የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር አሜሪካ ስልክ ደውለው መረጃ አሳልፈው በመስጠታቸው ዋጋ የሚያስከፍል ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተሰማ። አፈጉባዔው እንደተቀጣሪ ሪፖርተር በአሜሪካዊ ዜግነት አማራ ክልል ሆኖ ዜና ሲያሰራጭ የነበረው አቶ ተዋቸው ደርሶ የመታሰሩን ዜና ነው በስልክ ያሳበቁት። አቶ ተዋቸው መታሰሩን ዘሃበሻ “ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ባለሥልጣን ነገሩኝ” ሲል ነው የዘገበው። በዚሁ መነሻ አቶ ተዋቸውን አስመልክቶ መረጃ ለማሰባሰብ የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ ባደረገው ማጣራት በቀጥታ ለእስር የዳረገው ምክንያት ባይታወቅም፣ የግንኙነት ሰንሰለቱን ተከትሎ በርካታ መረጃ እንደተገኘበት ለማወቅ ተችሏል። ሰላማዊ መንገድን አማራጭ አድርገው ከማይከተሉ ኃይላት አመራሮች ጋር ግንኙነት አለው የሚለው ግን ለመታሰሩ ከተነገሩት ምክንያቶች ገዝፎ የወጣው … [Read more...] about አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ