• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የገዱ አንዳርጋቸው ፈተና

December 22, 2017 03:27 pm by Editor Leave a Comment

በህወሓት ተመልምለውና ለሥልጣን በቅተው ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ “የለውጥ ኃይል” እየተባሉ ከሚወደሱት መካከል አንዱ የሆነው ገዱ አንዳርጋቸው ለምስክርነት መጥሪያ ተቆርጦለታል። ገዱና ሌሎች ህወሓት እንደ ጭቃ ጠፍጥፎ የሠራው ብአዴን አባላት የተጠሩት በነ ንግሥት ይርጋ ክስ በመከላከያ ምስክርነት ነው።

ህዝባዊ ዓመጹ የተነሳው “በመልካም አስተዳደር ችግር” ምክንያት እንደነበር እነ ገዱ በተደጋጋሚ በየሚዲያው ሲናገሩ ቆይተዋል። ዓቃቤሕግ ደግሞ ክሱን የመሠረተው ሕዝባዊ ዓመጹን ከ“ሽብር” ጋር በማገናኘት ነው። በ“ለውጥ ኃይልነት” ሲወደስ የነበረው ገዱ አንዳርጋቸው ታማኝነቱ ለማን እንደሆነ በይፋ የሚያሳይበት ፈታኝ ወቅት ላይ የሚገኝ ሲሆን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች “አንገቱ ላይ ያለውን ገመድ ለማጥበቅ በህወሓት የታቀደ ሤራ ነው” ብለውታል። በተለይ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና ደመቀ መኮንን በመከላከያ ምስክርነት ተቶጥረው መጥሪያ ሳይቆረጥላቸው መቅረቱ ጉዳዩን ልዩ ትኩረት አሰጥቶታል።

ጌታቸው ሽፈራው በፌስቡክ ገጹ በዘገበው መሠረት፤ “ምስክሮቹ ለታህሳስ 12/2010 ዓም ቀርበው እንዲመሰክሩ ትዕዛዝ ተፅፎ የነበር ቢሆንም መጥሪያው ዘግይቶ በመውጣቱ አልደረሳቸውም። ታህሳስ 12/2010 ዓም ተከሳሾቹ ተነጣጥለን ወደ ችሎት አንገባም በማለታቸው ጉዳዩ ሳይታይ ቀርቷል።” ፈተናው ግን ሳይታይ የሚቀር አልሆነም።

የጌታቸው ሽፈራው በሙሉ ዘገባ እንዲህ ይነበባል፤

የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር አቶ ሙሉጌታ ወርቁ፣ የጎንደር ከንቲባ አቶ ተቀባ ተባባል እና ስለ ህዝባዊ አመፁ ማስረዳት ይችላሉ የተባሉ ባለስልጣናት እና የፖሊስ አዛዦች በእነ ንግስት ይርጋ ተፈራ ክስ መዝገብ ስር ለተከሰሱት 6 ግለሰቦች የመከላከያ ምስክር ሆነው (ታህሳስ 12፤ 2010) እንዲቀርቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አዟል።

ባለስልጣናቱ ህዝባዊ አመፁ በመልካም አስተዳደር ችግር የተነሳ ግጭት እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት በሚዲያ ቀርበው ያስረዱ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ ህዝባዊ አመፁን ከ”ሽብር” ወንጀል ጋር በማገናኘት ተከሳሾቹ ላይ የ”ሽብር” ክስ መስርቶባቸዋል።

በተጨማሪም ተከሳሾች ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንም በመከላከያ ምስክርነት የቆጠሩ ሲሆን የሁለቱ ባለስልጣናት መጥሪያ አልወጣም ተብሏል።

በእነ ንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ ስር የተከሰሱት ንግስት ይርጋ ተፈራ፣ አለምነህ ዋሴ ገ/ማርያም፣ ቴዎድሮስ ተላይ ቁሜ፣ አወቀ አባተ ገበየሁ፣ በላይነህ አለምነህ አበጀ እና ያሬድ ግርማ ኃይሌ ናቸው።

ተከሳሾቹ በምርመራ ወቅት በህዝባዊ አመፁ እጃቸው እንዳለበት እና የ”ሽብር ወንጀል” ፈፅመናል ብለው በሀሰት እንዲያምኑ ለማድረግ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ሲገልፁ የቆዩ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ ንግስት ይርጋ ጥፍሮቿ እንደተነቀሉ በክስ መቃወሚያዋ ላይ ተገልፆአል። ሌሎች ተከሳሾችም ያልፈፀሙትን ፈፅማችሁታል ተብለው በደል እንደደረሰባቸው መግለፃቸው ይታወሳል።

ከባለስልጣናት ባሻገር የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች፣ ጋዜጠኞች፣ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም፣ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ሌሎች ምሁራንም በተከሳሾቹ በመከላከያ ምስክርነት ተቆጥረዋል። ምስክሮቹ ለታህሳስ 12/2010 ዓም ቀርበው እንዲመሰክሩ ትዕዛዝ ተፅፎ የነበር ቢሆንም መጥሪያው ዘግይቶ በመውጣቱ አልደረሳቸውም። ታህሳስ 12/2010 ዓም ተከሳሾቹ ተነጣጥለን ወደ ችሎት አንገባም በማለታቸው ጉዳዩ ሳይታይ ቀርቷል።

ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Law, Politics Tagged With: andm, eprdf, Full Width Top, gedu, Middle Column, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule