቤተሰቦቻቸው ተፈናቅለዋል፡፡ እነዚህ “ሕገ ወጥ ናችሁ” በሚል ሰበብ ተዘርፈውና ተደብድበው የተፈባቀሉት አማራዎች ህጋዊ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ያላቸው ናቸው፡፡ በባለቤትነት ለሚያስተዳድሩት መሬት በአግባቡ ግብር ይከፍላሉ! በፎቶው የሚታዩት የይዞታ ማረጋገጫ ደብተሮች ባህርዳር ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ተጠልለው የሚገኙ ሶስት አባውራዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ያለ ምንም መነሻ ምክንያት ከመሬታቸው አልተፈናቀሉም፣ በግፍ አልተገደሉም፡፡ ከዚህ በስተጀርባ በጥላቻና ማንአለብኝነት የናወዙ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመንግስት … [Read more...] about አማራ የሚፈናቀለው ሆነ የሚገደለው በመንግስት ፍቃድ ነው!
የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!
በእርግጥ ፖለቲካ ማለት ልክ "Bicycle" ነው። ሁልግዜም በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል መሽከርከር አለበት። ለውጥና መሻሻል ከቆመ ልክ እንደ "Bicycle" ፖለቲካዊ ስርዓቱም ተንጋሎ ይወድቃል። ህወሓት የማይለወጥ የፖለቲካ ቡድን ከመሆኑም በላይ ሌሎች እንዳይለወጡ የሚያደርግ ፀረ-ለውጥ ቡድን ነው። ስለዚህ ይህ ቆሞ-ቀር ቡድን የሌሎችን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያለመታከት ጥረት ያደርጋል። በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥና መሻሻል ጠፍቶ መንግስታዊ ስርዓቱ ለመውደቅ እየተንገዳገደ ባለበት ወቅት እንኳን ህወሓት በኦህዴድ መሪነት የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል ላይ-ታች ሲል ነበር። አዲሱ የኦህዴድ አመራር ወደ ስልጣን እንደመጣ የወሰደው የለውጥ እርምጃ ፀረ-ለውጥ አቋም ከሚያራምደው የህወሓት ቡድን ራሱን ማላቀቅ ነው። በዚህ ረገድ የክልሉ ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ … [Read more...] about የህወሓት ዕቅድ፥ የእስር ማዘዣው እና የብአዴን ጆከር!
ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!
ህወሓት የሚዘውረው ኢህአዴግ ከሁለት ሳምንታት በላይ ስብሰባ አድርጎ “መግለጫ” ያለውን “ቀጭን ትዕዛዝ” በማውጣት ተጠናቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በለውጥ አራማጅነት ሲጠቀሱ የነበሩት እነለማ መገርሳ “መግለጫውን” አብረው አጽድቀው ወጥተዋል። “የጨለንቆን ፍጅት የፈጸመው ማነው?” የሚለውም ደፋር አጀንዳ አብሮ የሞተ ጉዳይ ሆኗል። “ምን ይዤ (ወደ ሕዝቤ) ልመለስ?” በማለት ወደስብሰባው የገቡት ኦህዴድና ብአዴን “የተቀናጁ ተጨማሪ እርምጃዎች” እወስዳለሁ (መግደሌን እቀጥላለሁ) ለሚለው የህወሓት “መግለጫ” ይሁንታቸውን ሰጥተው ወጥተዋል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ከወር በላይ ስብሰባ በማድረግ የደቆሰውና የፈጨውን በተስፈኞቹ ብአዴንና ኦህዴድ ላይ በመድፋት በድንፋታ ኢህአዴግ የሚለውን የድርጅቱን ሥራ አስፈጻሚ መግለጫ በማውጣት መጠናቀቁ ከራሱ ከአገዛዙ የሚዲያ ተቋማት … [Read more...] about ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!
የገዱ አንዳርጋቸው ፈተና
በህወሓት ተመልምለውና ለሥልጣን በቅተው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ “የለውጥ ኃይል” እየተባሉ ከሚወደሱት መካከል አንዱ የሆነው ገዱ አንዳርጋቸው ለምስክርነት መጥሪያ ተቆርጦለታል። ገዱና ሌሎች ህወሓት እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ የሠራው ብአዴን አባላት የተጠሩት በነ ንግሥት ይርጋ ክስ በመከላከያ ምስክርነት ነው። ህዝባዊ ዓመጹ የተነሳው “በመልካም አስተዳደር ችግር” ምክንያት እንደነበር እነ ገዱ በተደጋጋሚ በየሚዲያው ሲናገሩ ቆይተዋል። ዓቃቤሕግ ደግሞ ክሱን የመሠረተው ሕዝባዊ ዓመጹን ከ“ሽብር” ጋር በማገናኘት ነው። በ“ለውጥ ኃይልነት” ሲወደስ የነበረው ገዱ አንዳርጋቸው ታማኝነቱ ለማን እንደሆነ በይፋ የሚያሳይበት ፈታኝ ወቅት ላይ የሚገኝ ሲሆን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች “አንገቱ ላይ ያለውን ገመድ ለማጥበቅ በህወሓት የታቀደ ሤራ ነው” ብለውታል። በተለይ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ደመቀ መኮንን … [Read more...] about የገዱ አንዳርጋቸው ፈተና
ኦህዴድ በህወሓት ላይ ላወጣው መግለጫ ሃይለማርያም ምላሽ ሠጠ
በጨለንቆ በተፈፅመው የጅምላ ግድያ በስተጀርባ ማን ነው ያለው ? የኢፌዲሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 87 (3) ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት የአገርን ሉዓላዊነት ለማሰከበር ነው የተቋቋመው። በዚሁ ንዑስ አንቀፅ 4 እና 5 ስር የአገር መከላከያ ሰራዊት በማንኛውም ጊዜ ለህገመንግስቱ ታዛዥ በመሆን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ውግንና ሳያሳይ ነፃ ሆኖ የአገር ደህንነት የመጠበቅ ስራውን እንደሚሰራ ይደነግጋል። ይሄው የመከላከያ ሰራዊቱ ከውጭ የሚመጣውን የአገሪቱን ጠላት ለመከላከል በአገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች የተገነባ ከተቋቋመለት አላማ ውጭ ታሪካዊ ስህተቶችን በህዝቦች ላይ ሲፈፅም ታይቷል። የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 8 (1-5) ስር የአገሪቱ ህዝቦች ሉዓላዊነት አስመልክቶ የአገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦና ህዝቦች የኢተዮጵያ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት መሆናቸው ይደነግጋል። ይህ ህገ-መንግስት የአገሪቷ … [Read more...] about ኦህዴድ በህወሓት ላይ ላወጣው መግለጫ ሃይለማርያም ምላሽ ሠጠ